አዲስ አዳጊዎቹ ሀድያ ሆሳአና ብኃይሉ ተሻገር(ኣኪራ) ና አፍወርቅ ኃይሉን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።በግርማ ታደሰ እየተመሩ በወቅቱ የተጨዋቾች ዝውውሩ ላይ ጥሩ ሚባል ተሳትፎ እያደረጉ ሚገኙት ሀድያ ሆሳእና የክረምቱ ፈራሚዎቻቸውን ወደ 9 ከፍ ያደረጉላቸውን ሁለት ዝውውሮች አጠናቀዋል።
ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ሁለተኛ ቡድን አድጎ ለዋናው ቡድን፣ለኢትዮጵያ ወጣት ብሄራዊ ቡድን አንዲሁም ኦሎምፒክ ቡድን መጫወት የችለው የመስመር አጥቂው ብኃይሉ ተሻገር ሀድያዎችን በአንድ አመት ውል ተቀላቅሏል።
በተጨማሪ ያለፋትን ሁለት ዓመታት ከወልዋሎ ጋር የተሳካ ጊዜ ያሳለፈው አፍወርቅ ኃይሉ ሀድያ ሆሳእናን በአንድ ዓመት ውል ለመቀላቀል ተስማምቷል።በአሰልጣኝ አብርሃም መብራህቱ ጥሪ ተደርጎለት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ኦሎምፒክ ቡድንን መወከል የችለው አፍወርቅ በያዝነው የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ባህርዳር ከተማን ለመቀላቀል በቃል ደረጃ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ውሉ ፌዴሬሽን ሄዶ ያልፀደቀ ስለነበር የተሻለ ጥቅም ወደ አቀረበለት ሀድያ ሊጓዝ ችሏል።