በ 29ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ ላይ የተካሄደው የመቐለ ና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታ በባለ ሜዳዎቹ መቐለ አሸናፊነት ተጠናቋል። መቐለዎች ሲዳማን ከገጠመው ቡድን ሃይሉ ገ/እየሱስን በ ዳዊት ዑቅባዝጊ ቀይረው ገብተዋል። ኤሌክትሪክም ፋሲልን ካሸነፈው ቡድን ጫላ ድሪባን በዘካሪያ ቱጂ ቀይረው ገብተዋል።
በማልያ መመሳሰል ምክንያት በተጀመረ በ ሁለተኛው ደቂቃ የተቋረጠው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከ 6 ደቂቃዎች በኃላ እንደገና ሊጀመር ችሏል።በ 3-5-2 አሰላለፍ ወደ ሜዳ የገቡት ኤሌክትሪኮች አንድ ነጥብ ይዘው ለመውጣት ከነበራቸው እቅድ አንፃር ከኋላ በ5 ተከላካዮች ሲከላከሉ ነበር። ይህ እንዲሆንም በሁለቱም መስመር እንደ ተመላላሽ ኣማካይ የተሰለፋት ዘካርያስ ቱጁ እና ዓወት ገ/ሚካኤል ወደ ኋላ በመሳብ ከኋላ ካሉት ሦስት ተከላካዮች ጋር በመጣመር የኋላ አምስት መስመርን ሲሰሩ ነበር። መቐለዎችም ይህን ጠጣር የኤሌክትሪክ የመከላከል አጥር ለማስከፈት ከ ጋቶችና ከእያሱ በሚነሱ ኳሶች ለማስከፈት ቢሞክሩም ይህ የሚባል ንፁ የግብ ዕድልን መፍጠር አልቻሉም። ለተመልካች ኣሰልቺ በነበረው የመጀመርያው አጋማሽ ብዙ ሙከራ ያልታየበት ነበር።
- ማሰታውቂያ -
ባለሜዳዎቹ መቐለ በፋሱይኒ እና በአማኑኤል የግብ ሙከራ ቢያደርጉም ሊሳካላቸው ኣልቻለም በተለይም በ46ኛው ደቂቃ በረጅሙ የተጣለውን ኳስ አማኑኤል ከተከላካዮቹ ሾልኮ በመውጣት ያገኘውን ወደ ግብ ቢመታውም ተከላካዩ ሲሴይ ሀሰን አውጥቶበታል ሙከራው ከተደረገ በኋላ ተቀያሪ ወንበር ላይ የተቀመጡት የኤሌክትሪክ ተጨዋቾች አማኑኤል ከጨዋታ ውጪ ነበር በሚል በፈጠሩት ሰጣ ገባ ተቀያሪ ወንበር ላይ የነበረው ተክሉ ተስፋይ ቀይ ካርድ ሊያገኝ ችሏል። የመጀመርያው አጋማሽ በመቐለ የኳስ በላይነት በኤሌትሪኮች መከላከል ታጅቦ ያለግብ ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ መቐለ አያሱን በያሬድ ብርሃኑ ቀይረው በማስገባት በቀኝ መስመር ለማጥቃት ሙከራ ሲያደርጉ ታይቷል ሆኖም እንደ መጀመርያው አጋማሽ በአምስት ተከላካይ መከላከልን የቀጠሉበት ኤሌክትሪክ የሚቀመሱ አልነበሩም። ኤሌክትሪኮችም ለማጥቃት የሚያድርጉት እንቅስቃሴ በቁጥር አንሰው በመገኘታቸው በቀላሉ በመቐለ ተከላካዮች ኳስ ሲነጠቁ ነበር አልፈው አልፈው በአጥቂያቸው በሃይሌ እሸቱ ያደረጉዋቸው ሙከራዎች በ ኦቮኖ ሲመለሱ ነበር። መቐለዎችም ተጭነው ለመጫወት ቢሞክሩም አሁንም በተመሳሳይ ንፁህ የጎል ዕድል ሊፈጥሩ አልቻሉም።
የመቐለ ከተማው አሰልጣኝ ዮሃንስ የመቐለን የማጥቃት ሃይል ለማስቀጠል አሸናፊን በዳዊት ቀይረው በማስገባት በሶስት ተከላካይ መከላከልን መርጠዋል። ጨዋታው ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ሰዓት ጋቶች ፓኖም በግምት ከ25 ሜትር አክርሮ የመታው ኳስ በኤሌክትሪክ መረብ ሊያርፍ ችሏል። ጨዋታውም በመቐለ አሸናፊነት ተጠናቋል። ውጤቱም ተከትል መቐለ ነጥቡን 49 በማድረስ ከመሪዎቹ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሦስት ነጥብ ማጥበብ ችለዋል። የወራጅ ስጋት ያንዣበበበት ኤሌክትሪክም 32 ነጥብ በመያዝ በ14ተኛ ደረጃ ተቀምጧል
የአሰልጣኞች አስተያየት፡
ዮሃንስ ሳህሌ— መቐለ ከተማ
“እስከ መጨረሻው ድረስ ዘግተው ነው የተጫወቱት ግን መጨረሻ ላይ አጨዋወታችንን ቀይረን ጎል አግብተን አሸንፈናል የሜዳችን የመጨረሻ ጨዋታ በመሆኑም ህዝቡን ለማስደሰት ነው የሞከርነው ተሳክቶልናል።”
ጋቶች ፓኖም
“ጨዋታው ከባድ ነበር እነሱ ለመከላከልና ኣንድ ነጥብ ለማግኘት ነው የገቡት ያው በመጨረሻ ላይ ጎል አግብተን ኣሸንፈናል።