በቅርብ ዓመታት በኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ላይ ከታዩት ተስፈኛ ወጣቶች ኣንዱ የሆነው ደስታ ደሙ በእግር ኳስ ህይወቱ እና ሌሎች ጉዳዮች ከ ሃትሪክ ስፖርት ድረ ገፅ ፀሃፊ ዳዊት ብርሃነ ጋር ያረገውን ቆይታ በዚህ መልክ ኣቅርበነዋል።
ሃትሪክ ስፖርት፡ የእግር ኳስ ህይወትህ ኣጀማመር እንዴት ይመስላል?
ደስታ ደሙ፡ የእግር ኳስ ህይወቴ ሚጀምረው ሰፈር ውስጥ ነው፤ተወልጄ ያደግኩት ወንጂ ባሌች ቦኩ ሚባል ኣካባቢ ነው እና የቀበሌ ውድድር ላይ እየተጫወትኩኝ ነው በሙገር መልማዮች ተመልምዬ ሙገር ሁለተኛ ቡድን ውስጥ መግባት የቻልኩት።ከሙገር ጋር ከመውረዱ በፊት ግማሽ ዓመት ፕሪመርሊግ እንዲሁም ከፍተኛ ሊግ ላይ ኣንድ ዓመት ተጫውቻለው።
ደደቢት የተቀላቀልኩት በ 2008 ከ 20 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በግርማ ሃብቴ ዮውሃንስ ተመርጬ በምጫወትበት ጊዜ የተመለከተኝ የደደቢት የግብ ጠባቂዎች ኣሰልጣኝ የነበረው ጸጋዝኣብ ጥቆማ ነው።
- ማሰታውቂያ -
ሃትሪክ ስፖርት: በደደቢት ላይ ያሳለፍካቸው ሁለት ዓመታት እንዴት ታያቸዋለህ?
ደስታ ደሙ: በደደቢት ያሳለፍኳቸው ሁለት ዓመታት በጣም ጥሩና ደስ የሚል ግዜ ነበሩ።መጀመርያ ኣካባቢ እንደገባው ትንሽ ከበድ ብሎኝ ነበር ማለት በተፈጥሮዬ ከሰው ጋር ቶሎ ስለማልቀራረብ ትንሽቨ ከብዶኝ ነበር።በመጀመርያ ዓመት ላይ ተጠባባቂም ሆኜ ኣሳልፍያለው ሁለተኛ ዓመት ላይ ከመጀመርያው ዓመት ብዙ ነገር ተምሬ ያሳብኩትን አሳክቻለሁ ።
ሃትሪክ ስፖርት፡ ባለፈው የውድድር ዓመት ኣጀማመራችሁ መልካም ነበር በኣንዴ ውጤት ማጣት የገባችሁበት ምክንያት ምንድን ነው ብለህ ታስባለህ?
ደስታ ደሙ፡ እንዳያችሁት በጣም ከሚገባው በላይ ጥሩ ነበርን ግን ሁለተኛው ዙር ላይ እንደ ቡድን ደከም ብለን ታይተናል፤የኛም ስህተት እንዳለ ሆኖ ከሜዳ ውጪ ስትጫወት ሚታዩት ችግሮችም ዉጤታችን ላይ ተጽእኖ ፈጥረዋል።እንደ ሰራነው ስራና እንደ ስብስቡ ኣቅም ዋንጫውን ማንሳት ነበረብን ያው ፈጣሪ ካልፈቀደ ምንም ነገር ኣይሆንም።
ሃትሪክ ስፖርት፡ ቀጣይ ዓመት ለወልዋሎ ዓ.ዪኒቨርሲቲ ለመጫወት ፈርመሃል እና ቡድኑን እንዴት ኣየሀው?
ደስታ ደሙ፡ ለወልዋሎ በመፈረሜ ደስተኛ ነኝ ቡድኑ ጥሩ ተጨዋቾች ያሉበት ነው እናም በህብረት ጠንክረን ከሰራን ጥሩ ነገር እናሳያለን ብዬ እገምታለው።
ሃትሪክ ስፖርት፡ እስካሁን ከገጠምካቸው አጥቂዎች ለመያዝ በጣም ያስቸገረህ?
ደስታ ደሙ፡ ሳቅ…..አገራችን ውስጥ ጥሩ ጥሩ ኣጥቂዎች ኣሉ ግን ይሄ ኣስቸግሮኛል ብዬ የማስበው ኣጥቂ ኣላጋጠመኝም።
ሃትሪክ ስፖርት፡ በ 2010 ውድድር ዓመት ከደደቢት ውጪ ለኣንተ የተመቸህ ቡድን?
ደስታ ደሙ፡ ለኔ አዳማ ተመችቶኛል ምክንያቱም በወጣቶች የተገነባና ጥሩ እግር ኳስ ሚጫወት እንዲሁም በሜዳው ጠንካራ ቡድን ነበር።
ሃትሪክ ስፖርት፡ በተጠናቀቀው የ2010 የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ለኣንተ ኮከብ ተጫዋች ማን ነው?
ደስታ ደሙ፡ ለኔ ሄኖክ ኣዱኛ ኮከብ ነበር ምክንያቱም ሄኖክ ታታሪ እንዲሁም በመከላከልም ማጥቃትም እኩል ተሳትፎ ሚያደርግ ከዚህም ባለፈ ከመስመር እየተነሳ ሚያሻማቸው ኳሶች ኣደገኛ ናቸው እንዲሁም ክለቡ ጅማ ኣባጅፋር ሻምፒዮን ስለሆነ ሽልማቱ ይገባዋል እላለው።
ሃትሪክ ስፖርት፡ በመጨረሻም የምታስተላልፈው መልዕክት ካለህ?
ደስታ ደሙ፡ ያው በ2010 ያየናቸው ጥሩ ነገሮች እንዳለ ሆኖ መጥፎ ነገሮችም ነበሩ እና እነኚህ መጥፎ ነገሮች ተቀርፈው 2011 ላይ ጥሩ ነገር እናያለን ብዬ ኣስባለው።
ሃትሪክ ስፖርት፡ ኣመሰግናለው
ደስታ ደሙ፡ ኣመሰግናለው