ሐዋሳ ከተማ ተጫዋች አስፈርሟል !
የቀድሞው ተጫዋቻቸውን ሙሉጌታ ምህረትን በአዲሴ ካሴ የተኩት ሐዋሳ ከተማዎች ጋናዊውን ጋብሬል አህመድ የግላቸው ማድረግ ችለዋል ።
የዘንድሮውን የውድድር ዓመት በአፄዎቹ ቤት በመጫወት ያሳለፈው ጋብሬል አህመድ ለቀጣይ አንድ ዓመት በድጋሚ ለቀድሞ ክለቡ ሐዋሳ ለመጫወት መስማማቱ ተገልጿል ።
ጋብሬል አህመድ በሊጉ ልምድ አላቸው ከሚባሉ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ግምባር ቀደሙ ሲሆን በደደቢት ፣ ሀዋሳ ከተማ ፣ ንግድ ባንክ ፣ መቐለ 70 እንደርታ እንዲሁም ፋሲል ከነማ በመጫወት ማሳለፉ የሚታወስ ነው ።