በ 26ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሜየርሊግ ዓዲግራት ላይ የተደረገው የወልዋሎ እና ደደቢት ጨዋታ በወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ኣሸናፊነት ተጠናቅዋል።
ወልድያን ካሸነፈው ቡድን ማናዬ ፋንቱን በ ጋናዊው ኣብዱራህማን ፋሱይኒ ቀይረው ገብተዋል።
በኣሰልጣኛቸው ንጉሴ ደስታ ድንገተኛ ሞት ምክንያት የ 25ተኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ያልተጫወቱት ደደቢቶች ቡናን ከገጠመው ቡድን እንዶህ ኩዌኬን በቅጣት በያኣብስራ ተስፋዬ እንዲሁም በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ርቆ የቆየው ግብ ጠባቂው ክሌመንት በ ታሪኬ ጌትነት ቀይረው ገብተዋል።
በዝናብ ታጅቦ የጀመረው የመጀመርያው አጋማሽ በሁለቱም ቡድን በኩል ብዙየጎል ሙከራ የታየበት ነበር።መሃል ሜዳ ላይ ሲደረጉ የነበሩ ቅብብሎች በሜዳው መጨቅየት ምክንያት ለመጫወት ሲያስቸግራቸው ነበር።
- ማሰታውቂያ -
መሃል ሜዳ ላይ የተሻለ የጨዋታ ብልጫ መውሰድ የቻሉት ወልዋሎዎች የግብ ሙከራ በማድረግም ቀዳሚ ነበሩ በተለይም ራችሞንድ ኦዶንጎ እና ፕሪንስ ያደረግዋቸው ሙከራዎች ተጠቃሽ ናቸው።
ደደቢትም ከተከላካይ ክፍሉ በሚጣሉ ረጃጅም ኳሶች የወልዋሎን ተከላካይ ክፍል ሲፈትኑ ነበር በተለይም ኣቤል ያለው ያመከናቸው ኳሶች ኣስቆጪ ነበሩ።
ባለሜዳዎቹ በ28ተኛው ደቂቃ ያገኙትን ማኣዘን ምት በኣጭሩ በማስጀመር ከግራ መስመር ኣለምነህ ያሻማውን ኳስ በረከት ተሰማ በግንባሩ በመግጨት ወልዋሎን መሪ ማድረግ ችሏል።ከግቧ መቆጠር በኋላ ደደቢቶች ኣቻ ለመሆን ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካላቸው ቀርቷል።
ሁለተኛው ኣጋማሽ ሹክቻ የበዛበት ብዙ ሙከራ ያልታየበት ነበር።የ ሁለተኛው ኣጋማሽ ሚጠቀስ ሙከራ ዋለልኝ ገብሬ በፍፁም ቅጣት ምት ሳጥን ጠርዝ ላይ ያገኘውን ኳስ በባናና ምት ጠምዝዞ ቢመታውም ክሌመንት በሚገርም ብቃት ኣድኖበታል።
ከ 60ኛው ደቂቃ በኃላ ደደቢት ተጭነው ቢጫወቱም የኣቻነት ግብ ማግኘት ኣልቻሉም።ይባስ ብሎ ኣማካይ ተጫዋቻቸው ኣስራት በሁለት ቢጫ በቀይ ኣጥተዋል።ጨዋታውም ሌላ ጎል ሳያስተናግድ በወልዋሎ ዩኒቨርስቲ ዓዲግራት ኣሸናፊነት ተጠናቋል።
ደረጃ ሰንጠረዥ
[team_standings id=”6559″ title=”” number=”16″ columns=”p,gd,pts” show_team_logo=”1″ show_full_table_link=”1″ align=”right”]