የ11ኛው ሳምት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ረቡዕ እና ሐሙስ የተከናወኑ ሲሆን እኛ ደግሞ የግብ ጠባቂዎች እንቅስቃሴ መሰረት አድርገን የተመለከትናቸውን ዓበይት የሳምንቱ ጉዳዮች አንሰተንላቹሀል።
ወንድወሰን አሸናፊ
ወንድ ወሰን አሸናፊ በምንተስኖት አሎ አለመኖር ተከትሎ ወደ ቋሚ አሰላለፍ የመጣው ግብ ጠባቂው ትላንት በነበረው ጨዋታ የኦኪኪ አፎላቢን ፍፁም ቅጣት ጨምሮ ሁለት ግብ የሚሆኑ አጋጣሚዎችን በማምከን ቡድኑን ተጨማሪ ግቦች ከማስተናገድ ታድጓል።
- ማሰታውቂያ -
ጃፋር ደሊል
በሶስት ሳምንታት ጥሩ አቋም ላይ የነበረው ጃፋር ደሊል ትላንት በርካታ ግቦችን አስተናግዷል። በሲዳማ ቡና 5-0 ለባዶ የተሸነፈው ወልዋሎ እንደቡድን ያደረጉት እንቅስቃሴ ለጎሉ መብዛት አስተዋፅኦ ቢኖረውም። ግብ ጠባቂው የሚሰነዘሩበት ጥቃቶች ለመመከት የሚያደርጋቸው እንቅስቃሴ ደከም ያሉ ነበሩ።
ሚካኤል ሳማኬ
የፋሲል ከነማ ሁነኛ ግብ ጠባቂው ሳማኪ ሚካኤል ምንም እንኳን ቡድኑ ነጥብ ቢጥልም በተከታታይ ሁለት ጨዋታዎች መረቡን ሳያስደፍር የወጣ ግብ ጠባቂ ነው።