በ12ኛ ሳምንት ክለቦች ውጤት እንዲስመዘግቡ የረዳቸው ጠንካራ ጎናቸው እና ለነጥብ ማጣታቸው እንደምክንያትነት ናቸው ያልናቸውን እንደሚከተለው አቅርበናል።
አሰፈሪ የቅዱስ ጊዮርጊስ አጥቂዎች
ከቅርብ ጨዋታዎች ወዲህ ግብ ባያስቆጥር እንኳን ፈረሰኞቹ የግብ አጋጣሚዎች እንዲፈጥር በመታተር የተጋጣሚ ቡድን ፋታ እየነሱ ያሉት የፊት መስመር ተጫዋቾቹ። ትላንት ደግሞ በሚገባ ተቀናጅተው ሲዳማ ቡና ላይ ግማሽ ደርዘን ግብ ማስቆጠር ችሏል። በተለይ ደግሞ የጌታነህ ከበደ እና ጋዲሳ መብራቴ ወደ ጥሩ አቋም መመለስ የፈረሰኞቹ የፊት መስመራቸው እንዲፈራ ያደረጉ ተጫዋቾች ናቸው
- ማሰታውቂያ -
አሰደናቂው የወላይታ ድቻ አጨዋወት
በጊዚያዊ አሰልጣኝ ደለለኝ ደቻሳ እየተመራ ድንቅ ጉዞ እያደረገ የሚገኘው ወላይታ ድቻ። በሜዳው ድሬዳዋን ሲያሸንፍ የነበረው አጨዋወት ለተጋጣሚ የሚረብ እና በርከት ያሉ የግብ ሙከራዎችን እያደረገ ይገኛል። በተለይ አማካዩ እንድሪስ አህመድ አመቻችቶ ወደ ፊት የሚለቃቸው ኳስች ከፊት መስመር የሚገኙት ባየ ገዛኻኝ፣እዮብ አለማየሁ እና ቸርነት ጉግሳ ወደ ግብነት በመቀየር ቡድኑን ወደ ወጤታማ እንዲሆን እያደረጉ ያሉ ተጫዋቾች ናቸው።
የስሁል ሽረ ለዘብተኛ አካሄድሀ
በራጅ ቀጠናው ሲንደፋደፍ የነበረው ስሁል ሽረ ጥሩ አቋም እያስመዘገብ ወደ መሪዎቾ ዳዴ እያለ መጠጋቱን ቀጥሎበታል። አይሰበሬው የተከላካይ ክፍላቸው እና ግብ ለማስቆጠር ምህረት የሌለው የፊት አጥቂዎች ታግዞ ከጨዋታ ነጥቦችን እያገኘ ይገኛል። ግብ አስቆጥሮ ከማሸነፍ በላይ ከቅርብ ጨዋታዎች ወዲህ በጠጣር ተከላካዮቻቸው እና ግብ ጠባቂው ወንድወሰን አሸናፊ የግል ብቃት ከሊጉ በየጨዋታው ዝቅተኛ ግብ እንዲቆጠር ማድረግ ችለዋል
የድሬዳዋ ደከማ የመከላከል ስፍራ
የድሬዳዋ ደካማ የመከላከል ስፍራ በቀላሉ ተለካጣሚ ተጋላጭ ከመሆኑ የተነሳ በርካታ ነጥቦችን ለመጣል ተገደዋል። ቡድኑ ትላንት በወላይታ ድቻ 3-0 የተሸነፈበት የዚህ ሳምንት ጨዋታ። በተለይ በመጀመሪያዎቹ አጋማሽ የነበረው የተከላካይ ስፍራ ያልተቀናጀ አጨዋወት። የቡድኑ ተከላካይ ስፈራ ለወደፊት መጠገን እንዳለበት ቁልጭ አድርጎ ያሳየ ነበር። የበረከት ሳሞኤል የግል በቃት በመጠኑም ቢሆን ስፍራውን ቢረጋጋውም የአጣማሪዎቹ ስህተት ግን ዋጋ ከማስከፈል ወደኋላ አይልም።
ዋጋ እያስከፈለ ያለው የሲዳማ ቡና ተከላካይ
የፈቱዲን ጀማል መውጣት ተከትሎ ሁነኛ የመሀል ተከላካይ ለማግኘት እየተቸገረ የሚገኘው ሲዳማ ቡና። አሁን በመሀል ተከላካይነት እየተጫወተ የሚገኘው ወጣቱ ተከላካይ ጊት ጋትኮች ከብስለት ጋር በተያያዘ የሚሰራቸው ስህተቶች ቡድኑ ግቦች እንዲቶጠሩበት ምክንያት ሲሆን። በቅዱስ ጊዮርጊስ በርካታ ግቦች እንዲያስተናግዱ ያደረጋቸው የዚህ ነፀብራቅ ነው።