በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 4ተኛ ሳምንት ሲዳማ ቡና ቅ/ጊዮርጊስን በሜዳው አስተናግዶ 1 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
የሁለቱም ክለቦች ደጋፊወች በሜዳ ላይ ያሳዩት አደጋገፍ እጅግ ማራኪ ነበር በተለይ የሲዳማ ደጋፊዎች በስቴዲየሙ ዘረኝነት ከእግር ኳሱ እንዲጠፋ በምስል የተደገፉ መፈክሮችን በስቴዲየሙ ይዘው ገብተዋል
ጨዋታው እንደ ተጀመረ ሲዳማ ቡና በፍፁም ተፈሪ አማካኝነት ሙከራን አድርገዋል ቅዱስ ጊዮርጊስም በአብዱል ከሪም ኒኪማ አማካኝነት ሙከራን ሲያደርጉ በተለይ አብዱልከሪም ኒኪማ ሰቶት አሜ መሀመድ የመታት እና ግብ ጠባቂው ያዳነበት ተጠቃሽ እድል ነበረች፡፡
- ማሰታውቂያ -
የሲዳማው የመስመር ተመላላሽ አብዱለጢፍ በሚያደርገው ፈጣን እንቅስቃሴ እና ጥሩ ኳሶቹ እንደሱ ጥረት ቢሆን ሲዳማ ቡና በርካታ ግብ ማስቆጠረ በቻሉ ነበር፡፡አብዱለጢፍ መሀመድ አቀብሎት ኬኔዲ አሽሊ ከሮበርት ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ የሳታት አሰቆጪ እድል ነበረች፡፡
የሲዳማው የመሀል አማካይ ፍፁም ተፈሪ(ፈቹ) የሚያደርጋቸው በርካታ አጋጣሚዎች እና ሙከራዎች እጅግ መልካም አጋጣሚዎች ነበሩ ፡፡ በ32 ደቂቃ ላይ በረጅሙ ወደ ሲዳማ ቡና የግብ ክልል የመጣችን ኳስ የሲዳማ ቡናው ግብ ጠባቂ መሳይ አያና ሲወጣ ሙጃይድ መሀመድ በራሱ ግብ አስቆጥሮ ቅ/ጊዮርጊስን መሪ አደረገ፡፡
ጨዋታው በፈረሰኞቹ መሪነት ሲቀጥል ምንተሰኖት አዳነ ወደ ግብ ውስጥ የመታት ኳስ ሲዳማዎች ራሳቸው ላይ ተጨማሪ ግብ አሁንም ሊያስቆጥሩ ሙከራ አድርገዋል፡፡ ተመሳሳይ የጨዋታ ቅርፅ የነበረው አንደኛው አጋማሽም በፈረሰኞቹ መሪነት ተጠናቋል፡፡
እጅግ ሲዳማ ቡና ተሻሽሎ በቀረበበት እና የበላይ በሆነበት ሁለተኛው አጋማሽ በተቃራኒው ፈረሰኞቹ ተቀዛቅዘው የታዩበት ነበር፡፡ በእለቱ ድንቅ ሆኖ የዋለው ፍፁም ተፈሪ የሚያደርገው አስገራሚ እንቅስቃሴ እንዲሁም በራሱ ላይ ግብ ያስቆጠረው ወጣቱ ሙጃይድ መሀመድ ለሲዳማ በአማካይ ስፍራ በተከላካይ ስፍራ ላይ ልዮነት ፈጣሪዎች ሆነዋል :: በ49ኛ ደቂቃ ላይ ፍፁም ተፈሪ ወደ ግብ የመታትን ኳስ ስትመለስ ኬኔዲ አሽሊ አጊንቶ የመሞከራት የፈረሰኞቹ ግብ ጠባቂ ሮበርት ኡዱንካራ በድንቅ ሁኔታ አድኖበታል፡፡ ሲዳማዎች በተደጋጋሚ ጎል ለማግኘት እና አቻ ለመሆን ተጭነው በመጫወት በተመልካቹ አድናቆት ተችሯቸዋል ፡፡አብዱለጢፍ መሀመድ ያቀበለውን የሊጉ ቀዳሚው ተከፋይ ኬኔዲ አሽሊ ኳሷን ሳያገኛት የቀረችው ኳስ እምታስቆጭ አጋጣሚ ነበረች፡፡
ባዬ ገዛኸኝ ከሮበርት ጋር ፊት ለፊት ተገናኝቶ የሳታት ተጠቃሽ ነበረች፡፡ ሲዳማ ቡናዎች ግብ ለማስቆጠር የባዬን ታናሽ ወንድም ሀብታሙ ገዛኸኝ እና አዲስአለም ደበበን ካስገቡ በኃላ እጅግ ተጨማሪ አማራጮችን እንዲያገኙና ጫና እንዲፈጥሩ አድርጓቸው ተስተውሏል ፡፡
በተለይም ፍፁም ተፈሪ ከሀብታሙ ገዛኸኝ ጋር ተቀባብሎ የመታትን የቅዱስ ጊዮርጊስ ተከላካይ ሳላሀዲን ባርጌቾ በድንቅ ሁኔታ አውጥቶበታል፡፡ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 10 ደቂቃዎች ገደማ ላይ ሲዳማ ቡናዎች ያገኞዋትን ቅጣት ምት ሀብታሙ ሲያሻማ ሚካኤል አናን በግንባሩ ገጭቶ የግቡ ቋሚ ያወጣበት ኳስ እድለኛ ላልነበሩት ሲዳማ ቡናዎች አስቆጪ ነበረች::
ውጤቱን ለማስጠበቅ ፈረሰኞቹ በመከላከል ሲዳማ ቡና ግብ ለማስቆጠር ጫና ቢፈጥሩም ቅዱስ ጊዮርጊስ በማብቂያው ሰአት ላይ በሀይሉ አሰፋ ግልፅ የግብ እድል አግኘቶ ከማዕዘን አካባቢ የሳታት እንዲሁም አሜ ግልፅ ጎል ሊሆን የሚችልን እድል አልተጠቀመበትም:: ሀብታሙ ገዛኸኝ ግልፅ አጋጣሚን አግኝቶም ሳይጠቀምበት ቀርቷል ፡፡ በዚሁ ጨዋታው 1-0 በሆነ ውጤት ፈረሰኞቹ ወሳኝ ሶስት ነጥብ ከይርጋለም ይዘው መመለስ ችለዋል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
አለማየሁ አባይነህ-ሲዳማ ቡና
“ይህ እግር ኳስ ነው እግር ኳስን ተወዳጅ ያደረገውም ይህ ነው እኛ ተጫወትን እኛ እራሳችን ላይም አገባን ሲዳማ ቡና ከሲዳማ ቡና ጋር ተጫወተ ሲዳማ ቡና አሸነፈ ሙሉ ለሙሉ 90 ደቂቃውን በልጠን ተጫውተናል ያገኘናቸውንም እድሎች በበረኛው ጥረት እና በግቡ ብረት ታግዘው አሸንፈው ወተዋል ጫዋታው ግን እኛ ሰባት ወይም ስድስት አግብተን ማለቅ ነበረበት ውጤቱ ጫዋታውን አይገልፀውም ፡፡ በአራት ጨዋታዎች ላይ አለማሸነፋችን ግን ቡድኔን ጫና ውስጥ አይከተውም ከቋሚ ተሰላፊዋቼ አራት ወሳኝ ተጫዋቾች ሳይኖሩ ከትልቁ ጊዮርጊስ ጋር ተጫውቶ የተሻለ ተንቀሳቅሶ መውጣት በራሱ ጥሩ ነው በቀጣይ ግን ወደ አሸናፊነት እንመጣለን በርግጠኝነት ይህን ማድረግ የሚችሉ ልጆችም አለን ያያቹህትን ይመስሉም ነበር :: ግቧን ያስቆጠረው ሙጃይድ ልጅ ነው ካለቦታው ተሰልፎ ጥሩ ነገር አድርጎል ግብ ስላገባ ምክኖያት አናደርግበትም ጥሩም ልጅ ነው በሱ ላይ ተቃውሞ የለኝም፡፡
ፋሲል ተካልኝ-የቅዱስ ጊዮርጊስ ም/አሰልጣኝ
“በመጀመሪያ ወደ ዚህ ስንመጣ ጫዋታው ለኛ ከባድ እንደሚሆን ገምተን ነበር ለምን በብሔራዊ ቡድን እና በጉዳት ያልነበሩ ተጫዋቾች ነበሩን ሜዳ ላይም አማራጮቻችንን ሊያሳጥሩ እንደሚችሉ እናውቅ ስለነበረ ነገር ግን ከዚህ ጫዋታ በዋነኝነት ምንፈልገው ሶስት ነጥብ ብቻ ነበር ፡፡ በሁለተኛው አጋማሽ ሲዳማ ከኛ የተሻለ ነበር ጥሩ ተጫውቷል የግብ እድልም መፍጠር ችሏል ተጫዋቾቻችንም ያን ሶስት ነጥብ አሳልፎ ላለመስጠት የነበራቸው ፍላጎት እጅግ ጥሩ ነበር፡፡ በመጨረሻም ያን አሳክተን ወጠናል የሚመራ ቡድን ምንጊዜም የሚታወቅ ነው ከሜዳ ውጭ እንደመጫወታችን በሁለተኛው አርባአምስት ያንን ለማስጠበቅ ወደ ኃላ ተመልሰን ተጫውተናል ይህም በተፈጥሯዊ ለሚመራ ቡድን ይህ አጨዋወት መከተል ግድ እኛም በመጨረሻወቹ ደቂቃዎች ላይ እኛም የግብ እድል ፈጥረናል እንደ ተጋጣሚያችንን ጥንካሬ በርግጥ ክፍተቶቻችንን አሳይቶናል ከማሸነፋችንም በዘለለ ብዙ ነገር ለቀጣይ አስተምሮናል በዛሬው ጫወታ በተለያዩ ምክንያቶች 7 ያህል ተጫዋቾች የሉንም አማራጮቻችንንም ያሳጣናል ይህንን ግን እንደ ሰበብ ማቅረብ አንፈልግም ወደ ሻምፒዮናው መዝለቅ ነው የምንፈልገው::