ሀትሪክ ስፖርት፤ ሀትሪክ ስፖርት፤ ሀትሪክ ስፖርት ማክሰኞ በገበያ ላይ ባለቀለሟ፣ ተወዳጇ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ከእናንተ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮን ይዛለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ለመሆኑ በነገ እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ዘገባዋ ነገ ከምታስነብቦት ውስጥ THE BIG INTERVIEW በሚለው ተወዳጅ አምዷ ኢትዮጵያ ቡና ከአሰልጣኝ ዲዲየር ጎሜዝ ጋር ከተለያየ በኋላ ክለቡን በኃላፊነት እንዲመራው የተቀጠረው አሰልጣኝ ገዘኸኝ ከተማ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጥያቄ ቀርቦለት ምላሹን ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ እትሟ ይዛላችሁ የቀረበችው የፕሪምየር ሊጉን የመጀመረያው ዙር በቀዳሚነት ካጠናቀቀው የመቐሌ 70 እንደርታ ተጨዋቾች ውስጥ ያሬድ ሀሰንን በክለቡ ወቅታዊ አቋም ዙሪያ እና ስለሁለተኛው ዙር ውድድራቸው አናግረነው እሱም የሠጠውን ምላሽ ይዘንላችሁ እንቀርባለን፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ ደግሞ ከሲዳማ ቡናው አሰልጣኝ ዘርዓይ ሙሉ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልልስ ነው፤ አሰልጣኝ ዘርዓይ እግር ኳስን ለ14 ዓመታት የተጫወተ ሲሆን ይህን በአሁን ሰዓት በአሰልጣኝነት ሙያ ላይ የተሰማራውን ወጣት አሰልጣኝ በተለያዩ የኳስ ህይወቱ ዙሪያና ስለ አሰልጣኝነቱ እንደዚሁም በቡድኑ ዙሪያ ጠይቀነው የሰጠውን ምላሽ እንዲያነቡት ጋብዘንዎታል፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋስ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
ከወዲሁ እንንገሮት ነገና ረቡዕ ስለሚካሄዱት የሻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታ ዘገባዎች፣ በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ስለ ሮሜሉ ሉካኩ የብቃት ለውጥ እና ስለ ማንቸስተር ዩናይትድ ተከታታይ የውጤታማነት ሚስጠር እንደዚሁም ደግሞ አርሰናል ከቶተንሃም ጋር ባደረገው ጨዋታ ነጥብ ስለመጋራቱ እና ሌሎችም በርካታ መረጃዎችን ይዘንሎት ቀርበናል፤ የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡