ሀትሪክ ስፖርት ነገ ማክሰኞ ለንባብ ስትበቃ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ወጥታ ይሆን? በዚህ ዙሪያ ምንም አያስቡ፤ ጫፍ ጫፉን ትነግሮታለች፡፡
ሀትሪክ በሀገር ውስጥ የስፖርት ዘገባዋ በየሳምንቱ ከምታስነብቦት ውስጥ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት THE BIG INTERVIEW አምዷ የሀትሪክ ስፖርት ማኔጂኒግ ኤዲተር እና ጋዜጠኛ የሆነው ይስሃቅ በላይ የጅማ አባጅፋር አሰልጣኝ ከነበረው እና አሁን ከክለቡ ጋር ከተለያየው ዘማሪያም ገ/ጊዮርጊስ ጋር ሰፋ ያለ ቆይታን አድርጎ በስልጠና ህይወቱ፤ ከጅማ ጋር በመለያየቱ ዙሪያና ሌሎችንም ጥያቄዎች በቃለ-ምልልስ መልኩ አድርጎለት ተጨዋቹ ምላሾቹን ለሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ ሰጥቷል፡፡
ሀትሪክ በሌላ የሀገር ውስጥ ዘገባዋ የምታስነብቦት በዴንማርክ አስተናጋጅነት ተካሂዶ ስለነበረው እና በኢትዮጵያ አሸናፊነት ስለተጠናቀቀው የዓለም ሀገር አቋራጭ ሻምፒዮና ውድድር የአትሌቶቻችንን ገድል አስመልክቶ የሚወዱትን መረጃ ያቀረብንሎት ሲሆን ከዛ ውጪም የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድርን አስመልክቶ በሳምንቱ መጨረሻ መቐለ 70 እንደርታንና ወልዋሎ አዲግራትን በማሸነፍ ድል ከቀናቸው ክለቦች መካከል የፋሲል ከነማውን አሰልጣኝ ውበቱ አባተን እና የኢትዮጵያ ቡናውን ካፒቴን አማኑኤል ዩሃንስን አናግረናቸው ምላሻቸውን ሰጥተውናል፡፡
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎቿም የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግን አስመልክቶ ከቋሚ ቅጥሩ በኋላ ድል ስለቀናው የማንቸስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ስልሻየር ስለ አርሰናሉ አሰልጣኝ ሁናይ ኤምሪ እና ሊቨርፑል በወሳኙ ጨዋታ ቶተንሃምን በመጨረሻ ደቂቃ ጎል ድል ስላደረገበት ጨዋታ ሰፋ ያለን መረጃን አቅርበንሎታል፤ ሀትሪክ ሌሎች ሊያነቡት የሚችሉት ምርጥ ምርጥ ዘገባዎችም ያገኙባታል፡፡
ሀትሪክ የእናንተው ናት አታምልጦት፡፡
ሀትሪክን ከሳምንታዊ ጋዜጣዋ በተጨማሪ http://www.hatricksport.com/ ድረ-ገፃችን ላይ አዳዲስና ወቅታዊ መረጃዎችን ያገኛሉና አሁኑኑ ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፤ የሀትሪክ ቤተሰብም ይሁኑ፡፡
የሀትሪክ ጋዜጣ የነገው የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡