የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹን) የሚያሰለጥን አሰልጣኝ ለመመረጥ 7 የምርጫ መስፈርት በማዉጣት አሰልጣኛችን ለዉድድር መጋበዙ ይታወቃል ።
* አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ-ከአሜሪካ…
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወንዶቹን ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ የቅጥር ሁኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሰጠው መግለጫ ለ10 ቀናት መስፈርቱን እናሟላለን ያሉ የ25 አሰልጣኞችን ሲቪ መቀበሉን ይፋ አድርጓል።
ፌዴሬሽኑ እንዳለው ሲቪያቸውን ካስገቡት 25 አሰልጣኞች ውስጥ 13 እና ከዛ በላይ የውጪ ሀገር ዜግነት ያላቸው አሰልጣኞች መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።
- ማሰታውቂያ -
ብሔራዊ ቡድኑን ለማሰልጣን ሲቪያቸውን ካስገቡ የውጭ አሰልጣኞች መካከል የቀድሞ የዋሊያዎቹ አሰልጣኝ ቶም ሴንትፊት ጨምሮ ፣ የቀድሞ የቤኔፊካ ተጫዋች ቪቶል ሳልቫዶር ፣የቀድሞ የሆላንድ ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች ዶን ባልዶል እና ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ሀራጋርሲዮም ስማቸው በቀዳሚነት እየተጠቀሰ ነው።
ከአገር ውስጥ የአስልጣኝ ፀጋዪ ኪዳነማርያም እና የአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ስም እየተነሳ እንዳለ ለሀትሪክ ስፖርት ደህረ-ገፅ ቅርበት ያላቸው ምንጮጭ ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብ/ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ለሚሆነው አሰልጣኝ ዝቅተኛው 50 ሺህ ከፍተኛው 85 ሺህ ሊሆን እንደሚችል እየተነገረ ነው ።