በ23ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳው ትግራይ ስታድየም ስሑል ሽረን ያስተናገደው መቐለ 70 እንደርታ ሥስት ለ እንድ በማሸነፍ ከተከታዩ ፋሲል ከነማ ጋር ያለውን የ 5 ነጥብ ልዩነት ማስጠበቅ ችሏል።ባሳለፍነው ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስን ከገጠመው ቡድን አንድ ቅያሪ ማለትም ተከላካዩን እንተነህ ገብረክርስቶስን በያሬድ ሃሰን ሲቀይሩ ስሑል ሽረዎች በበኩላቸው ሃዋሳ ከተማን ካሸነፈው ስብስብ ቅያሪ ሳያደርጉ ወደ ሜዳ ገብተዋል።
ጥሩ ፋክክር እና ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ያስተናገደው የመጀመርያ እጋማሽ የጨዋታው የመጀመርያ ጎልን ለማስተናገድ ሥስት ደቂቃዎችን ብቻ ፈጅቷል።ከቀኝ መስመር ሚኪኤለ ደስታ ያሻማው ኳስ አማኑኤል እና ግብ ጠባቂው ተሻምተውት ሁለቱንም ነክቶ የመጣውን ኳስ ከጎሉ ቅርብ የነበረው ያሬድ ከበደ እስቆጥሮ መቐለን መሪ ማድረግ ችሏል።ከመጀመርያው ግብ መቆጠር 4 ደቂቃ በኃላ ሳሊሳ ፎፎና ከቢስማርክ እፒያ የተላከለትን ያለቀ ኳስ ቢመታውም ፊሊፕ ኦቮኖ ሊያድንበት ችሏል።በ4-4-2 ዳይመንድ እሰላለፍ ፊት ላይ ኦሰይ ማውሊን ከአማኑኤል ገብረሚካኤል ያጣመረው የመቐለ 70 እንደርታ እሰላለፍ ማጥቃቱን አጠናክሮ ቀጥሏል በዚህም በ10ኛው ደቂቃ እማኑኤል ገብረሚካኤል ፍፁም ቅጣት ሳጥን ላይ በዲሜጥሮስ ወልደሥላሴ ጥፋት ተስርቶበት የተገኘችውን ፍፁም ቅጣት ምት ራሱ እማኑኤል ቢመታውም ሰንደይ ሮቲሚ እድኖበታል።ከፍፁም ቅጣት ምቱ መሳት 9 ደቂቃዎች በኃላ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጭ ወደ ቀኝ በኩል ከያሬድ ከበደ ያገኘውን ኳስ እማኑኤል ገብረሚካኤል እክርሮ የመታው እስደናቂ ኳስ ሰንደይ ሮቲሚን አልፋ የስሑል ሽረ መርበብ ላይ እርፋ የመቐለን ጎል ወደ ሁለት ከፍ አድርጋለች።ሁለተኛው ግብ ከተቆጠረ በኃላ ወደ ጨዋታው በተሻለ መልኩ መግባት የጀመሩት ስሑል ሽረዎች ጨዋታውን የተሻለ መቆጣጠር ችለዋል።በተለይም መሃል ላይ የተሰለፋት ሃብታሙ ሸዋለም እና እሳሪ እልማህዲ የቡድኑን ቅርጽ በመጠበቅም ኳሶች ወደ መስመር እንዲወጡና እድሎች እንዲፈጠሩ ሲያደርጉ ነበር።የዚህም ውጤት በ29ኛው ደቂቃ ቢስማርክ እፒያ ከአብዱሰላም እማን ከቀኝ መስመር የተሻገረለትን ኳስ በጥሩ እጨራረስ ስሑል ሽረን ወደ ጨዋታው መመለስ ችሏል።ከዚህ በኃላ በሁለቱም ቡድኖች በኩል ተመጣጣኝ ሚባል ጨዋታን እሳይተዋል፤ስሑል ሽረ በሃብታሙ ሸዋለም እማካኝነት መቐለዎችም በእማኑኤል ሙከራዎችን እድርገዋል።
ከመጀመርያው እጋማሽ እንፃር ቀዝቀዝ ያለ ጨዋታ የታየበት ሁለተኛው እጋማሽ በተቆራረጡ ቅብብሎሽ የታጀበ ነበር።ስሑል ሽረዎች በመጀመርያ 45 ያሳዩትን ቅርጽ ያለው እና መስመር ላይ ትኩረት ያደረገ እጨዋወታቸው ሁለተኛው እጋማሽ ላይ በብዛት ባይታይም ቢስማርክ እፖንግ ከቀኝ መስመር ወደ ውስጥ ሰብሮ በመግባት ያደረገው ሙከራ ፊሊፕ ኦቮኖ ያዳነበት እንዲሁም በተደጋጋሚ ከቆሙ ኳሶች እድሎችን ቢፈጥሩም የቆሙ ኳሶች ላይ የነበራቸው ደካማ እጠቃቀም ግቦችን እንዳያገኙ እድርጓቸዋል።ምዓም እናብስቶችም በሁለተኛው እጋማሽ ተቀዛቅዘው ቢታዩም እልፎ እልፎ ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል፤ ሁለተኛው እጋማሽ መጀመርያ ላይ ኦሰይ ማውሊ ከቀኝ መስመር ያሻማውን ኳስ ሃይደር ሸረፋ በግምባሩ ቢመታውም ከግቡ ጎን ወጥቷል በተመሳሳይ ሚኪኤለ ደስታ ከፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ውጭ መሬት ለመሬት የመታው ኳስ ሰንደይ ሮቲሚ አድኖበታል።ጨዋታው ሊጠናቀቅ በተቃረበበት ሰዓት ከመሃል ሜዳ በጅብሪል መሃመድና በሚኪኤለ ደስታ ጥሩ ቅብብል የመጣውን ኳስ ኦሰይ ማውሊ በግምት ከ20 ሜትር አክርሮ በመምታት የመቐለን እሸናፊነት ያረጋገጠች ግብ ማስቆጠር ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
ውጤቱን ተከትሎ የገብረመድህን ሃይለ ስብስብ መቐለ 70 እንደርታ ነጥቡን 48 በማድረስ ከተከታዩ ፋሲል ጋር ያለውን ነጥብ ልዩነት በ5 ነጥብ ማስቀጠል ችሏል።