በካፍ ኮንፌድሬሽን ካፕ የዛንዚባሩ ዚማሞቶ 2ለ1 በሆነ የድምር ውጤት አሸንፈው ያለፉት ወላይታ ዲቻዎች ዛሬ በሐዋሳ አለማቀፍ እስቴድየም የግብፁን ጠንካራ ተፋላሚ ዛማሌክን 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።
በከፍተኛ ድጋፍ ታጀበው ወደ ሜዳ የገቡት ባለሜዳዎቹ ወላይታ ዲቻዎች ኳስን ተቆጣጥሮ በአንድ ሁለት ቅብብል በመጫወት የተሻሉ ነበሩ።በአንፃሩ እንግዳዎቹ ዛማሌኮች ሜዳቸውን ሸፍነው በመልሶ ማጥቃት እና ከመስመር በሚጣሉ ኳሶች ጫና ለመፍጠር ሙከራ አድርገዋል።
በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ዛማሌክ ግብ ክልል መድረስ የቻሉት ወላይታ ዲቻዎች በዛብህ መለዮ ግብ ክልል ውስጥ ያገኘውን ኳስ በግሩም ሁኔታ ከመረብ አሳርፋት ባለ ሜዳዎቹን መሪ አድርጓቸዋል።
ከግቧ መቆጠር በሆላ በተሻለ መልኩ ኳስን ተቆጣጥሮ በመጫወት ቢችሉ ወደ ወላይታ ዲቻ ግብ ክልል የሚጥሏቸው የመስመርም ሆነ ረዥም ኳሳች የተሳኩ አልነበሩም።
- ማሰታውቂያ -
በ37ተኛው ደቂቃ የወላይታ ዲቻው ተከላካይ ተክሉ ታፈሰ የሰራውን ስህተት ተጠቅሞ ኢማድ ፋቲህ ግብ ጠባቂውን ወንደሰን ገረውን በማታለል ግብ አስቆጥሮ ጨዋታውን ወደ 1ለ1 ውጤት ቀይሮታል።ከግቧ መቆጠር በሓላ እንግዳዎቹ የተረጋጋ የኳስ እንቅስቃሴ አድርገዋል። በ41ተኛው ደቂቃ ሀዚም ኢማም ከቀኝ መስመር ያሻገረውን ኳስ የዛማሊኩ የፊት መስመር ተጫዋች ሳይጠቀምበት ግብ ጠባቂው ወንደሰ ገረመው አድኖበታል።
በ44ተኝው ደቂቃ ከግራ መስመር ያሻገረለትን ኳስ ዘላለም እያሱ ግብ ክልሉ ጠርዝ ላይ አክርሮ መቷት በግቡ እናት ላይ ወታለች።የመጀመርያው አጋማሽ 1ለ1 በሆነ ውጤት የመጀመሪያው አጋማሽ ተጠናቋል።
በሁለተኛው አጋማሽ በይበልጥ ተጠናክረው የገቡት ባለሜዳዎቹ ወላይታ ዲቻዎ ኳስ ተቆጥረው በመጫወታው የበላይነት ወስደውል።በ48ተኛው ደቂቃ ተስፉ ኤሊያስ ወደ ግብ ለጃኮ አራፋት ያሻገረውን ኳስ ሳይጣቀምበት የዛማሊክ ተከላካዮች አውጥተውበታል።ዛማሊኮች በረጅ በሚለቋቸው ኳሶች ጫና ለመፍጠር ቢሞክሩም ለግብ የቀረበ ሙከራ ማድረግ አልቻሉም።
በ77ተኛው ደቂቃ አብዱልሰመድ አሊ ከመስመር ያሻገረለትን ታዳጊ ተጫዋች ያሬድ ዳዊት ወደ ግብ ቀይሯት ወላይታ ዲቻን መሪ አድርጓቸዋል።
እንግዳዎቹ ዛማሊኮች ከግቧ መቆጠር በሓላ በረዥም ኳሶች ግብ ለማስቆጠር ጥረት ቢያደርጉም የወላይታ ዲቻው ግብ ጠባቂው ወንደሰን ገረመው አምክኖባቸዋል።አራተኛው ዳኛ ጭማሪ 4 ደቂቃ ካሳዩ በሓላ ዛማሊኮ በወላይታ ዲቻ የግብ ክልል ውስጥ በጭንቅላት ሶስት ጊዜ ከተቀባበሉ በሓላ ካሶንጎ ካቦንጎ በጭንቅላት መቶት ግብ ጠባቂው በቀላሉ እድኖበታል። ወዲያው በቀኝ መስመር ካሶንጎ ካቦንጎ ያገኘውን ኳስ አክርሮ መቶት ወንደሰን በቀላሉ አድኖበታል ሆኖም ኳሷን ሲመታ ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ ወጥቷል።ጨዋታውም ለመድረኩ አዲስ በሆኑት ወላይታ ዲቻዎች 2ለ1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
ከ10 ቀን በኃላ ሁለተኛውን የመልስ ግጥሚያ በናስር ከተማ 75,000 ተመልካች በሚይዘው ካይሮ ኢንተርናሽናል ስታዲየም እሚጫወቱ ይሆናል።
የአሰልጣኞች አስተያየት
አሰልጣኝ ዘነበ ፍስሀ -ወላይታ ድቻ
“እኔ እንደጠበኩት ባይሆንም ጨዋታው ከሞላጎደል ጥሩ ነበር በመጀመሪያ አጋማሽ ኳሱን ተቆጣጥረን መጫወት ችለናል፡፡
የግብ እድሎችንም በተደጋጋሚ በመፍጠር ጎሎችን በማግባት የዛሬውን ጨዋታ አሸንፈን ልንወጣ ችለናል፡፡ተጋጣሚያችን ዛማሊክ በጣም ጥሩ እንቅስቃሴ አሳይተዋልየቡድን ስራቸው በጣም ደስ ይላል፡፡ ነገር ግን እኛ ጥሩ ስለነበርን የእነሱ አጨዋወት ጎልቶ እዳይወጣ ማድረግ ችለናል።በስነልቦና ረገድ እጅግ በጣም ተዘጋጅተናል ከዚማሚቶ ጋር በነበረን ጨዋታ ቡዙ ልምዶችን መውሰድ ችለናል፡፡ ከዛ በመቀጠል በተለይም ተጋጣሚያችን ዛማሊክ በቅርብ ያደረጋቸውን ጨዋታዎች በመመልከት በመስመር የሚያደርጉትን ጥቃት በመመልከት በዛ መሠረት የመስመር ጨዋታቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዳይጫወቱ ማድረጋችን ለዛሬው ድል አብቅቶናል፡፡ጨዋታው ገና አላለቀም ገና 90ደቂቃ አለ ዛሬ ያየናቸውን ስህተቶች በመድፈን ለቀጣዩ ጨዋታ ከዚህ በበለጠ ተጠናክረን እንቀርባለን፡፡”
አሰልጣኝ ኢሀብ ጋላል -ዛማሌክ
ድህረ ጨዋታ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።