በፍጹም ሀይሌ
ባሳለፍነው ሰኞና አርብ በቀሪ ተስተካካይ ጨዋታዎች የጀመረው የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ዛሬም ሲቀጥል በሀዋሳ ሰው ሰራሽ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሀዋሳዎች ከጨዋታ ብልጫ ጋር ፋሲል ከተማን 3-0 በሆነ ውጤት መርታት ችሏል።
ቁጥራቸው በርከት ያሉ የእንግዳው ቡድን ደጋፊዎችም መታደም ችለዋል። ወደ ጨዋታው እንቅስቃሴ ስንመለስ ሀዋሳ ከተማዎች ያለፉትን ሁለት ጨዋታዎች ነጥቦችን መጣላቸውን ተከትሎ የዛሬውን ጨዋታ ለማሸነፍ ከመጀመሪያው የዳኛው ፊሺካ ከተሰማ ጀምሮ በተደጋጋሚ የፋሲልን በር መፈተሽ ችለዋል። በ15’ደቂቃ ላይ እስራኤል እሸቱ ጥሩ የግብ እድል አግኝቶ ሳይጠቀም ሲቀር በ28ኛ ደቂቃ ላይ እስራኤል እሸቱ በጥሩ ሁኔታ ያሻማውን ኴስ ፍቅረየሱስ ተ/ብርሀን በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት የወጣበት ኳስ ሀዋሳን ቀዳሚ ማድረግ ሚችልበት አጋጣሚ ነበር።
ሃዋሳዎች በተደጋጋሚ ወደ ግብ ቢደርሱም የፋሲልን ግብ መድፈር አልቻሉም።
በ34 ደቂቃ ላይ ታፈሰ ግብ ቢያስቆጥርም ከጨዋታ ውጭ ተብሏል ። ፋሲሎች አቻ ለመውጣት እየወደቁ ሰዓት ሲያባክኑ ታይተዋል ። ሃዋሳ በፍሬው ሰለሞን በታፈሰ ሰለሞን እንዲሁም። በእስራኤል አማካኝነት የግብ ሙከራ ቢያደርጉም ግብ ማስቆጠር አልቻሉም። 59’ፋሲል ያለቀለት የግብ እድል መጠቀም አልቻሉም 61 ‘ሃዋሳዎች ያገኙትን ቅጣት ምት በ26 ቁጥሩ ያቡን ዊሊያም አማካኝነት በጭንቅላት በመግጨት ቀዳሚ መሆን ችለዋል። ሃዋሳ ወዲያው ሌላ አጋጣሚ ቢያገኝም እስራኤል አምክኗል በዚች ኳስ ምክንያት እስራኤል ጉዳት አጋጥሞት ወጥቶ ዳዊት ፍቃዱ ቀይሮ ገብቷል። 70ኛ ደቂቃ ላይ ፋሲሎች ጥሩ አጋጣሚ አግኝተው ሳይጠቀሙበት ቀርተዋል። 71 አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ፍሊፕ ዳውዝን በማስገባት የማጥቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ ቢምክሩም ሃዋሳዎች ፍፁም የበላይነት ጨዋታውን መግታት አልቻሉም ነበር። ተቆጣጥረውታል 72’ፍሬው ሰለሞን ከበረኛው ጋር ተገናኝቶ የነበረ ቢሆንም የፋሲል ተከላካይ እንደምንም ደርሶ አድናል ፋሲል ጨዋታው በጣም ከብዳቸው ታይተዋል በተቃራኒው አዋሳዎች በጥሩ ቅብብል በመጫወት ደጋፊዎቻቸውን ሲያስደስቱ ነበር በተለይ ሙሉ አለም ረጋሳ ሲያሳይ የነበረው ብቃት በሜዳ ከነበሩት ደጋፊዎች አድናቆት ተችሮታል 78’ኛ ደቂቃ ላይ ከግራ መስመር አምበሉ ደስታ ዮሃንስ ያሻማው ኳስ የፋሲል መረብ ለይ አርፋለች።
- ማሰታውቂያ -
ሃዋሳዎችም 2ተኛ ግብ አስቆጥረው መምራት ችለዋል። የጨዋታው 90′ ደቂቃ አልቆ 4ተኛ ዳኛ የባከነ 4 ደቂቃ አሳይተው የባከነውም አልቆ የዳኛ ፊሽካ በሚጠበቅበት ሰዓት ላይ አዲስ አለም ተስፋዬ ወደ ግብ የላካት ኳስ ግብ መሆን ብትችልም ዳኛው የመጠናቀቂያ ፊሻካ ባሰሙበት ቅጽበት በመሆኑ ሳያፀድቋት ቀርታለች ። ኳስዋ የተቆጠረችበት መንገድ የኢትዮጵያ እና የሱዳን ብሔራዊ ቡድኖች በአዲስ አበባ ስቴዲየም ባደረጉት ጨዋታ አዲስ ህንፃ ላይ እንደተቆጠረችው አይነት ነበረች አብዛኛው ደጋፊ ጎሉ እንደተቆጠረ ደስታውን ሲገልፅ ታይቷል። ጨዋታውም በሀዋሳ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል።