ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ በገበያ ላይ
ዘወትር ማክሰኞ ለንባብ የምትበቃው ሳምንታዊዋ እና ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ ማለዳም ከእጅዎ ትገባለች፤ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን? ከሀገር ውስጥ በየሳምንቱ ከምናስነብቦት ቃለ-ምልልሶች መካከል ዘ ቢግ ኢንተርቪው ይዘን የቀረብነው ተጨዋች ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውቶ ያሳለፈውን የቀድሞ የመከላከያ እና ዳሽን ቢራ እንደዚሁም ደግሞ ለፋሲል ከተማ የተጫወተውን ዓይናለም ኃይለን ነው፤ ዓይናለም ከሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ጋር ባደረገው ቃለ- ምልልስ ምን ብሎ ይሆን?
ከሰጣቸው ምላሾች መካከል
– “የሀገራችን ተጨዋቾች ያደጉ ትልቅ ደረጃም
የደረሱ አይደሉም”
– “ዘረኝነቱ ካልቀረ የተጨዋቾች እንጀራ
ይዘጋል እንጂ እግር ኳሱ ቢታገድ ደስ
ይለኛል”
– “በሄድኩበት ቦታ ተጨዋቾቹ ሳይቀር ወደ
ዘረኝነት መሄዳቸው ያሳስበኛል” ብሏል፡፡
የ
የፋሲሉ አይናለም ኃይለ
ሀትሪክ በሌላ መረጃዋ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቀድሞ ተጨዋች ሸዋረጋ ደስታ ያቋቋመው የሸዋረጋ ደስታ የባንክ ማሰልጠኛ ፕሮጀክት እውቅና ስለማግኘቱ ከእሱ ጋር ስለተደረገው ቃለ-ምልልስ እንደዚሁም ደግሞ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዙሪያ ኢትዮጵያ ቡና ወደ መቀሌ በማምራት ስላሳካው ድል ከአህመድ ረሺድ ሺሪላ ጋር ስለተደረገው ቃለ-ምልልስ እና በቅዱስ ጊዮርጊስ እና በባህርዳር ከተማ መካከል ተደርጎ ስለነበረው ጨዋታ ከአሸናፊው ቡድን ባህርዳር ከተማ አሰልጣኝ ጳውሎስ ጌታቸው ማንጎ ጋርና ከተሸናፊው ቡድን ተጨዋች ምንተስኖት አዳነ ጋር የተደረገ ቃለ-ምልለስ ቀርቦሎታል፡፡
ሀትሪክ ስፖርት በባህር ማዶ ዘገባዎቿም የአርሰናልን ያለመሸነፍ ሪከርድ ስላስቀጠለው ኮከብ አሌክሳንደር ላካዜት እንደዚሁም ደግሞ የቼልሲን ስብስብ በማሰልጠኔ እኮራለው ስላሉት ሳሪ እና ስለ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሰፋ ያለ መረጃ ቀርቦሎታል፤ ሀትሪክ ሌሎችም መረጃዎችን አካታ ነገ እናንተን ለማግኘት ዝግጁ ሆናለች፤ ሀትሪክ አታምልጦት፤ የእናንተው ናት፡፡
የሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገ በገበያ ላይ
Hatricksport team