ለ2022 የኳታር ዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣርያ የመጀመርያ ዙር ጨዋታውን ባህርዳር ላይ ከሌሴቶ ጋር የተጫወተው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይቷል።
በ4-3-3 አጨዋወት ወደ ሜዳ የገቡት ዋልያዎቹ ጨዋታው ላይ ከተጋጣምያቸው የተሻለ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢያሳዩም እድሎች በመፍጠርና የተፈጠሩት እድሎች በመጠቀም ላይ የነበራቸው ክፍተት ግብ አንዳያስቆጥሩ አንቅፋት ሆኗቸው ታይቷል።
- ማሰታውቂያ -
በመጀመርያው አጋማሽ የተሻለ የተንቀሳቀሱት ዋልያዎቹ ከግራ መስመር በሚነሱ ኳሶች የግብ እድሎችን መፍጠር ችለዋል።የጨዋታው የመጀመርያ እድል አማኑኤል ገብረሚካኤል ከግራ መስመር ያሻማው ኳስ ዑመድ ኡኩሪ በቀጥታ ቢመታውም በሌሴቶ ተከላካዮች ተጨርፎ ወደ ውጭ ወጥቷል።ኳስን ከኃላ መስረተው ለመጫወት የሞከሩት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች በሜዳው የመጨረሻ ክፍል ላይ የነበራቸው አለመግባባት የጠራ የግብ እድል እንዳይፈጥሩ አድርጓቸዋል።አሁንም በተመሳሳይ መልኩ ኳስን ከኃላ መመስረትን የመረጡት የአብርሃም መብራህቱ ልጆች በ24ኛው ደቂቃ በጥሩ ቅብብል የተጀመረችው ኳስ በግራ መስመር በነበረው ሽመልስ በቀለ እግር ላይ ገብታ ሽመልስም ወደ ውስጥ ሰብሮ በመግባት ቢያሻማትም ንቁ ሆነው ሲከላከሉ የታዩት የሌሴቶ ተከላካዮች አጨናግፈውታል።
መከላከልን ምርጫጨው አርገው ወደ ሜዳ የገቡት ሌሴቶዎች አልፎ አልፎ ከመሃል ሜዳ በረጅሙ በሚላኩ ኳሶች እድሎችን ሲፈጥሩ ታይቷል።በተለይ በ13ኛው ና 32ኛው ደቂቃ ላይ በታባንስ እና ስትሩማኔ አማካኝነት ያደረጉዋቸው ሙከራዎች በምሳሌነት ሚጠቀሱበጋቶች ናቸው።የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን የጨዋታው የመጀመርያ ሙከራውን በ34ኛው ደቂቃ በሙጂብ ቃሲም አማካኝነት አድርጓል፤አማኑኤል ገብረሚካኤል ከግራ መስመር ወደ ውስጥ ሰብሮ በመግባት ለሙጂብ ያሾለከለትን ኳስ ጨዋታው ላይ በብቸኛ አጥቂነት የተሰለፈው ሙጂብ ቢመታውም ግብ ጠባቂው ታሃቢሶ ሊቻባ አድኖበታል።የመጀመርያው አጋማሽ የመጨረሻ የግብ እድል የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ጋቶች ፓኖም አማካኝነት ቢያገኝም ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ብዙ የግብ እድሎች ያልተፈጠሩበት
ሁለተኛው አጋማሽ እንደ መጀመርያው አጋማሽ በተመሳሳይ መልኩ የዋልያዎች የኳስ ቁጥጥር ብልጫ የታየበት ነበር።ሆኖም ግን አሁንም የሜዳው የመጨረሻ ክፍል ላይ ሲደርሱ የነበራቸው አለመናበብና የፈጠራ ብቃት አጥረት እድሎችን እንዳይፈጥሩ እንቅፋት ሆኗቸው ታይቷል።
አዞዎቹ በበኩላቸው አሁንም በተመሳሳይ ወደ ኃላ ማፈግፈግን ምርጫጨውን በማድረግ ሲከላከሉ፤ከመጀመርያው አጋማሽ በተለየ መልኩ በመልሶ ማጥቃት በቁጥር በዝተው በመሄድ እድሎችን ለመፍጠር ሞክረዋል።አብርሃም መብራህቱ በሁለተኛው አጋማሽ የመጀመርያ ቅያርያቸውን ቢንያም በላይን አስወጥተው ከንዓን ማርክነህ በማስገባት እድሎች እንዲፈጠሩ ለማድረግ ቢሞክሩም የሌሴቶ መከላከልን ሚሰብር ሰንጣቂ ኳስ ሊገኝ አልቻለም።
ሰዓት እየገፋ በሄደ ቁጥር ጫና እየበዛባቸው የሄዱት ዋልያዎቹ በመጨረሻዎቹ 20 ደቂቃዎች ላይ መረጋጋት ተስንዋቸው ቷይቷል።በዚህም መሰረት ዋልያዎቹ በሜዳቸው ያካሄዱት የመጀመርያ ዙር ጨዋታቸውን ያለግብ አቻ ለማጠናቀቅ ተገደዋል።የመልሱ ጨዋታ የፊታችን እሁድ ጶግሜ 3 ሌሴቶ ላይ እሚካሄድ ይሆናል።