ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡና ላይ የግብ ናዳ አውርዶ ከረጅም ወራት በኋላ የሊጉ አናት ላይ ተቀምጧል
ቅዱስ ጊዮርጊስ ሲዳማ ቡናን 6-2 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት ከመቐለ 70 እንደርታ በመረከብ ሊጉን በ23 ነጥብ መምራት የጀመረበትን ውጤት በዚህ ሳምንት አስመዝግቧል። በርካታ ተቃውሞችን እያስተናገደ የነበረው የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ሰርዳን ዥቪዥኖቭ ወደ ሊጉ መሪነት መመለሳቸው ትንሽ እፎይታን የፈጠረላቸው ይመስላል። ቅዱስ ጊዮርጊስም ከአንድ አመት በኋላ ነው የሊጉ መሪ መሆን የቻለው።
- ማሰታውቂያ -
ወልቂጤ የአሸናፊነት ጉዞ
ክትፎዎቹ በተከታታ ሶስተኛ ድላቸውን ባህርዳር ከተማን 2-0 በማሸነፍ አስመዝግበዋል። በዚህም ደረጃቸውን በማሻሻል በ17 ነጥብ 5 ደረጃ ላይ መቀመት የቻሉበት ውጤት መሆን ችሏል።
ወላይታ ድቻ ድሬዳዋን በታሪኩ ማሸነፍ ችሏል
ከ2008 ጀምሮ ግንኙነት የጀመረው የሁለቱም ቡድኖች ጨዋታ። የጦና ንቦች በአንድም አጋጣሚ ቡርቱካናማዎቹን አሸንፈው የማያውቁ ሲሆን። በዚህ ሳምንት ግን 3 ግቦችን በማስቆጠር ግብ ሳይቆጠርበት በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ከጨዋታ ብልጫ ጋር በማሸነፍ ታሪኩን ቀይሯል። በዚህ ጨዋታም የአመቱን ፈጣን ግብ በእዮብ አለማየሁ 48ኛው ሰከንድ ላይ ተቆጥራለች።
ኢትዮጵያ ቡና ወራጅ ቀጠና ውስጥ መገኘት
ድንቅ እንቅስቃሴን በማድረግ ጥሩ ውጤት ሲያስመዘግብ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና ከቅርብ ጨዋታዎች ወዲህ ግን በተከታታይ ነጥብ ከመጣሉ ባሻገር ወራጅ ቀጠና ውስጥ መገኘቱ ግን ግርምትን ፈጥሯል። የቅርብ ጨዋታዎችን ስንመለከት ኢትዮጵያ ቡና ማግኘት ከነበረበት 9ነጥብ ሊያገኝ የቻለው 1 ነጥብ ብቻ ነው።
ሀድያ ሆሳዕና እና ሽንፈት አልላቀቅ ተባብለዋል
ጥሩ መነቃቃት ላይ የነበሩት ነብሮቹ አሁንም በድጋሚ በአመቱ መጀመሪያ የነበረቸው ተመሳሳይ የውጤት ማጣት ውስጥ ገብተዋል። ተከታታይ ሶስት ጨዋታዎችን በመሸነፍ መግኘት ከነበረባቸው 9 ነጥብ ምንም ያላሳኩት ነብሮቹ አሁንም ከሊጉ ግርጌ ፈቀቅ እንዳይሉ አድርጓቸዋል።
አዳማ ከተማ
ከተጫዋቾች ደሞዝ ክፍያ ተዳምሮ ውጤት ቀውስ ውስጥ ገብቶ የነበረው አዳማ ከተማ። አንፃራዊ መሻሻሎችን እያመጡ ቢሆንም በሜዳቸው ነጥብ መያዝ ቢችልም ከሜዳቸው ውጭ ያለው ነጥብ ጨዋታ ግን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚገባ ነው።
ሀዋሳ ከተማ
ከሜዳው ውጭ ነጥብ ይዞ ለመመለስ እየተቸገረ ነው። በዚህ ሳምንትም በስሁል ሽረ 3-0 ሽንፈትን አስተናግዶ ተመልሷል።