እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ ተወዳጇና ሳምንታዊዋ ሀትረክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ የሚወዷቸውን የሀገር ውስጥና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ይዛሎት በመቅረብ ልታስነብቦት ተዘጋጅታለች፤ በነገው እትሟም ከሀገር ውስጥ ይዛሎት ከምትቀርበው ዘገባ መካከል ዋና ዋና ከሆኑት ጉዳዮች ውስጥ በሩሲያ አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የዓለም ዋንጫ ግጥሚያውን ከሚመሩት የአገራችን አልቢትሮች መካከል ብቸኛውና ከበርካታ ዓመታት በኋላም ከአገራችን ይህንን በብዙዎች ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀውን ውድድር ለመምራት እየተዘጋጀ ስለሚገኘው ኢንተርናሽናል አልቢትር በአምላክ ተሰማ ምርጥና የሚወዱትን ቃለ-ምልልስ አቅርበንሎታል፤ ኢንተርናሽናል አልቢትር በአምላክ ተሰማ የዓለም ዋንጫን ሊመራ ስለመዘጋጀቱና በሌሎች ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ምን ብሎ ይሆን? ነገ ይጠብቁን፤ ከሀገር ውስጥ ሌላው ዘገባችን ቅ/ጊዮርጊስና ወላይታ ድቻ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የውድድር ተሳትፎአቸው በአዲስ አበባ ስታዲየምና በዳሬሰላም በፋሲካ ዋዜማ ስለሚያከናውኑት ጨዋታ፤ እንደዚሁም ከግጥሚያው ምን ውጤትን ለማስመዝገብ እንዳቀዱ ከቡድኑ ተጨዋቾች መካከል ከቅ/ጊዮርጊስ በሰሞኑ የቡድኑ ጨዋታ ላይ ካፒቴን ሆኖ እያገለገለ የሚገኘውን ምንተስኖት አዳነንና ከወላይታ ድቻ ደግሞ ግብ ጠባቂው ወንድወሰን ገረመውን አናግረናቸው ምላሽን ሰጥተውናል፤ ሌላው በነገው የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እትም የቀድሞ እግር ኳስ ተጨዋቾችን በምናስታውስበት የኦልዲስ በት ጉዲስ ዓምዳችን ላይ ይዘንላችሁ የምንቀርበው ተጨዋች በሀገራችን ክለቦች የኢንተርናሽናል የውድድር ተሳትፎና ታሪክ ብዙ ጨዋታዎችን በተከታታይ ድል በማድረግና እስከ ግማሽ ፍፃሜውም ደረጃ በመግባት ረጅሙን የስኬትና የድል ጉዞ በብቸኝነት ከተጓዙት ክለቦች አንዱ ለሆነው የመድን ክለብ በአማካይ ስፍራ በመጫወት በችሎታው በብዙዎቹ የስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ ይደነቅ የነበረውን ጌቱ መልካን ያቀረብንላችሁ ሲሆን እሱም ለቀረቡለት ጥያቄዎች ምላሹን ሰጥቷል፤ ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም ነገ ለእናንተ ልታስነብቦት ከተዘጋጀችው መረጃዎች ውስጥ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ወሳኝና ተጠባቂ ከሚባሉት ግጥሚያዎች መካከል ነገና ረቡዕ ስለሚካሄዱት የጁቬንቱስና የሪያል ማድሪድ እንደዚሁም ደግሞ የሊቨርፑልና የማንቸስተር ሲቲ ተጠባቂ ጨዋታዎችን አስመልክተን ሰፊና የሚወዱት መረጃን ይዘንሎት የቀረብን ሲሆን ሌላው በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግም ለማንቸስተር ዩናይትድ እየተጫወተ ስለሚገኘው ሮሜሉ ሉካኩ እስከ ውድድሩ መጨረሻ ምን ያህል ግብ እንደሚያስቆጥርና ስለ አርሰናል ጣፋጭ ድልና አቡሚያንግ ከፍ ብሎ ስለታየበት ምሽትም ይዘንሎት የቀረብነው ዳሰሳ ይጠቀሳል፡፡ ሀትሪክ የእናንተ ናት ያንብቧት ሀትሪክ ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ ዘገባዎችንም ይዛሎት ቀርባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች ባሉት hatricksport.com ድረ-ገፃችን ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ
ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ፤ ዘገባዎቿን ይወዷታል፤ እንዳታመልጦት
Managing Editor at Hatricksport Website