THE BIG INTERVIEW WITH MESERTE MANE
…መጽሐፍ ፅፎ ለንባባ ማብቃት
ምጥ አምጦ የመውለድ ያህል ስሜትን
ስለመፍጠሩ…
- ማሰታውቂያ -
“…እውነት ነው…፤…ሲጀመር የራሱ ደስ
የሚል ፈተና አለው… ሲያልቅ ግን የሚያባራ
ደስታን ነው በውስጥህ የማፈጥረው። …እኔም
መጽሐፌ ተፅፎ እሲኪያልቅ የተሠማኝ
ስሜት ልክ አንዲት ሴት አርግዛ፣ ዘጠኝ ወር
ሙሉ ፅንሱን በሆድዋ ተሸክማ፣ አምጣ፣
ተጨንቃ፣ በመጨረሻም ወልዳ ልጇን እቅፏ
ውስጥ አድርጋ ስትስም የሚሰማትን የተለየ
የደስታ ስሜት ነው በውስጤ የተፈጠረው፡፡
ባለፈው አርብ ከሴት ደራሲያን ማህበር
ፕሬዚዳንት ጋር በተገናኝበት ወቅት “…
እንኳን ደስ ያለሽ…”…ሣይሆን…“…
እንኳን…ማርያም…ማረችሽ…”…ያለችኝም…
መጽሐፍ ጽፎ ለንባብ ማብቃት…አርግዛ
ወልዳ…የመሳም ያህል…ከመሆኑ አንፃር
ይመስስስስስአለኛል…፡፡”
…ከእግር ኳስ አሰልጣኝነት ወደ
ደራሲነት…?
“…ወደ ደራሲነት…ተሸጋግሬያለሁ
ብዬ አላስብም…፤…አሁንም የማወራህ
እንደ ደራሲ አይደለም…፤…ምክንያቱም…
እኔ ለደራሲነት ገና አልበቃሁም…፡፡…
ይህንን መጽሐፍ የፃፈው…ጋዜጠኛ ዘርዓይ
እያሱ ነው…፡፡ ብዙ ሥራዎችን ብሰራም
በማረምም፣ በማስተካከል፣ በመገምገም ደረጃ
የተለያዩ ሰዎች ተሳትፈውበታል፤…ከዚህ
አንፃር… ከአሰልጣኝነት…ወደ ደራሲነት…
ተሸጋግሬያለሁ ለማለት ይቸግረኛል…፡፡
…ከዚህ ይልቅ… ያለችኝን…ትንሽ ታሪክ
ለማካፈል…እንደሞከርኩ ይቆጠርልኝ…፡፡”
…የህይወት ውጣ ውረዷን፣ ፅናቷን፣
ስኬቶቿን በመጽሐፍ ለመፃፍ ስላነሳሳት
ምክንያት…
“…ሁለት ነገሮች ይሄን መጽሐፍ
እንድጽፍ አስገድደውኛል፤ አንደኛው
ብዙውን ጊዜ ከእኛ በፊት የተለያየ ታሪክ
የሠሩ ሰዎች የሠሩት ታሪክ፣ የገጠማቸው
የህይወት ውጣ ውረድና ፈተና፣ የስኬታቸው
ምስጢር፣ ልምድና ተሞከሮአቸውን
ሳናገኝ ከዚህ አለም ያለፉ በርካታ ታላላቅ
ባለሙያዎች አሉ፤ ይሄ በውስጤ ሁልጊዜ
ትልቅ ቁጭትን ይፈጥር ነበር፡፡ ምነው
የእነዚህ ሙያተኞችን የስኬት ታሪክ፣ ውጣ
ውረድ፣ ልምድና ዕውቀታቸው በመጽሐፍ
ተፅፎ ብናገኘው ኖሮ ብዙ እንማርበት ነበር
የሚለው ወደዚህ ነገር የገፋኝ አንደኛው
ምክንያት ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ብዙ
ጓደኞቼ፣ ጋዜጠኞች፣ ስፖርቱ ውስጥ ያሉና
ከስፖርቱ ውጪ ያሉ ሳይቀር የእኔን የህይወት
ዝቅታና ከፍታ ስነግራቸው “…እንዴ…!…
ይሄ እኮ… ትልቅ መፅሐፍ ይወጣዋል…
ለምን… በመጽሐፍ ደረጃ ተፅፎ…ብዙዎች
እንደማሩበት አታደርጊም… ብለው ይገፋፉኝ
ነበር…፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች ውስጤ ካለው
ታሪኬንና ውጣ ውረዶቼን፣ ፅናቴን ለሌሎች
የማካፈል ከፍተኛ ግፊት ጋር ተዳምረው…
የአሁኑን መጽሐፌን… እንድጽፍ… ምክንያት
ሆኖኛል…፡፡”
…በማሰልጠንና መጽሐፍ ጽፎ ለንባብ
በማብቃት መካከል ስላለው ድካምና ውጣ
ውረዶች…
“…ሁለቱን ማወዳደር ለእኔ በጣም ከባድ
ቢሆንም… መጽሐፍ መፃፍ… ከማሰልጠን
ብቻ ሳይሆን… ዋንጫ አንስቶ ከመሳም
በላይ… ለእኔ በጣም ከባድና ፈታኝ ብዙ ውጣ
ውረዶችን ያየሁበት ነበር…፡፡…ምናልባት
መጽሐፍ መፃፍ የመጀመሪያዬ ስለሆነና
አዘጋጅቼ ስለማላውቅና አዲስ ባህል ከመሆኑ
አንፃር ይሁን በሌላ አላውቅም… የገጠመኝ
ፈተና…በጣም ከባድና በበርካታ ውጣ ውረዶች
የተሞላ ነበር…፤…መጨረሻ ላይ… ፍሬው
ቢጣፍጥም…፡፡”
…የወንዶችን ቡድን በማሰልጠን
የመጀመሪያ የሆነችው መሠረት ይሄን
መጽሐፍ በመፃፍዋ የሌላ አዲስ ታሪክ
ባለቤት ስለመሆንዋ…
“…በዚህ ደረጃ… ከዚህ በፊት
የነበሩ ካሉ ብዬ ባፈላልግ…ማስረጃ
ማግኘት አልቻልኩም… የሚነግረኝም
ሰው አላገኘሁም…፤…ከዚህ አንፃር ካየነው
ከኢትዮጵያ ብቻ አይደለም…ከአፍሪካም…
የመጀመሪያ ያደርገኛል…፡፡”
…በፈተናዎችና በውጣ ውረዶች መብዛት
መጽሐፉን መፃፍ ለመተው፣ ለተስፋ መቁረጥ
እጅ ለመስጠት ስለተቃረበችበት አጋጣሚ…
“…ኧረ… በጣም ብዙ ጊዜ…
ከፈተናዎች… ከውጣ ውረዶች መብዛት…
የተነሣ… ከዚህ ሁሉ ለምን ባይፃፍ
አይቀርም…!…ለምን…እርግፍ አድርጌ…
አልተወውም…በማለት… ለተስፋ መቁረጥ
እጅ…ለመሰጠት በጣም ተቃርቤ ነበር…፤…
ግን…ይሄን መጥፎ ውሳኔ እንዳልወስን…
ምን ይይዝሃል…?…ውስጥህ የሚፈጠር
እልህ…እዚህ ደረጃ ደርሶ…እንዲህ ለፍቼ…
እንዴት እሸነፋለሁ…?…በፍፁም መሸነፍ…
ተስፋ መቁረጥ… የለብኝም…የፈለገ ይምጣ…
ቢከፋ…ቢከፋ…ያለኝን ንብረት ሸጬ…ይሄን
መጸሐፍ አሳትመዋለሁ…እንጂ አልተወውም
ብዬ…ከራሴ ጋር…እልህ ተጋብቼ…(Positive
energy)…ጥሩ ስሜት…ውስጤ ፈጥሬ…
የአይቻልም ስሜትን በዚህ መንገድ ራሴው
አሸንፌ… ለማሳተም በቃሁ እንጂ… አሁን
ራሱ ላስመርቅ 10 ወይ 15 ቀን ሲቀረኝ…
እንኳን ራሱ…ለተስፋ መቁረጥ…እጅ
ልሰጥ…በጣም ተቃርቤ ነበር…፡፡ እንደገና
አንስራርቼ…የፈለገ ይምጣ…ቢፈልግ…ለምን
አስር መጽሐፍ አይታተምም… ብዬ…
ገባሁበት…አምላክ ደግ ነው…መጨረሻው
ያማረ ሆነ…፡፡”
…በተፈጥሮ እልኸኛ መሆንዋ መጽሐፉ
እንዲወለድ ምክንያት ስለመሆኑ…
“…እኔ በጣም…እልኸኛ ብቻ ሣልሆን…
ፅናትም ያለኝ ሰው ነኝ…ብዬ አስባለሁ…፤
…በእግር ኳሱ ውስጥ…ብዙ ርቀት
የወሰደኝ…በውስጤ ያለው…ከፍተኛ የሆነ
የጠነከረ…ፅናትና…እልኸኝነቴ ነው…፡፡…
በስልጠና ህይወቴ ብዙ ተስፋ አስቆራጭ
ነገሮች…ከፊት እየተደቀኑ ቢያስቸግረኝም…
ለተስፋ መቁረጥ…በቀላሉ እጅ የምሰጥ
ሰው አልነበርኩም…፤…ከፈተናዎች
ከውጣ ውረዶች ብዛት…ይሄ ባይሆን…
ብዬ… መጀመሪያ አልሸነፍም…፡፡…
ምክንያቱም ህልም ስላለኝና…ህልሜን መኖር
ስለምወድ…፣…ነገ የሆነ ቦታ እንደምደርስ…
ስለማምን…የእግዚአብሔር ቸርነትም…፣…
የድንግል ማርያም አማላጅነትም… ከእኔ ጋር
ስላለ…ይሄ እልኸኝነቴና የጠነከረው ፅናቴ
ተጨምሮበት…ለዚህ አብቅቶኛል…፡፡”
…መጽሐፍ ስለሚያስተላልፈው ቁም
ነገርና ሌሎችን አስተምሮ ስለሚያልፈው…
“…ይሄ መጽሐፍ…በእኔ እምነት ብዙ ቁም
ነገሮችን ያስተላልፋል ብዬ አምናለሁ…፤…
በተለይ ደግሞ…ሴትነትና ጥንካሬን…
በዚህ መጽሐፍ ውስጥ በደንብ ታያለህ…፡
፡…ምን ያህል ፈተናዎችን…ተቋቁመን
ማለፍና…ለስኬት መብቃት እንደምንችል…
ፍንትው አድርጎ ያሳያል…ያስተምራል…፡፡
…ሴት ልጅ እድሉ ከተሰጣት…ውጤታማ
እንደሆነች…በተለያየ መስክ ብትሰማራም…
ኃላፊነቷን በብቃት ከመወጣት…የሚያግዳት
ነገር እንደሌለ ይጠቁማል…፡፡…ምክንያቱም…
የእኔ ህይወት በእግር ኳስ ላይ ብቻ ሣይሆን…
ከዚያም ውጪ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ላይ
ስለሠራሁኝ…እነዚያ ስራዎች ሁሉ ምስክር
ሆነው…ብዙዎችን ያስተምራሉ…ይለወጣሉ…
ያነሳሳሉ ብዬ አምናለሁ…፡፡”
…የመጽሐፉ ዋነኛ ትኩረት ወይም
ጭብጥ የመሠረትን ህይወትና ውጣ ውረድ
ፍንትው አድርጎ ስለማሳየቱ…
“…የእኔን ብቻ ሣይሆን በእኔ ውስጥ
የሌሎችን ሴቶች…ልፋት…፣…ድካም…፣…
ጥንካሬ…፣…ስኬት…እንዲሁም…የዚህን
ያህል ደክመው ለፍተው ግን የልፋታቸውን…
የድካማቸውን…ያህል…አለማግኘታቸው…
፣የሚያገኙት ዋጋ ትንሽ መሆን…፣….
ሚዲያው… ወይም ጥቂት ሰዎች…ከሚሰጡት
አድናቆት ማበረታታት በዘለለ…እንደ ታሪክ
ሰሪ…(legend)…አድርጎ አለመውሰድ…
ታሪክ ሰራን…ይዞ…አከብሮ…ሌላ ታሪክ
ሰሪ አለመፍጠር…እነዚህ ነገሮች…መጽሐፉ
ውስጥ በደንብ ይታያሉ…፡፡”
…መጽሐፉ በርካታ አቅም ያላቸው ታሪክ
የሠሩ ሴቶችን ከጓዳ የማውጣትና ተነሳሽነትን
ስለመፍጠሩ…
“…የዚህ መጽሐፍ ዋና አላማ…
የራሴን ገድል ለመዘርዘርና…እኔ እንደዚህ
ነኝ ለማለት አይደለም….፤…የመጽሐፉ ዋና
አላማም…አቅም እያላቸው…ትልቅ ታሪክ
ሰርተው…ጓዳ ውስጥ ተደብቀው ያሉ…
በየተሰማሩበት ሙያ ታሪክ መስራት የሚችሉ
ሰዎችን…አቅማቸውን እንዲያወጡ…ይሄም
ይችላል ለካ…?…ብለው እንዲያስቡ የሚያነሳሳ
ነው…፤…ትልቁ የመጽሐፉ ዓላማም ይሄው
ነው…፡፡
…መጽሐፉ ውስጥ ከተነሱት ነጥቦች
በጣም የተለየና አስገራሚ ስለምትለው
ገጠመኝ…
“…የተለያዩ ቁም ነገር ያላቸው ገጠመኞች
በውስጡ አሉ…፤…ከዚህ ውስጥ በጣም
የማልረሣውና እስከ አሁን ግጥምጥሞሹ
የሚገርመው…በ2002 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴት
ብ/ቡድንን ለማሰልጠን የቅጥር ማስታወቂያ
ይወጣል…፡፡…እኔም ለቦታው ፍላጎት
ያድርብኝና ዶክሜንቶቼን ለፌዴሬሽኑ
እልካለሁ…የቃል ፈተናና ቃለ መጠይቁ
ደግሞ ቅዳሜ ቀን ነበር የሚሰጠው…
ስለዚህ እኔ አርብ እለት ከድሬደዋ ለመነሣት
ፕሮግራም ይዣለሁ…፤…ከዚያ በፊት
እዚህ ድሬደዋ ሰርከስ ቡድን ላይ እየሰራሁ
ነበር፡፡ ቀን ስሰራ ጨጓራዬን በጣም
ያመኝና ለማስታገሻ እንዲሁም ጉዞ ላይ
ይበልጥ እንዳያመኝ መርፌ እወጋለሁ፤…ያ
የተወጋሁት መርፌ በጣም ያደክመኝና ልተኛ
ብዬ እቤቴ ገብቼ አረፍ እላለሁ፡፡ የዚያኑ
ቀን ምሽት ላይ ማለትም አርብ እለት
ወደ አዲስ አበባ ይዞኝ የሚበረው ሚኒ ባስ
ስለነበር… እኔን ለመውሰድ ሰዓቱ ሲቃረብ…
ስልክ ቢደውሉ… መኖሪያ ቤቴ መጥተው
ቢጣሩ “አቤት” የሚላቸው ሰው አላገኙም…
በዚህን ጊዜ “…አይ በቃ ሄዳ ነው…” በለው
ተስፋ ቆርጠው ይመለሳሉ፡፡ በዚህ መሃል
መሄዴ ነው ብዬ የተሰናበትኩት አንድ
ጓደኛዬ… የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ሆኖ
እቤቴ ይመጣል…በሩን ከፍቶ ድንገት ሲገባ
ተኝቼ ያገኘኛል…፤…በጣምም ይደነግጣል…
ምክንያቱም መጀመሪያ ተሰነባብተናል…
እሱም ሄዳለች ብሎ ነው የሚያስበው…፤…
በኋላ በድንጋጤ ውስጥ ሆኖ ይቀሰቅሰኝና “…
እንዴት አልሄድሽም…?…ምን ገጠመሽ…?”…
ብሎ ይጠይቃኛል… እኔም ድንግጥ ብዬ…
ወይኔ ሰዓቱ ሄዷል እንዴ…?…ወይኔ
ሚኒባሱ አመለጠኝ…በቃ ለነገው ፈተና
አልደርስም…ማለት ነው… እባክህ ሚኒባሱ
ጋ ደውልለት አልኩት…ሲደውልለት…እንደ
አጋጣሚ ለመውጣት እየተነሣ ነው “…
ቶሎ ካልመጣችሁ ጉዞ ልንጀምር ነው…”
አለን…፡፡…ዕቃችንን ሰብስበን በጥድፊያ ሄደን
ደረስንበት…ምሽቱን ስንጓዝ አድረን ቅዳሜ
ጠዋት ለቃል ፈተናውም ለቃለ መጠይቁ
ደረስኩ…በዚህ ውስጥ አልፌ ተፈተንኩ…፤…
በመጨረሻም ውጤቱ… ሀገርን የሚወክለው
የሴቶች ብ/ቡድንን በታሪክ ለመጀመሪያ
ጊዜ የማሰልጠን ትልቅ የታሪክ አጋጣሚን
ያገኘሁበት ይጠቀሳል…፡፡…ያ ለእኔ የስልጠና
ህይወት ትልቅ ታሪክ በመሆኑ ይሄ ገጠመኝ
አይረሳኝም፡፡ ከዚህ ውጪም የወንዶችን
ቡድን ሴት ሆኜ ሳሰለጥን አሜሪካ ሄጄ
የገጠሙኝና ሌሎች ገጠመኞች በመጽሐፉ
ውስጥ ተካተዋል፡፡
…መጽሐፉ ከህልምነት
ወደ እውነትነት እንዲቀየር ስለነበረው ድጋፍ…
“ ይ ሄ መጽሐፍ እውን እንዲሆን ብዙዎች
ተረባርበዋል…፣…በገንዘብ፣ በሃሣብ፣
ተስፋ እንዳልቆርጥና እንዳልሸነፍ [በርቺ
አይዞሽ] በሚል ማበረታቻ በኮሚቴነት ተዋቅረው
አብረውኝ ላይ ታች ብለው የደከሙ፣ መጽሐፉን
በ ማ ረ ም በመገምገም የተባበሩኝ ሰዎች አሉና እነሱ
የምስጋና ፀበሉ እንዲደረሳቸው እፈልጋሁ፡፡
በዚህ በኩል በተለይ ማመስገን የምፈልገው
የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር የቦርድ
ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አብነት ገ/መስቀልን
ነው፤አቶ አብነት መጽሐፉን እንዳሳትም
ላደረጉልኝ ድጋፍ የምስጋናውን ትልቁን
ድርሻ እንዲወስዱ እፈልጋለሁ፡፡ በመቀጠል
በጠየኳቸው ጊዜ [አይዞሽ ከጎንሽ ነን]
በማለት ድጋፋቸውን ያልነፈጉኝ የድሬዳዋ
ሲሚንት፣የድሬደዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣
የድሬደዋ ስፖርት ኮሚሽን፣ የድሬዳዋ ከተማ
ስፖርት ክለብ፣ የድሬዳዋ ከንቲባ ጽ/ቤትንና
አሁን ደግሞ የኢ.ፌ.ድ.ሪ ስፖርት ኮሚሽንን
በጣም ማመስገን እፈልጋሁ፤የኢ.ፌ.ድ.ሬ
ስፖርት ኮሚሽን መፅሐፌን ለመግዛት
ሁሉ ቃል በመግባታቸው ሳላመሰግናቸው
አላልፍም፡፡ ከዚህ ውጪ በኮሚቴነት
መጽሐፉን በመገምገም በማረም የተባበሩኝ
አቶ ዳንኤል የኋላሸት፣ አቶ የማነ ዘገየ፣
ከእኔ እኩል ስቃዩን ያየው ስንታየሁ
ታደሰ፣ ጋዜጠኛ ቆንጅት ተሾመ፣ ጋዜጠኛ
መንሱር አብዱልቀኒ እና መጽሐፉን ፅፎ
ለዚህ ያበቃው ዘርዓይ እያሱንና…የተባበሩኝ
ግን ሌሎች ያልጠቀስኳቸውን ለአጋርነታቸው
ለድጋፋቸው ለአይዞሽ ባይነታቸው ከልብ
አመሰግናለሁ…፡፡…ከእነዚህ ሌላ በአዲስ አበባ
ቆይታዬ ችግሮቼንም፣ብሶቶቼንም ተቋቁሜ
ተስፋ እንዳልቆርጥ፣እንዳልከፋ፣ ህልሜ
እንዳይጨናገፍ ከጎኔ በመሆን የረዳችኝ እንደ
እህቴ የማያትን እመቤት ጌታቸውንም በዚህ
አጋጣሚ ላመሰግናት እግዜር ይስጥልኝ ልላት
እወዳለሁ፡፡”
…ያልተጠበቀ ምላሽ ስለሰጡ፤ ሃሳቧን
ሊደግፉ ሲገባ ምላሻቸውን ስለነፈጉ አካላት…
“…ለምን እንደሆነ ባላውቅም ከማንም
በፊት ቀድሞ ይገኛል…፣..ያበረታታኛል፣…
ያግዘኛል፣…ይደግፈኛል ብዬ…ከፍተኛ
እምነት ለጣልኩበት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ
ፌዴሬሽን ጥያቄ አቅርቤ ሌሎች ሲረባረቡ
እስከአሁን ምላሽ አለመስጠቱ አስገርሞኛል፡
፡ ፕሬዚዳንቱንና ምክትል ፕሬዚዳንቱን
ሳይቀር በስልክ አነጋሬያቸው እስከአሁን
የሰጡኝ ምላሽ የለም፡፡ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
ለምን እንደዚህ እንደደረገ የማይፈታ
እንቆቅልሽ ሆኖብኛል…፡፡…ከማንም በፊት
ቀድሞ መገኘት ይገባው ነበር…፤…ከእግር
ኳስ ፌዴሬሽኑ ሌላ…ኦሎምፒክ ኮሜቴም…
ምላሻቸውን አልሰጡኝም…በግለሰብ ደረጃ ቃል
ገብተው…የተስፋ ዳቦ መግበውኝ መፅሐፉ
ውስጥ ሣይቀር…ስማቸው ገብቶ [ለህትመቱ
መሳካት ላደረጉት ድጋፍ] በሚል ምስጋና
ሁሉ ቀርቦላቸው ቃላቸውንም ያላከበሩ
የጠፉብኝ ሰዎች አሉ…ምናልባት ሥራ
በዝቶባቸው ሊሆን ይችላል ብዬ አምናለሁ
በዚህ አጋጣሚ ግን በቃላቸው መሠረት
ምላሻቸውን ቢሰጡ መልካም ነው…ቃልን
ማጠፍ ለማንም ጥሩ እንዳልሆነም ለማሳወቅ
ነው የምወደው…፡፡
…በምርቃቴ ግን ተገኝተው
የበኩር መጽሐፌን ቢመርቁልኝ ኖሮ ብላ
የምትቆጭበት…
“…በዚህ ቀን ተገኝታ የዚህ ታሪክ አካል…
የደስታዬም ተካፋይ ብትሆን… ሌላኛውን
የህይወቴን ስኬታማ ክፍል ብታይልኝ ኖሮ…
ደስታዬ ይበልጥ እጥፍ ይሆን ነበር… ብዬ
የምመኘው ወላጅ እናቴን ነበር…፡፡…ወላጅ
እናቴ መጽሐፉ ሲጠነሰስ ጀምሮ አብራኝ
ስትጨነቅ…ከህልም ወደ እውነትነት
እንዲቀየር በፀሎት ሁሉ አምላኳን ትማፀን…
መጽሐፌም ተመርቆ የማየት ትልቅ ጉጉት
ነበራት…ግን አልሆነም…የአምላክ ጥሪ
ነውና…ከዛሬ 10 ወር በፊት…በማይቀረው
ሞት ምክያት በመለየትዋ…በዚህ ልዩ ቀኔ
እሷ ባለመገኘትዋ በጣም ነው የተሰማኝ…፡
፡…ኖራልኝ…የልፋቷን…የጭንቀቷን ውጤት
ብታይ… ደስታዬን እኩል ብትጋራኝ…ይበልጥ
እደሰት ነበር…አልሆነም…፡፡ …በእናቴ
ባለመገኘት ባዝንም…ብዙዎች ግን እንደ
እናትም እንደ እህትና ወንድም የደስታዬ
አካል ለመሆን ቃል ገብተው ስለተገኙልኝ
ሃዘኔን አስረስተውኛል… አፅናንተውኛል…፡፡”
…መጽሐፍ መፃፍ ካለው ውጣ ውረድና
ፈተና አንፃር ይሄ መጽሐፍ የመጀመሪያ
ወይስ የመጨረሻ ለሚለው…
“…እንዳልኩህ ነው ወልዶ የመሳም
ያህል ከባድ ነው…፤…መጽሐፍ መፃፍ
በራሱ በፈተናዎች፣በውጣ ውረድ የተሞላ
ቢሆንም ጥሎት ከሚሄደው አሻራ
ከሰዎች እያየሁት ያለው አቀባበል በአንድ
እንዳልቆም… ሌሎች መጽሐፎችን እንድፅፍ
ጉልበት የሚሆን ነው፡፡ እንደዚህ አይነት
በውጣ ውረድ፣ በስኬትና በፈተና የተሞላ
ህይወትን የሚዳስስ
መጽሐፍ መፃፍ አለበት ብለው የሚያበረታቱ
ግለሰቦችና ተቋማት መኖራቸው ብዕርህ
ከወረቀት ጋር መገናኘቱ እንዳይቋረጥ የሚገፉ
በመሆናቸው ነገ እንደገና በመጽሐፍ ውስጥ
ያልተካተቱ እንዲሁም በተጨማሪ አዳዲስ
ስኬቶች ታጅቦ ከአሁኑ መጽሐፍ ትምህርት
ወስጄ እፅፋለሁ ብዬ ነው የማስበው…፡፡”
…አሜሪካን ሀገር በሴቶች ጉዳይ ተጋብዛ
ስለመሄድዋ…
“…በአሜሪካ በጣም ደስ የሚል ብዙ
ቁምነገር ያለው ትምህርትን ያኘሁበት
እድል ነበር…።…የአሜሪካ ኤምባሲ ሁልጊዜ
በተለያዩ ሀገራት ያሉ…የተሻለ ስራን
ሠርተው…ደካማ አመለካከቶችን ሰብረው
የወጡ…የተሻለ ታሪክ የሠሩ ሴቶችን
በኢንተርሽናል ቮሌንተርስ ሊደርሺፕ
እየጋበዘ… አሜሪካ ውስጥ ያለውን የሴቶች
ተሞክሮ የሚያስዳስስበት ፕሮግራም አለው፡
፡ በዚህ ፕሮግራም ላይ ከኢትዮጵያ እኔን
ጨምሮ ከአውሮፓ፣ ከኤዢያ፣ ከአፍሪካ፣
ከአውስትራሊያ የተውጣጡ 22 ታዋቂ ሴቶች
ጋር ነበር የተጋበዝኩት። 22 ታችንም ሴቶች
የተለያየ ተሞክሮና ስኬቶች ነበር የነበሩን…
እዚያ ላይ ልምዶቻችንንም ስኬቶቻችንንም
የተለዋወጥንበት ጥሩ የሚባል መድረክ ነበር፡
፡ ፖለቲካው፣ማህበራዊው፣ኢኮኖሚውም፣
የሴቶች ተሳትፎ፣ ጠንክረው ለስኬት
የመብቃታቸውን ምስጢር አሜሪካ ውስጥ
ካለና ጠንክረው ለስኬት የመብቃታቸውን
ምስጢር አሜሪካ ውስጥ ካሉና ከተለያዩ ሀገር
ከመጡ ሴቶች ሁሉን አቀፍ ልምድና ተሞክሮ
ወስጄያለሁ፤ በቂ እውቀት የገበየሁበት ትልቅ
ግብዣ ነበር ማለቱ ይቀለኛል…፡፡”
…ረዥም ጊዜ ከስልጠና ስለመራቅዋና…
ስለቀጣይ ዕቅድዋ…
“…እውነት ነው ከስልጠናው ርቄ
ቆይቻለሁ…፤…መጽሐፍ መፃፍ ምን እንደሆነ
ታውቁታላችሁ…በጣም ጊዜ…ትኩረት…
ልፋትና ድካምን አጥብቆ ይፈልጋል…፤…
በዚህ ምክንያት ለመጽሐፌ በቂ ጊዜ ለመስጠት
ስል ከስልጠናው ዞር ያልኩበት ሁኔታ ነው
የነበረው…፤…ይሄኛው አንደኛውና ዋነኛው
ምክንያቴ ቢሆንም…የተለያዩ ችግሮች ተፅዕኖ
ፈጥረውብኝ…ተስፋ መቁረጥ ባልልም
እንኳን…ስልጠናውን እንድጠላውና ጭራሽ
ስልጠና በቃኝ እንድል ጫና የፈጠሩብኝ
በርካታ ነገሮች ነበሩብኝ…፡፡ …ከሥልጠናው
ርቄ ለመቀመጥ እየዳዳሁኝ ነበር…፤…ነገር
ግን “…እንዴት..?…በፍፁም…ከስልጠናው
መራቅና ማቆም የለብሽም…ገና ከአንቺ
ብዙ ይጠበቃል…፤…ብዙ ውጣ ውረዶችን
አልፈሽ እዚህ የደረሽ ሰው ነሽና…ነገሮች
ቀላል ባይሆኑም…በእንደዚህ አይነት ነገር
ተሸንፈሽ እጅ ልትሰጪ አይገባም…”…የሚሉ
ጫናዎች ከየአቅጣጫው እየተፈጠሩብኝ ነው፡፡
በእነዚህን ሰዎች ሃሳብና ለእኔ ያላቸውን ነገር
የማከብር ቢሆንም በቀጣይ ወደ ስልጠናው
መመለስ አለመመለሴን በተመለከተ ከዚህ
መጽሐፍ ምርቃት በኋላ ከራሴ ጋር ቁጭ
ብዬ አውርቼ የምወስነው ነው የሚሆነው፡፡”
…ወደ ስልጠናው የምትመለስ ከሆነ
ወንዶችን…?…ወይስ…ሴቶችን…?…የትኞቹን
ስታሰለጥን ነው የምንመለከታት ስለመባሉ…
“…እንደነገርኩህ ነው…እስከአሁን
ሙሉ ትኩረቴም…ሁሉም ነገሬን የሰጠሁት
ለመፅሐፌ ነበር…እሱን ከእግዚአበሔር
እርዳታ ጋር በስኬት አጠናቅቄያለሁ ብዬ
አስባለሁ…በቀጣይ ወንዶችን…?…ወይም…
ሴቶችን…?…ላሰልጥን…የትኛውን ነው
ማድረግ ያለብኝ የሚለውን…እንዳልኩህ…
ከራሴ ጋር ተሟግቼ…አውጥቼ አውርጄ…
እቅዴን የማሳውቅ ነው የሚሆነው…፡፡”
የ“…ብርታት ተምሣሌት…” የሚለው
የግል ህይወቷ ላይ ያጠነጠነው መጽሐፍ
የበኩር መጽሐፍዋ ነውና እንደ መጀመሪያ
ልጇ ይቆጠራል ስለመባሉ…
“…የመጀመሪያ ልጅ ወልደህ ስትስም
የሚሠማህ ስሜት የለም…?…እኔም እንደዛ
አይነት ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ የመጀመሪያ
መጽሐፍ ሣይሆን የመጀመሪያ ልጄን ያገኘሁ
ያህል ነው የምቆጥረው፡፡ ከላይም ብዬሃለሁ
ልጅ አርግዞ፣አምጦ፣ወልዶ የመሳም ያህል ነው
ስሜቱ። የመጽሐፌ ለምርቃት መብቃትም
ተመሳሳይ ስሜት ነው በውስጤ የፈጠረው።
በዚህም በጣም ክብር ነው የተሰማኝ…፡፡”
….ለመጨረሻ ጊዜ የወንዶችን ቡደን
ያሰለጠንችው የድሬደዋ ከተማን ቡድንን
ነውና ከዚህ በኋላ ሃሳቧ ለውጣ የምትመለስ
ከሆነ መሠረት ወንዶችን ስታሰለጥን ትታይ
ይሆን በሚል ለቀረበው…
“…እሱም በቀጣይ የምወስነው ነው
የሚሆነው…እንደምታውቀው በሴቶች
የማመን ነገር አብዛኛዎቹ ጋ የለም…
ሴትነትህን ነው ቀድመው የሚለኩት…፤…
ውስጥህ ያለውን እምቅ ችሎታ… የተሰጠህን
ኃላፊነት ትወጣለህ…?…አትወጣም…?…
ወይም ከዚህ በፊት ምን ሠርታለች…?
የሚለውን ሣይሆን ሴትነትህን ብቻ
ስለሚመለከቱና በዚያ ስለሚለኩ ይሄ
የሙያው ትልቁ ፈተና ነው ማለት እችላለሁ፡
፡ በእንደዚህ አይነት የተሳሳተ አመለካከት
የተቃኙ አመራሮች እስካሉ እንዴት ይሄን
ስብረህ ኃላፊነቱን ትረከባለህ…? የሚለው
ከማሰልጠኑም…ውጤት ከማምጣቱም…
በላይ ትልቁ የሙያው ፈተና ሆኗል…፡፡…
እዚህ አይደለም ሌላም ቦታ የተሻለ ነገር
መስራት የምችልበት አቅም አለኝ…ብሎ
ውስጥህ የሚተማመነው የሚያውቀው
ነገር ብቻውን የትም አያደርስህም፡፡
መጀመሪያ ይሄ በጾታ የመለካት፣የመገደብ
አመለካከት ሙሉ በሙሉ መስበር አለበት፡፡
የአሰልጣኞች ስልጠና ሲሰጥ እኮ ለወንዶች
ለብቻ…ለሴቶች ለብቻ…ተብሎ የተቀመጠ
ነገር የለም፡፡ A ላይሰንስ ስንወስድ
ፕሪምየር ሊግም ብ/ቡድም ከሚያስለጥኑ
ወንድ አሰልጣኞች ጋር አብረን ነው
የወሰድነው፣ የተማርነው፣ የተፈተነው፡
፡ የተለየ ነገር የለም…፤ልዩነቱ ጾታ ብቻ
ነው…፡፡…ጾታ ብቻውን ደግሞ የአንዱን
አቅም ጠንካራነትና የአንደኛውን ደካማነት
አይጠቁምም…፤…ተፈጥሮአዊ ወይም
ባዮሎጂካል ከሆነው ውጩ፡፡ በጾታ ሳይሆን
በአቅም፣በእውቀት የሚለኩ የስፖርት
አመራሮች እስኪመጡ ድረስ…ይሄ ሰው
ሠራሽ ፈተናና መስናክል ይቀጥላል፡፡…
ግን እኔ ወንዶችን ላሰልጥን ወይስ ሴቶችን
…የሚለውን በቀጣይ የማሳውቅ ነው
የሚሆነው፡፡
…ህልመኛ ስለመሆንዋ…
“…እኔ ህልመና ነኝ፣…ሳልም
ደግሞ ትላልቅ…ከፍ ያሉ ህልሞችን ነው
የማልመው…፡፡ ….እስከአሁን ያኖረኝም…
ለስኬት ያበቃኝም ህልመኝነቴ ነው…፤…
ግን ህልም ማለም ብቻ ሣይሆን…
ህልሜንም የምኖር ሰው ነኝ…፡፡…ህልም
ባይኖረኝ ኖሮ ህልሜንም የማልኖር ሰው
ብሆን ኖሮ አሁን የምገኝበት ደረጃ
ላይ አልገኝም…ወድቄ እቀር ነበር…፡
፡…ምክንያቱም ሴትነቱ በራሱ ፈተና
ነው…፤…የሰዎች አዕምሮ…ባህሉ…
በራሱ ህልመኛ ባትሆን ኖሮ ከሌሎች
ነገሮች ቀድሞ ይጥልሃል፡፡ ከዚህ አንፃር
ህልመኛ መሆኔና ህልሜን መኖር…የሆነን
ነገር ዳር ማድረስ ስለምፈልግ ወድቆ
መነሳትን ጠንቅቄ ስለማውቅ ተሸንፌ
ማሸነፍ እንደምችል ስለማውቅና በዚህ
ቅኝት ውስጥ ስለማልም ነው መቆም
የቻልኩት…፡፡”
…ለዚህ ስኬት ስላበቃትና ስለ
ተምሣሌቷ…
“… አሁን ለምገኝበት ስኬት ያበቃኝ…
ከማንም በላይ የረዳኝ…የድንግል ማርያም
ልጅና ራስዋ ድንግል ማርያም ናቸው…
እንደዚህ አቅም፣ጉልብት፣እውቀት ሰጥቶ
ያከበረኝ እሱ ነው፡፡…ከዚህ ውጪ በሥራ
ህይወትህ በዙሪያህ ብዙ ሰዎች ይኖራሉ…
የእነሱም ድጋፍ የሚዘነጋ አይደለም፤…
አብዛኛውን መጽሐፉ ላይ ጠቅሻቸዋለሁ፡
፡…ከዚህ በተረፈ ግን እናቴ ለእኔ እንደ
ሞደሌ…የስኬታማነቴ ምስጢርና ዋነኛ
ተምሣሌቴ ናት…፡፡ …ምክንያቱም…
ከችግር እንዴት መውጣት…፣…ለችግሮች
እንዴት መፍትሔ መስጠት …፣…ገቢ
ሣይኖር ልጆችን እንዴት ማሳደግ…፣…
ፈተናን እንዴት መቋቋም…እንዴት ወድቆ
መነሣት እንደሚቻል… በወሬ ሳይሆን
በተግባር አሣይታኛለች…፡፡…ከዚህ አንፃር
እኔ የእሷ ስራ ውጤት በመሆኔ…ለእኔ
ከማንም በላይ ሞዴሌ (ተምሣሌቴ) ወላጅ
እናቴ ናት፡፡”
…በመጨረሻ…
“…እኔ አንድ እምነት አለኝ ብቻ
ሣይሆን… አንድ እውነት አለ…፤…
ሴቶች እድሉ ከተሰጣቸው በየትኛውም
መስክ ስኬታማ ናቸው…ስለዚህ የስራ
ገደብ አታድርጉባቸው…ማንኛውንም ስራ
መስራት ይችላሉ…፡፡…በጾታቸው ብቻ
አትለኳቸው…፤…ባላቸው አቅም ብቻ
“ትችላለች…?…አትችልም…” በሚል
ለኳቸው…።…ብዙ ቦታ እናያለን ወንዶች
“…ይችላል… አይቻልም…” ተብለው
አይለኩም…፤…ወንድ ስለሆኑ ብቻ…
ሁሉን እንደሚችሉ…ሴት…ስለሆነች
ግን…እንደማትችል ተደርጎ የማሰብ…
የተሳሳተ አመለካከት በብዛት አለ…፡፡…
ምንም ሣይችል ምንም ሣያውቅ ወንድ
ስለሆነ ብቻ ተመድቦ የሚሠራ አለ…፡
፡…ሴቷ እየቻለች ከወንዱ የተሻለች
ሆና ደግሞ በር የሚዘጋባት አለች…፡
፡…ስለዚህ እንደዚህ ባይሆን… ይሄ
አመለካከት ተሰብሮ… መመዘኛው ጾታ
ሣይሆን ችሎታቸው፣ እውቀታቸው
ቢሆን በጾታ መለካት ቢቀር መልካም
ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ከልጅነት እስከ
እውቀት እኔ ላይ አሻራቸውን ያሳረፉ…
ስሳሳት መክረው…ጥሩ ሰርተው…ከዚህ
ያደረሱኝን…ያበረታቱኝን ተመልካቾች…
የስፖርት ቤተሰቦችን…በሙሉ ከልብ
አመሰግናለሁ…አንተንም…የሀትሪክ ጋዜጣ
ዝግጅት ክፍልንም…ሁሌም ለሥራዬ
ዋጋ በመስጠት ለምታደርጉት ድጋፍና
ከህዝብ ጋር ድልድይ በመሆን እንድገናኝ
ለሰጣችሁኝ ዕድል ከልብ አመሰግናለሁ፡፡