በቱርክ ቢኦቢ የሴቶች ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ከሜዳቸው ውጪ ኪርኮፕን የገጠመቱ ቢርኪርካራ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፋ።
በመጀመርያው ሳምንት ሃይበርኒያንስ 8ለ0 በማሸነፍ የጀመሩት ቢርኪርካራዎች አሁንም በተመሳሳይ ኪርኮፕን ላይ 7 ግቦችን በማስቆጠር አሸንፈዋል።በመጀመርያ ጨዋታዋ ሁለት ግቦችን ማስቆጠር የቻለቸው ሎዛ አበራ ትላንትናም ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የግብ መጠናን አራት አድርሳለች።ቀሪዎቹን ግቦች ቬሮኒክ ሚስፋድ፣አንማሪ ሰይድ፣ዩሊዬና ካርቦት፣ቲሬሲ ና ባሳለፍነው የውውድር ዓመት የክለቡ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዋ ኬይሊ ዊልስ አስቆጥረዋል።
በዚህም መሰረት የመጀመርያ ሁለት ጨዋታቸውን በአሸናፊነት ያጠናቀቁት ሻምፒዮኖቹ ቢርኪርካራዎች ሊጉን በስድስት ነጥብና በ14 ንፁህ ግቦች እየመሩ ይገኛሉ።