ሀትሪክ በነገው እትሟ
ተወዳጅ ጋዜጣዎ ሀትሪክ ስፖርት ነገ በገበያ ላይ ትውላለች።
ሀትሪክ በገበያ ላይ ስትውልም ምን ምን ጉዳዬችን ይዛ ወጥታ ይሆን?
በሀገር ውስጥ ዘገባ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ባተረፈላት The big interview አምድ የአዲስ አበባ ከተማ እግር ካስ ክለብ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽን ሰጥተዋል።
ሀትሪክ ከዛ ውጪ በፕሪምየር ሊጉ የእዚህ ሳምንት ጨዋታ ዙሪያ ከጅማ አባጅፋር ጋር አቻ ስለተለያየው የመቀለ 70 እንደርታ ክለብ ወቅታዊ አቅዋም እና የሊጉን መሪነት ባለፈው ሳምንት ስለመነጠቁ እንደዚሁም የሊጉ ሻምፒዮና ማን እንደሚሆን የቡድኑን ተጨዋች አሌክስ ተሰማን ጠይቀነው ምላሽ ሰጥቶናል።
ሀትሪክ ስለ ካናዳ ኦትዋ ማራቶንም የምትሎት አለ።
ሀትሪክ በባህር ማዶ ዘገባዎችስ ምን ጉዳዮች ይኖራት ይሆን?
የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ እና የኤሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታዎችን አስመልክቶም ምርጥ ዘገባ አላት።
የነገዋ ሀትሪክ አታምልጦት።