ሀትሪክ ስፖርት ሀትሪክ ስፖርት ሀትሪክ ስፖርት
የእርስዎ ናትና ያንብቧት
ሳምንታዊዋ ባለቀለሟ እና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ከእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ጋር ዳግም ለመገናኘት ስራዋን አጠናቃ ወደ ማተሚያ ቤት አምርታለች፡፡
ሀትሪክ ሰፖርት ነገ ለንባብ ስትበቃ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ዘገባዋ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ኢሳያስ ጅራ በተወዳጅነቱ የብዙዎችን ትኩረት እየሳበ ከመጣው ዘ ቢግ ኢንተርቪው ዓምድ ላይ በኳሱ ዙሪያ ሰፋ ያለ ቃለ-ምልልስን የሰጡ ሲሆን ከእሱ ባሻገርም ሀገራችንን በኢንተርናሽናል የውድድር መድረክ በመወከል የሚሳተፉት ጅማ አባጅፋርና መከላከያም ዛሬና ነገ ከተጋጣሚዎቻቸው የጅቢቲው ቴሌኮምና ሬንጀርስ ጋር በሚያደርጉት የመልስ ጨዋታ ዙሪያ አሰልጣኞቹን በማናገር ምላሽን ሰጥተዋል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶም በ4ኛው ሳምንት ከተደረጉት ግጥሚያዎች መካከል ቅ/ጊዮርጊስ ስሁል ሽሬ እንደስላሴን ባሸነፈበት እና ኢትዮጵያ ቡናም ወደ ጎንደር ተጉዞ ከፋሲል ከተማ ጋር አቻ ስለተለያበት ጨዋታ ከቡድኑ ተጨዋቾች መካከል ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሁለት የድል ግብ ያስቆጠረውን አቤል ያለው ከኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ሳምሶን ጥላሁንን አናግረናቸው ምላሽን ሰጥተዋል፡፡ሰ
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የሰሜን ለንደንን ወደ ቀይነት ስለቀየረው የአርሰናል ጣፋጭ ድል የሚወዱት ዘገባ የቀረበ ሲሆን የሊቨርፑሉ ሳዲዬ ማኔም የእኔ የምንግዜም ምርጡ ተጨዋች ሮናልዲኒሆ ነው ስላለበት እና ስለ ጆሴ ሞውሪኖም ስለ ቡድናቸው እና ሙያቸውን አስመልክቶም ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡትን ምላሽ እናቀርብሎታለን፡፡
ሀትሪክ ነገ ብቻ ሳይሆን ሁሌም አታምልጦት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል
ሀትሪክ ስፖርት የእርስዎ ናትና ያንብቧት ሳምንታዊዋ ባለቀለሟ እና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማክሰኞም ከእናንተ ውድ አንባቢዎቿ ጋር ዳግም ለመገናኘት ስራዋን አጠናቃ ወደ ማተሚያ ቤት አምርታለች፡፡
Hatricksport team