ዛሬ በደስታ ኢንተርናሽናል ሆቴል በተካሄደው ጋዜጣዉ መግለጫ መቐለ ከተማ እና ገ/መድህን ሃይለ የሁለት ዓመት ውል ተፈራርመዋል።ከጅማ ጋር የኢትዮጵያ ፕሪመርሊግ ዋንጫን ያነሳው ገ/መድህን ወጣት ተጨዋቾች በማሳደግ ላይ ትኩረት ኣድርጎ እንደሚሰራና ቡድኑ ሚለይበት የጨዋታ ስልት ለመስራት እንደሚፈልግ ገልፅዋል።
በተመሳሳይ ቡድኑ በለቀቁት ተጨዋቾች ምትክ ተጨቾችን ማስፈረሙንና በገበያው ኣንድ ሁነኛ ኣጥቂ እያፈላለጉ መሆኑን ኣሰልጣኝ ገ/መድህን ሃይለ ገልፅዋል።እንደሚታወቀው እስካሁን መቐለ ከተማ ስምንት ተጨዋቾችን ሲያስፈርም ኣምስት ተጨዋቾች ክለቡን ለቀዋል።ኣምና ቡድኑ ላይ ቀዋሚ ተሰላፊ የነበሩት ጋይሳ ኣምፖንግ ቢስማርክ፣ፍቃዱ ደነቀ፣ፋሱይኒ ኑሁ እና ኣንተነህ ገ/ክርስቶስ ውላቸውን ካጠናቀቁ ተጨዋቾች መካከል ናቸው።