ሀትሪክ በነገው እትሟ
ባለቀለሟሟዋ እና ሳምንታዊዋ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ነገም እናንተን በእትሟ ልታገኞት ስራዋን አጠናቃለች፤ ሀትሪክ በነገው እትሟ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን፤
በሀገር ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምድ የመከላከያ ስፖርት ክለብ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል ደረጀ መንግስቱ በክለባቸው እና የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ እያስተላለፈው ባለው ውሳኔ ዙሪያ ከጋዜጣው ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽን ሰጥተዋል፤ ሌላው በሀገር ውስጥ የምናስነብባችሁ ዘገባ የስዑል ሽረ ፕሬዝዳንት አቶ ኪዳነ ገ/መድህንም እንዲሁ የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ የፕሪምየር ሊግ መጀመርን አስመልክቶ ሰሞኑን እየወሰናቸው ባሉት ጉዳዮች ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎች ቀርቦላቸው ምላሻቸውን ሰጥተዋል፤ ከዛ ውጪም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በቻን አፍሪካ ዋንጫ ሩዋንዳን ስለሚፋለምበት የመልስ ጨዋታ የቡድኑ ተጨዋች ደስታ ደሙም የሚላችሁ ይኖራል፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዋስ ምን ይዛ ይሆን?
የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሊቨርፑል ተከታታይ ጨዋታዎችን በማሸነፍ ሪከርድን እየበጣጠሰ ስላለበት ጉዳይ፣ ለአርሰናል የመጀመሪያ የድል ጎሉን ማስቆጠር ስለቻለው ዴቪድ ሉዊዝ፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ከውጤት ጋር እየተጣላ ስላለበት ጉዳይና ስለ ቼልሲ በአሸናፊነት እየተጓዘ ስላለበት ሁኔታ እና ሌሎችን መረጃዎች ከጋዜጣችን ላይ ያገኙታል፡፡
ሀትሪክ የእርስዎ ናት አታምልጦት፡፡