የሊጉ መጨረሻ ደረጃን ይዘው ወልዋሎን የገጠሙት ሀድያ ሆሳእናዎች ቢስማርክ አፖንግ በመጀመርያው አጋማሽ ባስቆጠረው ግብ ታግዘው ወሳኝ ሥስት ነጥብ አሳክተዋል።
ባለሜዳዎቹ ወልዋሎዎች ባሳላፍነው ሳምንት ድሬዳዋን ካሸነፈው ስብስብ ጠዓመ ወልደኪሮስን በሰመረ ሀፍታይ ሲቀይሩ ሀድያዎች በበኩላቸው የዓመቱ የመጀመርያ ድልን ካስመዘገው ቀዋሚ 11 ሄኖክ አርፌጮ ና በኃይሉ ተሻገርን አስወጥተው ዓብዱልሰመድ ዓሊ ና ፍራኦል መንግስቱ አስገብተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ብዙ ሙከራዎችን ያላስተናገደው የመጀመርያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድኖች ሳቢ ጨዋታ ያልታየበት ነበር።ሆኖም በአንፃሩ የተሻለ እንቅስቃሴ የነበራቸው ሀድያዎች በ15ኛው ደቂቃ በቢስማርክ አፖንግ አማካኝነት ባስቆጠሩት ግብ ባልታሰበ ሁኔታ መሪ መሆን ችለዋል።በፍፁም ቅጣት ሳጥን በቀኝ በኩል ሱራፋኤል ዳንኤል የመታው ኳስ የግቡ ቀዋሚ ብረት ሲመልሰው ቅርብ የነበረው ቢስማርክ አፖንግ በቀላሉ አስቆጥሮታል።ወልዋሎዎች አቻ ሚያደርገውን ግብ ለማግኘት ረጃጅም ኳሶች ላይ ትኩረት ቢያድርጉም በሀድያ ሆሳእና ተከላካዮች ተመልሶባቸዋል።
ከመጀመርያው አጋማሽ በተሻለ መልኩ ብዙ ሙከራዎችን ያስተናገደው ሁለተኛው አጋማሽ የቢጫ ለባሾቹ የሙከራ በላይነት የታየበት ነበር።ወልዋሎ ከመስመርና ከቆሙ ኳሶች በሳሙኤል ዮውሀንስ፣ሰመረ ሀፍታይና፣ጁንያንስ ናጋንጂቡ ና ራምኬል ሎክ አማካኝነት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎችን ቢያደርጉም በኦቤር ኦቮኖ ድንቅ ብቃት ግብ ሳይሆኑ ቀርተዋል።
ሁለተኛው አጋማሽ ላይ ጥንቃቄ መሰረት አድርገው ያገቡትን ግብ ለማስጠበቅ የተጫወቱት ሀድያዎች እቅዳቸው ተሳክቶ የውድድር ዓመቱ የመጀመርያ የሜዳ ውጭ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሀድያ ሆሳእናዎች ነጥባቸውን ወደ ስምንት ከፍ በማድረግ ከነበሩበት 16ተኛ ደረጃ ሁለት ወደ ላይ ከፍ ሲሉ፤ወልዋሎዎች በበኩላቸው የሊጉ መሪነታቸውን ለተቀናቃኛቸው መቐለ 70 እንደርታ አስረክበዋል።