በአዳማ ከተማ ተደጋጋሚ ሙከራዎች በተጀመረው ተጠባቂው የኦሮሚያ ደርቢ አዳማ ከተማዎች በዳዋ ሆቴሳ አደገኛ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም የጎሉን አናት ታካ ልትወጣ ችላለች ::
አዳማ ከተማ በመጀመሪያዎቹ አጋማሽ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ከሳጥን ውጪ ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ተስተውለዋል ::
- ማሰታውቂያ -
በተለይም በከንአን ማርክነህ አደገኛ ሙከራ ማድረግ ቢችሉም በሊጉ አሰደናቂ ብቃቱን እያሳየ የሚገኘው የጅማ አባጅፋር ግብ ጠባቂ ሰኢድ ሀብታሙ ሊያድንበት ችሏል ::
ኳስን መሰረት አድርገው መጫወት የፈለጉት አዳማዎች በግራ እና በቀኝ መስመር ክፍላቸውን በመጠቀም ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ለማድረግ ሲጥሩ ተስተውለዋል ::
በተለይም በበረከት ደስታ ጫናዎችን ለማድረግ ሲሞክሩ በአንድ አጋጣሚ ወደ ውስጥ አሻምቶ ከንአን ማርክነህ በግምባር ገጭቶ ሰኢድ ሀብታሙ ያዳነበት ሙከራ ተጠቃሹ ነው ::ከሳጥን ውጪ በሚሻሙ ኳሶች ሙከራዎችን ማድረጋቸውን የቀጠሉት አዳማዎች በምኞት ደበበ ጥሩ የጭንቅላት ሙከራ ቢያደርጉም ወደ ግብነት ሳይቀየር ቀርቶል ::
ጨዋታውን ሙሉ ለሙሉ የተቆጣጠሩት አዳማዎች ከሳጥን ውጪተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርጉም በሰኢድ ሀብታሙ ሊድን ችሏል ::ዳዋ ሆቴሳ ከመሀል ሜዳ ተሻግሮለት ለበረከት ደስታ ሲያቀብለው ሰኢድ ቀድሞ ያዳነበት አጋጣሚ ከሚያስቆጩ አጋጣሚዎች አንዱ ነበር ::ጅማ አባጅፋሮች በተቀዛቀዙበት የመጀመሪያው አጋማሽ የግብ እድሎችን መፍጠር ተስኖቸው በጥልቀት በመከላከል አሳልፈዋል ::
ለብዙ ደቂቃዎች ያለ ሙከራ በዘለቀው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ዳዋ ሆቴሳ ከመሀል ሜዳ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ፊት ይዞ በመሄድ ግብ ጠባቂው ሰኢድ ሀብታሙን በማለፍ የሞከራት እና በግቡ አግዳሚ ላይ የወጣችው ኳስ የምታስቆጭ አጋጣሚ ነበረች ::
በሁለተኛው አጋማሽ ተሽለው መቅረብ የቻሉት ጅማ አባ ጅፋሮች በተደጋጋሚ ወደ ጎል ሲደርሱ ተስተወለዋል ::
አዳማ ከተማዎች የግራ የመስመር ክፍላቸውን ይበልጥኑ በማጠናከር በበረከት ደስታ የጅማ አባጅፋር ተከላካዮችን ሲረብሽ ታስተውላል ::
በተለይም ከመስመር ኳስን በመያዝ ከሳጥን ውጪ አክርሮ የሚሞክራቸው እና በእለቱ ድንቅ ሆኖ ባመሸው የጅማ አባጅፋር ግብ ጠባቂ ሰኢድ ሀብታሙ ሲመለሱበት ነበር ::
በሁለተኛው አጋማሽ ከመጀመሪያው አጋማሽ አንፃር የተቀዛቀዘው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ብዙም ሳቢ ባልሆነ የጨዋታ ጊዜ ያለ ግብ ሲጠናቀቅ አዳማ ከተማ ያለ መሸነፍ ጉዞውን አጠናክሮ ቀጥሏል ::