በመቐለ ከተማ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እያከናወኑ ሚገኙት ሻምፒዮኖቹ ናይጀርያዊው ላውረንስ ኤድዋርድ፣አቤል መብራህቱ እና ፍፁም ተክለማርያም አስፈርመዋል።
የተከላካይ መስመር ተጨዋች ለማስፈረም በእንቅስቃሴ ውስጥ የነበሩት መቐለ 70 እንደርታ በመጨረሻም ናይጀርያዊውን ላውረንስ ኤድዋርድን አስፈርመዋል።ከዚህ በፊት በኢራን ሊግ አልሲናትና ካርባያን ክለቦች ተጫውቷል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ብሄራዊ ሊግ ላይ ከትግራይ ውሀ ስራ ጋር ያሳለፈው አቤል መብራህቱ መቐለ 70 እንደርታን መቀላቀል ችሏል።ከዚህ በፊት ለስሑል ሽረ፣መቐለ 70 አንደርታ መጫወት የቻለው አቤል ከብዙ ዓመታት በኃላ ወደ ቀድሞ ክለቡ መመለስ ችሏል።
ላለፋት ሁለት ዓመታት ከዋናው ቡድን ጋር መደበኛ ልምምድ ሲያከናውን የነበረው ፍፁም በቀዋሚነት ክለቡን መቀላቀል ችሏል።በ2010 በዮውሃንስ ሳህለ አማካኝነት 2011 ላይ ከፈረሰው ሁለተኛ ቡድን ወደ ዋናው ቡድን ያደገው ፍፁም መቐለ 70 እንደርታ መሀል ሜዳ ላይ ያላቸውን የተጨዋች አማራጭ ሊያሰፋላቸው እንደሚችል ይገመታል።