(በይስሀቅ በላይ (ከለንደን ኦሎምፒክ ስታዲየም)
በመጨረሻም ሙክታር እድሪስ ወርቁን አጠለቀ፤በትራክ ላይ ለዓነግሶ የቆየው ሞ ፋራህ የትራኩን ዓለም በሽንፈት ተሰናበተ።ሞ ፋራህ በመጨረሻም የዩዜይን ቦልት ዕጣ ፈንታ ደረሰው።
ለዓመታት አልሸነፍ በማለት የኢትዮጵያዊያንን የትራክ ንጉስነት ነጥቆ የቆየው ሞ ፋራህ ጠፍቶ የቆየው የኢትዮጵያዊያን የቡድን ስራ ጎልቶ በታየበት ውድድር ሙክታር እድሪስ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳልያ ለሀገሩ አበረከተ።
ለተመዘገበው ውጤት የሁሉም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ተጋድሎ ከፍተኛ ቢሆንም በተለይ የዮሜፍ ቀጀልቻ ስራ ለተገኘው ውጤት ከፍተኛውን ድርሻ ይወስዳል።
ሙክታር እድሪስ ውድድሩን ካጠናቀቀ በኃላ ለሚዲያዎች እንደገለፀው በውጤቱ መደሰቱንና ትልቁን ሰው በሀገሩና በደጋፊው ማሸነፍ መቼም ደግሜ የማላገኘው ድል ነው ካለ በኃላ ከውድድሩ በፊት ከጋደኞቼ ጋር የተነጋገርነውን ነገር ተግባራዊ ማድረጋችን ነው አሸናፊ ያደረገንም ብላል። ሞ ፋራህ ቀደም ሲል ቶሎ ይወጣ ነበር አሁን ግን ሳይወጣ ሲቀር ይህቺ ሰውዪ በቃ አለቀላት የሚል ስሜት ተሰማኝ ያለው እድሪስ በተገኘው ድል የኢትዮጵያን ህዝብና የደገፉኝን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ብላል።የሙክታር እድሪስ ኦሎምፒክ ሰታዲየምን ያጣበቡትና ጀግናቸውን በድልና በክብር ለመሰናበት የመጡትን እንግሊዝያዊያን አንገት ሲያስደፋ ኢትዮጵያውያንና ተቀናቃኛችን የሆኑት ኬንያውያንን ሳይቀር አስፈንድቃል።ሞ ፋራህ የትራክ ሩጫን በሽንፈት ተሰናብተዋል፤ቀጣዩ የትራክ ንጉሥ ማን ይሆናል ጊዜ የሚመልሰው ጥያቄ ነው።
- ማሰታውቂያ -
ፎቶ-ሙክታር እድሪስ ከድሉ በኃላ..