የባለሜዳዎቹ አርባምንጮች የበላይነት የታየበት እንዲሁም እንግዳዎቹ ድሬዳዋ ከተማዎች ወርደው የታዩበት የመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ገና በመጀመርያወቹ ደቂቃዎች ነበር ሙከራን መመልከት የቻልነው፡፡
በ 2ደቂቃ ከ25 ሜትር እርቀት አከባቢ በአጥቂው ፀጋዬ አበራ አማካኝነት ያገኙት ኳስ አግዳሚ ብረቱን በመግጨት ወደ ውጪ የወጣችው ኳስ በአዞዎቹ በኩል የመጀመሪያ ሙከራቸው ነበረች፡፡
ከዚች ሙከራ በሃላ መነቃቃትን ያሳዩት አዞዎቹ በጥቂት ደቂቃወች ልዩነት ተመስገን ካስትሮ እና ፀጋዬ አበራ በተደጋጋሚ ወደ ግብ ቢሞክሩም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡
ከነዚህ ሙከራ በሃላ ድሬዳዋ ከተማዎች የማጥቃጥ ቁጥራቸውን ቀንሰው ወደ መከላከሉ በማመዘን የጨዋታውን ፍጥነት ለመቀነስ ኳስን በረጅም ሲያወጡ ተስተውለዋል፡፡
- ማሰታውቂያ -
ከብዙ ደቂቃዎች በሃላ ጫና መፍጠር የጀመሩት አዞዎቹ በ31ኛው ደቂቃ በጨዋታው የድሬወችን ተከላካዮች ሲፈትን የቆየው ፀጋዬ አበራ የግል ብቃቱን በመጠቀም ያሻማውን ኳስ በጥሩ ቦታ ላይ የነበረው አለልኝ አዘነ ወደ ጎል በመቀየር ባለሜዳወቹን ቀዳሚ ማድረግ ችሏል፡፡ የግቧ ባለቤት ታዳጊው ተስፈኛ አለልኝ አዘነ የመጀመሪያ የፕርምየር ሊግ ጎሉ ሆና ተመዝግባለች፡፡
ከግቧ በሃላ በጥቂት ደቂቃዎች ልዩነት አጥቂው ተመስገን ካስትሮ በግንባሩ የሞከራት ኳስ ቋሚ ብረቱን ታካ ሲትወጣ፡፡የአየር ንብረቱ የከበዳቸው ሚመስሉት ድሬዳዋ ከተማዎች ከኩዋሜ አትራም መጠነኛ የቅጣት ምት ሙከራ በስተቀር ምንም አይነት ሙከራ ሳያደርጉ ወደ እረፍት ልወጡ ችለዋል፡፡
በሁለተኛው አጋማሽ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ባለሜዳወቹ ነጥብ አስተብቆ ለመወጣት ወደሃላ በማፈግፈግ በመልሶ ማጥቃት ለመጫወጥ ወደ ሜዳ የገቡ ሲሆን፡፡ ድሬዳዋ ከተማዎች ከመጀመሪያው አጋማሽ እንቅስቃሴ ተሽለው የተገኙበት ነበር፡፡
በተደጋጋሚ ወደ አርባምንጭ ግብ ክልል መድረስ የቻሉት ድሬወቹ የአርባምንጭ ተከላካይ ክፍል ተጫዋቾችን አልፈው ጎል ማስቆጠር ሲያቅታቸው ተሰተውለዋል፡፡ የተጫዋች ለውጥ በማድረግ ወሰኑ ማዜን በዘካርያስ ፍቅሬ በመቀየር የተከላካይ ክፍላቸውን በመቀነስ የአጥቂ ክፍላቸውን ከፍ በማድረግ የአቻነት ግብ ለማግኘት ቢጥሩም የረባ ሚባል ሙከራ ማድረግ ሳችሉ ቀርተዋል፡፡ አዞዎቹ በመከላከሉ ረገድ የተሳካ እንቅስቃሴ በማድረግ ጨዋታውን 1-0 በሆነ ውጤት ሊጨርሱ ችለዋል፡፡
ድሉንም ተከትሎ አርባምንጭ ከተማ ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ሲችል ሽንፈት ያስተናገደው ድሬዳዋ ከተማ በወራጅ ቀጠናው ሊቆይ ችሏል፡፡
የአሰልጣኞች አስተያየት
አሰልጣኝ እዮብ ማለ ~ አርባምንጭ ከተማ
” በጨዋታው ያገኘናቸውን የጎል ዕድሎች ያክል ባናስቆጥርም የክለቡን ነጥብ ወደ 13 ከፍ የሚያደርግ ውጤት ማግኘታችን አስደስቶናል። ቀደም ሲል ቡድናችን የስነልቦና ችግር የነበረበት ሲሆን አሁን ግን ሙሉ ለሙሉ ችግራችንን በመቅረፋችን ውጤታማ አድርጎናል። ቡድኑን ከያዝኩ ሶስተኛ ጨዋታዬ ነው በሶስት ጨዋታዎች በሜዳችን በሚገባ ሙሉ ነጥብ ሰብስበናል ከሜዳችን ውጭ አቻ ተለያይተናል ለአንድ ቡድን ይሄ ትልቅ መሻሻል ነው በዚህ ውጤት መቀጠል ያስፈልጋል፡፡ በቀጣይ በአጥቂ ክፍል ላይ የሚታየውን ክፍተት በማስተካከል በአሸናፊነት መንፈስ እንቀጥላለን።”
ም/አሰልጣኝ ስምዖን አባይ ~ ድሬዳዋ ከተማ
” በመጀመሪያው አጋማሽ ቡድናችን የቅንጅት ችግር ነበረበት፡፡ጎል ለማስቆጠር ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም በሁለተኛው አጋማሽ ተጭነን በመጫወት በኳስ ቁጥጥሩ የበላይነት አሳይተናል። አርባ ምንጭ ከተማ ላይ ያለው ሙቀት ያሰብነውን ያህል እንዳንጫወት አድርጎናል ። ቀጣይ ጨዋታዎች ለኛ ወሳኝ እንደ መሆናቸው ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት ጠንክረን እንጫወታለን፡፡”
ደረጃ ሰንጠረዥ
[team_standings id=”6559″ title=”” number=”16″ columns=”p,gd,pts” show_team_logo=”1″ show_full_table_link=”1″ align=”right”]