ሰርክ ኢትዮጵያ ቡና ሲጫወት ከአፍ እስከ ገደፉ ጢም ብሎ የሚሞላው የአዲስ አበባ ስታዲዮም ያለወትሮው ጭር ብሎ ነበር ጨዋታው የጀመረው። አዲስ የተጀመረው የስታድዮም የትኬት አቆራረጥ ሲስተም እና የስታድዮም ታዳሚውዎች በቀላሉ መላመድም የተሳናቸው ይመስላል።
በ 5ተኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀ ግብር ድል ማስመዝገብ ተስኗቸው አቻ በውጣት አንድ ነጥብ ብቻ ማስመዝገብ የቻሉትን ኢትዮጵያ ቡና እና ሀድያ ሆሳዕናን ያገናኘው የዛሬው ጨዋታ በመጀመሪያዎቹ 15 ደቂቃዎች የተቀዛቀዘ ጨዋታን ያሳየን ሲሆን ሁለቱም ቡድኖች ጨዋታውን ለመቆጣጠር ይሄ ኔው የሚባል ጥረት ሲያደርጉ መመልከት አልቻንም ነበር። በተደጋጋሚ የሚያደርጓቸው ቅብብሎችም ሲቆራረጡ እና የማጥቃት እንቅስቃሴያቸው ሲደነቃቀፍ ማስተዋል ችለናል።
- ማሰታውቂያ -
ከግብተባቂያቸው በረከት ኳስን መስርተው መጫወትን ያቀዱ የሚመስሉት ኢትዮጺያ ቡናዎች ሀድያ ሆሳእናዎች በአማካኝ ክፍል በቁጥር በዛ ብለው መገኘት ይህንን ያሰቡትን እንቅስቃሴ ሲያበላሽባቸው ተስተውሏል። የተከላካይ አማካኝ ሆኖ ሲጫወት የነበረው አለምአንተ ካሳም ኳሶችን ወደ መስመር በረጅም በማሻገር ሀድያ ሆሳዕና ላይ ጫና ለመፍጠር ሙከራ ቢያደርግም ሙከራዎቹ የተሳኩ አልነበሩም። በመጀመሪያዎቹ ሰላሳ ደቂቃዊች በጣም ለግብ የቀረበ ሙከራ ሆኖ መመዝገብ የቻለው በ18ኛው ደቂቃ የሀድያ ሆሳዕናው የመሀል ተከላካይ እዮብ በመቀስ ምት የሞከራት አስደናቂ ሙከራ የግቡን አግዳሚ በመምታት መውጣት የቻለው ኳስ ብቻ ነበር።
ሰልሳኛው ደቂቃ ላይ የኢትዮጵያ ቡናው የቀኝ ተከላካይ ፍቅረስላሴ ያሻገራትን ኳስ የሀድያ ሆሳዕናው ግብ ጠባቂ አቤል አበኖ ቦታውን በመልቀቅ በእጁ ከክልሉ ያራቃርትን ኳስ የኢትዮጵያ ቡናው አማካኝ አማኑኤል ወደ ግብ በመቀየር ባለሜዳዎቹን ቀዳሚ ያደረገቻቸውን ግብ ማስቆጠር ችሏል።
የመጀመሪያዋ ግብ ከተቆጠረች ከደቂቃዎች በውሃላ የሀድያ ሆሳዕና ተጫዋቾች የፈጠሩትን ስህተት በመጠቀም ከፊት አጥቂነት ወደ መስመር ወጥቶ ሲጫወት የነበረው አቡበከር ነስሮ የግል ብቃቱን በመጠቀም ለቡድኑ ሁለተኛውን ግብ ማስቆጠር ችሏል።
በተቆጠሩባቸው ሁለት ግቦች የተደናገጡ የሚመስሉት ሀድያ ሆሳዕናዎች የመጀመሪያው አጋማሽ መገባደጃ ላይ ተደጋጋሚ ስህተቶችን ሲፈፅሙ ትሰተውሏል። ለዚህም ዋነኛ ማስረጃ የሚሆነው የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ እንዳለ ደባልቄ በአርባ ሁለተኛው ደቂቃ ላይ ከግብ ጠባቂ ጋር ተገናኝቶ ያመከናት ኳስ ትገኝበታለች።
ከእረፍት መልስ በመጀመሪያ አጋማሽ ጉዳት ያጋጠመውን ተከላካያቸውን እዮብ ቢቃተን በ መስቀሌ ሴቴቦ በመቀየር የጀመሩት ሀድያ ሆሳዕናዎች ወደጨታው ለመመለስ አንዳንድ ጥረቶችን ቢያደጉም ይሄነው የሚባል የተጠና የማጥቃት እንቃስቃሴ ማድረግ አልቻሉም ነበር።
ኢትዮጺያ ቡናዎች በጨዋታው ጥሩ እንቅስቃሴ ሲያደርግ የነበረው ፍቅረስላሴ በፍፁም ቅጣት ምት ውስጥ በተፈፀመበት ጥፋት አመካኝነት ያገኙትን የፍፁም ቅጣት ምት በአቡበከር ናስሮ አማካኝነት በጨዋታው ሶስተኛውን ግብ በማስቆጠር ሀድያ ሆሳዕናዎች ገና በጨዋታው ስልሳኛ ደቂቃ ላይ ተስፋ እንዲቆርጡ እና የበለጠ ሀፍረት እንዳይከናነቡ መረባቸውን ማስጠበቅ እንዲጀምሩ ማድረግ ችለዋል።
ሀድያ ሆሳዕናዎች ሶስተኛዋ ግብ እንደተቆረችባቸው ያሳዩትን መደናገጥ እና ተስፋ መቁረጥ በመጠቅም ኢትዮጵያ ቡናዎች በ አቤል ከበደ አማክኝነት በሁለት ደቂቃ ልዩነት ውስጥ በሜዳ ውስጥ የታደሙትን የቡናማዎቹን ደጋፊ ያስፈነጠዘች ግብ በማስቆጠር ጨዋታን በ4 ለባዶ በመምራት ፍፁም የበላይነታቸውን ማሳየት ቻሉ። የኢትዮጵያ ቡናው አጥቂ እንዳለ ደባልቄ በተደጋጋሚ ያገኛቸውን ለግብ ተቀረቡ ኳሶችን ሲያመክን ብንመለከተውም በጨዋታ እንቅስቃሴ ግን በሁከቱ መስመሮች ሲጫወቱ ለነብውሩት የቡድን አጋሮችን ቦታን በማስከፈት እና አማካኝ ክፍሉን በማገዝ ድንቅ ሆኖ መዋል ችሏል።
ጨዋታውን ማሳረጊያ ግብ በውብ የጨዋታ ፍሰት የተገኘቸዋን ኳስ በሰማንያኛው አጋማሽ በአጥቂው እንዳለ ደባልቄ ተቀይሮ ወደ ሜዳ ተቅይሮ መግባት የቻለው ሀብታሙ ታደሰ ወደ ግብ በመቀየር ኢትዮጵያ ቡናን በውድድ አመቱ ከፋሲል ከተማ ቀጥሎ ተጋጥያሚው ላይ አምስት ግብ ማስቆጠር የቻለ ሁለተኛው ቡድን መሆን እንዲችል አድርጎታል።
ከጨዋታው መጠናቀቅ በውሃላ አስተያየታቸውን የሰጡት የሀድያ ሆሳዕናው ዋና አሰልጣኝ ግርማ ታደሰ ቡድናቸው ለጨዋትው ጥሩ የሚባል ዝግጅት ማድረግ እንደቻለ እና ሆኖም ግን በጨዋትው የተቆጠሩባቸው ሁለት ተከታታይ ግቦች ተጫዋቾቻቸውን ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደከተቷቸው እና ይህም ጫና ለበርካታ ግቦች እንደዳረጓቸው ገልፀዋል። አሰልጣኙም አክለው ተከታታይ ሽንፈት ማስተናገዳቸው ተጫዋቾቻውን ተፅኖ ውስጥ መክተቱን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ቡናው ዋና አስለታኝ ካሳዬ አራጌ ከጨዋትው በውሃላ የሰጡት አስተያየት ደግሞ ቡድናቸው ሙሉ ለሙሉ ጨዋትውን እንዳለቆጣጠረ እና ገና መሰራት ያሉባቸው ስራዎች እንዳሉ ጠቁመው ተጫዋቾቻቸው ደጋፊውን ለማስደሰት የገቡበት ጫና አላስፈላጊ የግብ ሙከራዎች እንዲያደርጉ እንዳደረጋቸው መግለል ችለዋል። አሰልጣኝ ካሳዬ ከሜዳ ውጪ እያስመዘገቡ ስላሉት ደካማ እንቅስቃሴ ተጠይቀው በእንቅስቃሴ ደረጃ በጣም ደስተኛ እንድሆኑ እና ቡድናቸው ቀስ በቀስ ውጤቱን እያስተካከል እንደሚሄደ ገልፀዋል።