ተቋርጦ የቀጠለው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ 23ኛው ሳምንት መሪው ጅማ አባጅፋርንና የወራጅ ስጋት ያለበትን አርባምንጭን በጅማ አገናኝቶ ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል ።
#እሮብ ግንቦት 15 ከቀኑ በ 9፡00 ሰአት ሊጀመር መርሀ ግብር የተያዘለት ጨዋታ በኢንተርናሽናል ዳኛ በላይ ታደሰ 9፡00 ሲል ተጀምሯል ፡፡
ባለሜዳዎቹ ኢትዮጵያ ቡናን የገጠሙበትን 4-4-2 አሰላለፍ መላኩ ወልዴን በአሮን አሞሀ በመቀየር ይዘው ሲገቡ እንግዳው ቡድን አርባምንጭ በአንፃሩ 4-5-1 አሰላለፍን መርጦ ተጫውቷል ፡፡
ጨዋታው ከተጀመረ ጀምሮ አባጅፋር ሙሉበሙሉ በሚያስብል ሁኔታ ኳስን በመቆጣጠር እንዲሁም አርባምንጭ በመከላከል እና በተለያዩ ግዝያት በመውደቅ ሰዓት በማባከን ያለፈው የመጀመርያው 45ደቂቃ ተመልካቹን በጠም ያስቆጣና ዳኛውም የአርባምንጭ ተጫዋቾችን በማስጠንቀቅ ያለፈበት ነበር በዚህም ወቅት ዳኛው ለፅዩን እና ተመስገን የማስጠንቀቂያ ካርድ ሰጥተዋል።
- ማሰታውቂያ -
ወደጎል በመድረሱ በኩል ቅድሚያውን የወሰዱት ባለሜዳው ቡድን በኦኪኪ አማካኝነት በ2ኛው ደቂቃ ከአሮን ጋረሸ አንድ ሁለት በመጫወት ኦኪኪ የሞከረውን ኳስ የአርባምንጩ በረኛ ፅዮን በቀላሉ አድኗታል።
እምብዛም የጎል ሙከራ ባልታየበት የመጀመርያው አጋማሽ አርባምንጭ ሙሉ በሙሉ በመከላከል የጅማን የኳስ ፍሰት በማቋረጥ የተሳካ ስራ ሰርተዋል የጅማዎችም የኳስ ፍሰት እንደቀድሞ ባልነበረበት ኳስን ለአጥቂዎቹ ተመስገን እና ኦኪኪ ማድረስ አልቻሉም ነበር። በ35ኛ ደቂቃ ላይ ዮናስ ገረመው ከረጅም ርቀት የሚገርም ሙከራ አድርጎ ፅዮን በሚገርም ብቃት አውጥቶበታል
ከእረፍት መልስም ይበልጥ ተጠናክረው የኳስ ቁጥጥር የያዙት ጅማዎች በኦኪኪና ተመስገን ሙከራዎችን ቢያደርጉም ኳስና መረብን ማገናኘት አልተቻለም ሰዓት እየገፋ በሄደ ቁጥር አርባምንጮች በተደጋጋሚ በመውደቅና ዳኛን በመክበብ ሰዓት ሲያባክኑ ነበር ጅማዎችም ተጨማሪ ሁለት አጥቂዎችን ሳምሶንንና ኢብራሂምን በማስገባት በ4 አጥቂ ተጫውተዋል
ጨዋታው ሊያልቅ 88ኛው ደቂቃ ላይም ኳስ በእጅ በመነካትዋ ዳኛው ፍ/ቅ/ም በሰጡበት ወቅት የአርባምንጭ ተጫዋቾች አያሰጥም በማለት ሜዳ ለቀው በመውጣት ለ9ደቂቃ ተቋርጦ ነበር ጨዋታው ሲቀጥልም የተሰጠውን ፔናልቲ ኦኪኪ የመታውን ኳስ ፅዮን መርዕድ አድኖበታል። በዚሁ ጨዋታው ያለ ምንም ግብ 0-0 አልቋል። ይህን ተከትሎም ባለሜዳዎቹ አሁንም በ40ነጥብ በጎል ብልጫ 1ኛ ደረጃ ላይ ረግተዋል በአንፃሩ አርባምንጭ አሁንም እዛው ወራጅ ቀጠናው ውስጥ ይገኛሉ።