በ14ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መቐለ ከተማ ኢትዮ-ኤሌክትሪክን 2ለ1 አሸንፏል።
ጥሩ የጨዋታ እንቅስቃሴ በተስተዋለበት የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ወደ ጎል በመድረሱ ረገድ እንግዳዎቹ መቐለ ከተማዎች የተሻሉ ነበሩ።
በ31ኛው ደቂቃ የኢትዮ-ኤሌክትሪኩ ግብ ጠባቂ ዮሃንስ በዛብህ በመቐለ ከተማው ተጫዋች ቢስማርክ ጋይስ ላይ በሰራው ጥፋት በተገኘው ፍጹም ቅጣት ምት አማኑኤል ገብረሚካኤል ከመረብ በማሳረፍ መቐለ ከተማን መሪ አድርጓል።
ከገቧ መቆጠር በኀላ ኤሌክትሪኮች በመልሶ ማጥቃት ተደጋጋሚ ሞከራ ሲያደርጉ በ37ኛው ደቂቃ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ያገኙትን አጋጣሚ ተክሉ ተስፋዬ ከመረብ ላይ በማሳረፍ ቡድኑን አቻ ማድረግ ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
በመጀመሪያ አጋማሽ መቐለ ከተማዎች የተሻለ የግብ እድል በመፍጠር ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደጉ ተስተውሏል።በዚሁ ወደ 1-1 ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል።
በሁለተኛው አጋማሽ ኢትዮ-ኤሌክትሪኮች የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በአንጻሩ መቐለ ከተማዎች በማፈግፈግ በመልሶ ማጥቃት ግብ ለማስቆጠር ጥረት ሲያደር ቆይቶ በ85 ኛው ደቂቃ ላይ አማኑኤል ገብረሚካኤል ሁለተኛውን ጎል በማስቆጠር መቐለ ከተማን አሸናፊ ማድረግ ችሏል።
በዚህም የመቐለ ከተማዎ የፊት መስመር አጥቂ አማኑኤል ገ/ሚካኤል በከፍተኛ ግል አስቆጣሪ ደረጃ ከደደቢቱ አቤል ያለው ና ከኢትዮጵያ ቡናው ሳሙኤል ሳኑሚ ጋር በ5ግቦች መስተካከል ችሏል።
በውጤቱ መሰረት መቐለ ከተማ ደረጃውን ወደ ሁለተኛ ከፍ ሲያደርግ በአንጻሩ ኢትዮ-ኤሌክትሪክ በ16ኛ ደረጃ የፕሪሚየር ሊጉ ሰንጠረዥ ግርጌ ላይ ለመቀመጥ ተገዷል ።
የአስልጣኞች አስተያየት
ም/አሰልጣኝ ቅጣው ሙሉ -ኢትዮ-ኤሌክትሪክ
“በጨዋታው ሁለታችንም ጥሩ ተንቀሳቅሰናል።ያገኘናቸውን የግብ እድሎች አለመጠቀማችን በመጨረሻ ደቂቃ በተቆጠረብን ግብ ተሸንፈን እንድንወጣ አድርጎናል። በቀጣይ ጨዋታዎች ወደ አሸናፊነት እንመለሳለን።”
አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ~ መቐለ ከተማ
“ቡድኑን በዋናነት ስረከብ በሊጉ እንዳቆይላቸው ነው የጠየቁኝ ይህንንም ለማሳካት ነው እምንጫወተው ልጆቹም የተሰጣቸውን ስራ ባግባቡ እየተወጡ ነው። በዛሬው ጨዋታ እንድናሸነፍ የደጋፊዎቻችን ድጋፍ እንደሁለግዜው እረድቶናል። ”
ደረጃ ሰንጠረዥ
[team_standings id=”6559″ title=”” number=”16″ columns=”p,gd,pts” show_team_logo=”1″ show_full_table_link=”1″ align=”right”]