በ12ኛ ሳምንት የተመለከትናቸውን ዋና ነጥቦች አንስተናል።
የተቆጠሩ ግቦች
የ12ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ትላንት እና ዛሬ በደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜውን ሲያገኝ። በዚህ ሳምንት በጠቅላላ 24 ግቦች ተቆጥረዋል ይህ ማለት ደግሞ ባለፈው ሳምንት ከተቆጠሩ ግቦች በ8 ከፍ ብሏል። ሊጉ ከተጀመረ 24 ግቦች ሲቆጠሩ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ነው። 20 ተጫዋቾች ግብ ሲያስቆጥሩ 16ቱ ግቦች በተለያዩ ተጫዋቾች የተቆጠረ ሲሆን እዮብ አለማየሁ ፣አህመድ ሁሴን፣አቤል ያለው እና ጌታነህ ከበደ ሁለት ሁለት ግቦችን ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው። የሳምንቱ ፈጣን ግብ ያስቆጠረው እዮብ አለማየሁ በ48ኛው ሰከንድ ሲሆን ፍፁም ገብረማርያም እና ሳሊፍ ፎፋና 81ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠሯቸው ግቦች በሳምንቱ ዘግይተው የተቆጠሩ ግቦች ናቸው። ሁለት ግቦች በፍፁም ቅጣት ምት አንድ ግብ ላይ ደግሞ በራስ መረብ ሲቆጠሩ። ሶስት ግቦች ደግሞ በውጭ ተጫዋቾች መቆጠር የተቆጠሩ ሆነው አልፈዋል።
- ማሰታውቂያ -
የተመዘገቡ ውጤቶች
በዚህ ሳምንት የተደረጉ ሁሉም ጨዋታዎች በባለሜዳዎቹ አሸናፊነት መጠናቀቅ የቻለ ሲሆን። ስድስቱ ከሜዳቸው ውጭ የተጫወቱ ቡድኖች የተቃራኒ መረብ ላይ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል። በአንድ ጨዋታ ማለትም የቅዱስ ጊዮርጊስ ጨዋታ እና ሲዳማ ቡና በጠቅላላ 8 ግቦች የታዩበት ጨዋታ ሆኖ ሲያልፍ። ሶስት ቡድኖች ደግሞ በተመሳሳይ 3-0 በሆነ ውጤት አሸንፏል። ሁለት ቡድኖች ብቻ አንድ ግብ ብቻ አስቆጥረው ሶስት ነጥብ ይዘው መውጣት ችለዋል። ወልቂጤ ከተማ ተከታታይ ሶስተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ኢትዮጵያ ቡና እና ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ ለተከታታይ ሁለተኛ ግዜ ሸንፈትን አሰተናግዷል። ሀድያ ሆሳዕና አሁንም ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ተቸግሯል።