ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ምርጫዎ ትሁን!
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በሳምንት አንድ ቀን ለንባብ የምትበቃ ተወዳጅ እና ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ ስትሆን ዘወትር ማክሰኞም በገበያ ላይ ስትውል የተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የባህር ማዶ ዘገባዎችን ለእናንተ ውድ አንባቢዎቿ በማስኮምኮም የምትታወቅም ናት፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ለመሆኑ በነገው የማክሰኞ እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛሎት ከተፍ ብላ ይሆን? በሀገር ውስጥ ዘገባዋ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW ዓምዷ የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ኤክስኪዩቲቭ ኤዲተር የሆነው ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ለሲዳማ ቡና፣ ለቅ/ጊዮርጊስ፣ ለአርባምንጭ ከተማ፣ ለጅማ አባቡና እና ለወልዲያ ከተማ ከተጫወተው የአሁን ሰዓት ላይ ደግሞ ለፕሪምየር ሊጉ መሪ መቐሌ 70 እንደርታ በመጫወት ላይ ከሚገኘው የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድንቅ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ቢያድግልኝ ኤልያስ ጋር በኳሱ ሕይወት ዙሪያና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለና የሚወዱትን ቃለ-ምልልስን አድርጎ ተጨዋቹ ምላሹን ሰጥቷል፤ ቢያድግልኝ ኤልያስ ከሰጠው ቃለ-ምልልስ ውስጥ ምን ብሎ ይሆን? ከሰጣቸው ምልልሶች ውስጥ በተጨዋችነት ዘመኔ “ኳስ ከመጠለዝ ይልቅ ኳሱን ይዤ መጫወቴ ዋጋ አስከፍሎኛል፤ የብዙ አሰልጣኞች ሰለባም አድርጎኛል የሚል ምላሽን የሰጠ ሲሆን ሌሎችንም የሚወዱትን ምልልሶች ከጋዜጣው ጋር አድርጓል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በሌላ የሀገር ውስጥ እትሟ በሁለተኛው ዙር የተጨዋቾች ዝውውር መስኮት ሽረ እንደስላሴን በመልቀቅ ኢትዮጵያ ቡናን ስለተቀላቀለው ሄኖክ ካሳሁን የምናስነብቦት ነገር ይኖራል፤ ለመሆኑ ሄኖክ ማነው ስለተጨዋቹ የኳስ ሕይወት ቆይታ ቃለ-ምልልስን ያደረግንለት ሲሆን እሱም የተለያዩ ምላሾቹን ሰጥቷል፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና ፊርማውን ያኖረው ሄኖክ ካሳሁን ከዓመታቶች በፊት
በማን.ዩናይትድና በአርሰናል ጨዋታ በተፈጠረ ፀብ ለ1 ዓመት ከሰባት ወር መታሰሩን ታውቃላችሁ? ተጨዋቹ ስለታሰረበት ምክንያት ይነግራችኋል፤ አሁንስ ሄኖክ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛል? ስለ አዲሱ ክለቡስ ምን ይላል? የኳስ ሕይወቱስ ምን ይመስላል? በነገው የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ላይ ምላሾቹን ጠብቁ፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በቅ/ጊዮርጊስ የአንደኛው ዙር የውድድር ተሳትፎ ዙሪያ እና በሁለተኛው ዙር የሊጉ ውድድር በምን መልኩ ለመቅረብ እንደተዘጋጁ ከበኃይሉ አሰፋ /ቱሳ/ ጋር ቆይታን አድርገን ተጨዋቹ የራሱን ምላሽ ሰጥቷል፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የዘወትር ምርጫዎ ትሁን!
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎችም ነገ ለንባብ ስትበቃ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን አስመልክቶ ከምታስነብቦት ውስጥ አርሰናል የቶፕ አራት ተስፋውን ስላሳደገበት ጣፋጭ ድል፤ ማንቸስተር ሲቲ በካራቦካፕ ቼልሲን አሸንፎ ዋንጫ ስለማንሳቱ፣ ከእንግሊዛዊው የማንቸስተር ዩናይትዱ ተጨዋች ራሽፎርድ ስኬታማ ጉዞ ጀርባ ስላለው ሚስጥር እና የሊቨርፑሉ አጥቂ መሐመድ ሳላ በአሁን ሰዓት ጫና ቢኖርብንም ማንቸስተር ሲቲም በጫና ውስጥ ይገኛል ስለማለቱ እና ግላዊ ክብሮችም እንደማያስጨንቀው ስለመናገሩ በሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ላይ ተዳስሷል፡፡ ሀትሪክ ሌሎችም ዘገባዎች አሏት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡