ያሬድ ከበደ እና ዮናስ ገረመው በጉዳት ኦኪኪ አፎላቢ ደግሞ በቅጣት መቐለ 70 እደርታ ነገ የማይጠቀማቸው ተጫዋቾች መሆናቸው ታውቋል።
በ 12ኛ ሳምንት ጨዋታ ወደ ጅማ አቅንቶ ጅማ አባጅፋርን የሚገጥመው የሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ወሳኝ ተጫዋቾችን በነገው ጨዋታ የማይጠቀም ይሆናል። አጥቂው ያሬድ ከበደ ከስሁል ሽሬ ጋር በነበረው ጨዋታ 23 ኛው ደቂቃ ላይ በጉዳት ተቀይሮ መውጣቱ አይዘነጋም። ተጫዋቹ ከጉዳቱ ባለማገገሙ ለነገው ጨዋታ ሳይደርስ የቀረ ሲሆን። አማካዩ ዮናስ ገረመው ትላንት ልምምድ ላይ በመጎዳቱ ከነገው ጨዋታ ውጭ የሆነው ሌላኛው ተጫዋች ሲሆን። ከስሁል ሽሬ ጋር በነበረው ጨዋታ በሁለት ቀይ ካርድ ከሜዳ የተሰናበተው ናይጀሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በቅጣት የነገው ጨዋታ የሚያመልጠው ይሆናል።