ስሑል ሽረ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ምንተስኖት አሎን አስፈረመ።
ከሰንደይ ሮቲሚ ጋር የተለያዩት ስሑል ሽረዎች አምና በግብ ጠባቂ ላይ የታየባቸውን ክፍተት ለመፍታት የቀድሞ የባህርዳር ከተማ ና ፋሲል ከተማ ተጨዋች ምንተስኖት አሎን ምርጫቸው አድርገዋል።በያዝነው የተጨዋቾች መስኮት ዝውውር ካስፈረማቸው በርካታ ተጨዋቾች ጋር እየተለያዩ ሚገኙት መከላከያ ከምንተስኖት አሎም ጋር በስምምነት መለያየታቸው ተከትሎ የስሁል ሽረ የክረምቱ 9ኛ ፈራሚ ሆኖ ሊቀላቀል ችሏል።
በሽረ አንዳስላሰ በመከተም የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን እያካሄዱ ሚገኙት ስሑል ሽረዎች በሚቀጥሉት ቀናት ካምፓቸውን ወደ መቐለ በማዞር ዝግጅታቸውን ሚቀጥሉ ይሆናል።