በኢትዮጵያ ፕሪሜር ሊግ 13ተኛ ሳምንት ጨዋታ ሐዋሳ ከተማን ከአርባ ምንጭ አገናኝቶ 1ለ1 ነጥብ ተጋርተዋል፡፡
ባለ ሜዳዎቹ ሐዋሳ ከተማዎች በኳስ ቁጥጥሩም ሆነ ወደ ግብ በመድረሱ ተሻሉ ነበሩ በ5ተኛው ደቂቃ ከአዲስ አለም ተስፋዬ የተቀበለውን ኳስ ታፈሰ ሰለሞን መቷት በግቡ አናት ላይ ወታለች፡፡ በ11ኛው ደቂቃ እስራኤል እሸቱ ከግራ መስመር ያሻማውን ኳስ ፍቅረየሱስ ተ/ማርያም በግሩም ሁኔታ በጭንቅላት ከመረብ አሳርፏት ባለሜዳዎቹን መሪ አድርጓቸዋል፡፡ከግቧመቀጠር በሗላ አርባ ምንጭ ከተማዎች ሀይል በተቀላቀለበት እንቅስቃሴ በመልሶ ማጥቃት ሲጫወቱ በአንፃሩ ባለሜዳዎቹ ኳስን ተቆጣጥሮ በአንድ ሁለት ቅብብል ወደ ግብ በመድረስ ተጭነው ተጫውተዋል፡፡
በ32ተኛው ደቂቃ በአንድ ሁለት ወደ ግብ የቻሉት አርባ ምንጭ ከተማዎች ተመስገን ካስትሮ ወደ ግብ ቀይሯት ጫወታው 1ለ1 አርጎታል፡፡ የመጀመርያው አገሰማሽ ሊጠናቀቅ ደቂቃዎች ሲቀሩት ፍቅረየሱስ ተ/ማርያም ለታፈሰ ሰለሞን አሻግሮለት ያገኘውን ግልፅ የማግባት እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ በዚው ውጤት ወደ መልበሻ ቤት አምርተዋል፡፡በሁለተኛው አጋማሽ እደተጀመረ ሐዋሳ ከተማዎች እድሎችን መፍጠር ቢችሉም ሳይጠቀምባቸው ቀርተዋል፡፡50ኛው ደቂቃ ታፈሰ ሰለሞን ከማዕዘን ያሻገረውን ኳስ እስራኤል እሸቱ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡ከሶስት ደቂቃ በሗላ ስታ ዮሐንስ የመታው ኳስ ዮሐንስ ሴጌቦ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ተገናኝቶ ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡
በ56ኛው ደቂቃ በዮሐንስ ሴጌቦ ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ዳዊት ፍቃዱ ፍ.ቅ ክልል ውስጥ ያገውን ኳስ ግብ ጠባቂው በቀላሉ አድኖበታል፡፡ከደቂቃዎች በሗላ የተገኘችውን የመዕዘን ምት ፍቅረየሱስ ተ/ማርያም መቷት ወደ ግቡ አቅጣጫ ተቆርጣ ስትሄድ ግብ ጠባቂው አድኗታል፡፡አርባ ምንጭ ከተማዎች በተደጋጋሚ ጥፋት በመስራት እና ከዳኛ ጋር ጭቅጭቅ ሲፈጥሩ ነበር፡፡ጨዋታው ይሄ ነው የሚባል ለግብ የቀረበ ሙከራ ሳይታይበት በዚው ውጤት ተጠናቋል፡፡ከጨዋታው መጠናቀቅ በሗላ የሐዋሳ ከተማ ደጋፊዎች በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ላይ ተቃዋሟቸውን አሰምተዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
የአሰልጣኝ አስተያየት
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ -ሀዋሳ ከተማ
“በሜዳችን እንደ መጫወታችን አጥቅተን ነው የተጫወትንው፡፡አሁንም ግብ የማግባት ክፍተት አለብን፡፡ሊጉ ላይ ካሉት ክለቦች በበለጠ ሁኔታ ከታች ላደጉ ልጆች እድል እየስጠን ነው፡፡ ባሉኝ ልጆች ከማንም ቡድን የተሻለ እየተጫወትን ነው፡፡ ምንም ጫና የለብኝ ክፍታችን ላይ አንሰራለን፡፡ተጫዋቾች ላይ ምንም አይነት ቅጣት አላስተላለፍንም ከአቅም በታች ለተጫወቱ ተጫዋቾች ማስጠንቀቂያ ነው የሰጠንው፡፡ ”
አሰልጣኝ እዮብ ማለ-አርባምንጭ ከተማ
“ጨዋታው ደርቢ እንደመሆኑ ከባድ ነበር፡፡
በመጀመርያ ጎል ተቆጥሮብናል ከዛም በመልሶ ማጥቃት አስቆጥረን ነጥብ ተጋርተናል፡፡ቡድኑ ውስጥ በራስ መተማመን ችግር አለ አሱ ላይ እንሰራለን፡፡ወራጅ ቀጠና አይመጥነንም በርግጠኝነት እንወጣለን፡፡”