በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ዲፓርትመንት ከተለያዩ ዩኒቭርስቲዎች ለተውጣጡ 33 የስፖርት ሳይንስ መምህራን ሲሰጥ የነበረው የእግር ኳስ አሰልጠኞች ስልጠና ከ7ቀናት የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በኋላ በዛሬው ዕለት ተጠናቀቀ፡፡
ይህ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አማካኝነት የተሰጠው የሀገር ውስጥ ኢንትራክተሮች ስልጠና አላማ ያደረገው በሚሄዱባቸው የሃገራችን ክፍሎች ለእግር ኳስ አሰልጣኞች ከክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን ስልጠናዎችን እንዲሰጡ ለማደረግ የታቀደ መሆኑን ኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቴክኒክ ዳይሬክተር ኢንስትራክተር መኮንን ኩሩ ገልጸውልናል፡፡
ዛሬ በነበረው የመዝጊያ ፕሮግራም የተገኙት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ባደረጉት ንግግር በቀጣይ በርካታ ስራዎች ከሰልጣኖቹ እንደሚጠበቅ የገለጹ ሲሆን፤ አክለውም የወደፊቱን የተሻለ ብሔራዊ ቡድን ለማግኘት ሁሉም ለሀገሩ የሚጠበቅበትን እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡
ስልጠናውን የተከታተሉት የዩኒቨርስቲ መምህራንም ይህን ሀላፊነት በሚገባ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ስለመወጣታቸው የቴክኒክ ዳይሮክተሬቱ ክትትል እንደሚያደርግ እና ግንኙነታቸውም በጠበቀ መልኩ እንደሚያስቀጥሉ ኢንሰትራክተር መኮንን ኩሩ ገልጸውልናል፡፡ በስተመጨረሻም ለሰልጣኞቹ የምስክር ወረቀት ተሰጧቸዋል፡፡
Via- Eff website