በትግራይ ስታድየም የተካሄደው የወልዋሎ ዓድግራት ዩኒቨርሲቲ ና የደቡብ ፖሊስ ጨዋታ በኤፍሬም አሻሞ ብቸኛ ግብ በባለ ሜዳዎቹ ወልዋሎ አሸናፊነት ተጠናቋል።
በሁለተኛው ሳምንት መቐለ 70 እንደርታን ከገጠመው ቡድን ለውጦችን ኣርገው ወደ ሜዳ የወረዱት በጸጋይ ኪዳነ ማርያም እሚመሩት ወልዋሎዎች የመጀመርያ አጋማሽ ላይ ብልጫ ወስደው መጫወት ችለዋል።በሁለቱም መስመር በኤፍሬም አሻሞ፣አብዱራህማን ፋሴኒ፣እንየው ካሳሁን ኣማካኝነት የደቡብ ፖሊስ ተከላካይ ክፍልን ሲፈትኑ የነበሩት ወልዋሎዎች በሪችሞንድ ኦዶንግ ብዙ የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል።
በረከት ይስሃቅን በብቸኛ ኣጥቂነት የተጠቀሙት በዘላለም ሽፋራው ሚመሩት ደቡብ ፖሊሶች ኣብዛኛውን የመጀመርያ 45 በመከላከል ተጠምደው ሲያሳልፋ አልፎ እልፎ በበረከት ይስሃቅ ና በብርሃኑ በቀለ አማካኝነት ሙከራዎችን ማድረግ ችለዋል ።ጨዋታው በተጀመረ በ35ኛው ደቂቃ ከግራ መስመር አፈወርቅ ኃይሉ ሰንጥቆ ያሾለከውን ኳስ ኤፍሬም አሻሞ በጥሩ አጨራረስ ወልዋሎን መሪ ያደረገች ጎል ማስቆጠር ችሏል።
- ማሰታውቂያ -
በሁለተኛው አጋማሽ ወልዋሎ ከመጀመርያው አጋማሽ አንጻር ብዙም የግብ እድሎችን መፍጠር ባይችሉም እልፎ አልፎ እድሎችን ሲፈጥሩ ነበር በተለይ ከቀኝ መስመር ሪችሞንድ ኦዶንግ እሻምቶት እብዱራህማን ያባከነው ኳስ እሚጠቀስ አጋጣሚ ነበር። ደቡብ ፓሊሶችም የቀኝ መስመር ተከላካዩን ዘነበ ከድርን በብሩክ ኤልያስ በመቀየር ከመጀመርያው 45 የተሻለ ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም ቡድኑ የሚያጠቃበት መንገድ ተገማች እና ያልተደራጀ መሆኑን ተከትሎ በቀላሉ በወልዋሎ ተከላካይ ክፍል በቁጥጥር ስር ሲውሉ ተስተውሏል ።
ብዙ ሙከራዎች ያልታዩበት ሁለተኛው እጋማሽ ምንም ጎል ሳያስተናግድ ጨዋታው በወልዋሎ ዓድግራት ዩኒቨርሲቲ እሸናፊነት ተጠናቋል።
የአሰልጣኞች ኣስተያየት
ፀጋይ ኪዳነ ማርያም -ወልዋሎ አዲግራት ዮ
“የዛሬ ጨዋታ ከባድ ነበር ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ ነጥብ መጣላችን ጥሎ ስለመጣ ጫና ውስጥ ሆነን ስለተጫወትን ብዙ የግብ እድሎችን ማምከን ችለናል፤ተከላካይ ክፍላችንም ጥሩ ነበር። “
ዘላለም ሽፈራው -ደቡብ ፖሊስ
“ጨዋታው በተወሰነ መልኩ ጥሩ ነበር ብንሸነፍም ከሌሎች ጨዋታዎች የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገናል።”ጨዋታው በተወሰነ መልኩ ጥሩ ነበር ብንሸነፍም ከሌሎች ጨዋታዎች የተሻለ እንቅስቃሴ አድርገናል።በመጀመርያው አጋማሽ በተከላካዮቻችን ላይ ያለ መቀናጀት ችግሮች ነበር በሁለተኛው አጋማሽ ያንን ችግር ቀርፈው ገብተዋል። ሌላው የዛሬ ድክመታችን የማጥቃት ኃይላችን ትንሽ ተገድቦ ነበር። ከዛ ውጭ ጨዋታውን ለመቆጣጠር ጥረት አድርገናል።”