የአምና ቻምፒዮኖቹን መቐለ 70 እንደርታን እና እና የ14 ጊዜ የፕሪምየር ሊጉን ቻምፕዮኖች ቅዱስ ጊዮርጊስን ባገናኘውን የስድስተኛ ሳምንት ብቸኛው የእሁድ መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ስታድዮም ታዳሚ እና አዲሱ የስታድዮም መግቢያ ቲኬት መቁረጫ ሲስተም መላመድ ተስኗቸው በጨዋትው የመጀመሪያ ሰላሳ ደቂቃዎች በስታድዮሙ ባልተለመደ ሁኔታ በርካታ ባዶ መቀመጫዎችን ማስተዋል ችለናል።
በመጀመሪያዎቹ 30 ደቂቃዎች ሁለቱም ቡድኖች ለአጥቂዎቻቸው በሚሻገሩ ረጃጅም ኳሶች ለማጥቃት ሲሞክሩ የተስተዋለ ሲሆን ፈረሰኞቹ ከ ሙሉአለም መስፍን (ዴኮ) በረጅሙ ለአቤል ያለው እና ለ ጋዲሳ መብራህቴ በሚሻገሩ ኳሶች የ መቐለ 70 እንደርታን ተከላካይ ክፍል ለመፈተሽ ሙከራዎችን ቢያደርጉም አብዛኖቹ የተሳኩ አልነበሩም። በአንፃሩ ደግሞ እንግዶቹ መቐለዎች ኳሶችን ለአጥቂው ኦኪኪ አፎላቢ በማሻገር ከአምናው የፕሪምየር ሊጉ ኮከብ ግብ አግቢና ኮከብ ተጨዋች አማኑኤል ጋር ኳሶችን እየተቀባበሉ እንዲጫወቱ ሙከራዎችን ሲያደርጉ ተስተውሏል።
የጨዋትው ሂደት እየቀተምጠለ ሲሄድ የፈረሶኞቹ የመስመር ተጫዋች ጋዲሳ መብራህቴ ወደ መሃል እየገባ እና ወደ መስመር እየወጣ ሲያደርጋቸውየነበሩት እንቅስቃሴዎች ባለሜዳዎቹ አልፎ አልፎም ቢሆን ጥሩ የሆነ የማጥቃት እንቅስቃሴ እንዲፈጥሩ ሲረዳቸው መመልከት ችለናል ሆኖም ግን ኳሶች አጥቂዎቹ ጌታነህ ከበደ እና ሳልሀዲስ ሰዒድ ጋር ሲደርሱ በመቐለ ተከላካዮች ጫና እና ኳሶቹን ለመቀበል ትክክለኛ ቦታ ላይ የተገኘ ሰው በማጣት ምክንያት ሲቆራረጡ ተስተውሏል።
በኢትዮጺያ ፕሪምየር ሊግ ሰርክ የምንመለከተው የመዐዘን ምት አጠቃቀም ችግር በዛሬው ጨዋታ የመጀመርያ አጋማሽ ልይ በጉልህ የታየ ሲሆን በተለይም ፈረሰኞቹ በተደጋጋሚ ያገኟቸውን የማዕዘን ምቶች በማዕዘን ምት መቺዎቹ (አቤል ያለው እና ጋዲሳ መብራህቴ) ኳስን የማሻገር ችግር እና በተጨማሪም የማዕዘን ምቱን ለመሻማት ፍፁም ቅጣት ምት ክልል ውስጥ በከተሙት ተጫዋቾቻቸው የአቋቋም ችግር ምክንያት መዐዘን ምቶቹ ሲመክኑ ለማየት ችለናል።
- ማሰታውቂያ -
በመቐለ 70 እንደርታ በኩል በመጀመሪያው አጋማሽ ይሄ ነው የሚባል ለግብ የቀረበ ሙከራ ባያደርጉም አማኑኤም በመስመር በኩል ሲያደርጋቸው የነበሩት እንቅስቃሴዎች እና ኦኪኪ አፎላቢ በረጅሙ የሚሻገሩ ኳሶችን በመቀበል ለቡድን አጋሮቹ ለማቀበል ሲያደርጋቸው የነበሩት እንቅስቃሴዎች እንደ በጎ ጎን መገለፅ የሚችሉ ናቸው በተጨማሪም ተከላካዮቻቸው የፈረሰኞቹ አጥቂዎች የሚደርሷቸው ኳሶች ስኬታማ እንዳይሆኑ እና ወደ አስራ ስድስት ከሀምሳ ሳጥን ውስጥ እንዳይገቡ ሲያደርጉት የነበረው እንቅስቃሴ ውጤታማ ሆኖ ታይቷል።
ሁለተኛው አጋማሽ እንደተጀመረ ጥሩ የሚባል የማጥቃት እንቅስቃሴ ማድረግ የቻሉት ቅዱስ ጊዮርጊሶች በተደጋጋሚ የመቐለ ግብ መድረስ ቢችሉም በግብ ጠባቂው ፕሪንስ ኦቮና ጥረት ሙከራዎቻቸው ሲመክኑ ነበር። በጨዋታው 55ኛ ደቂቃ ላይ ሰልሀዲን ሰኢድ የመቐለ ተከላካዮች የፈፀሙትን የአቋቋም ስህተትን እና የቦታ አያያዝ ብቃቱን በመጠቀም ከመሀል ክፍል የተሻገረችለትን ኳስ በግራ እግሩ በግሩም ሁኔታ ከመረብ በማሳረፍ ባለሜዳዎቹን መሪ ማድርገ የቻልች ግብ ማስቆጠር ችሏል። ሳልሀዲን ከበርካታ ረጅም ጉዳቶች በውሃላ አሁንም የቅዱስ ጊዮርጊስ የፊት መስመር አልኝታ መሆኑን በዚህች ግብ ማሳየት ችሏል።
ከግቧ መቆጠር በኋላ መቐለዎች ወደ ጨዋታው ለመመለስ እና ግብ ለማቆጠር ብልጭ ድርግም የሚል ጥረት ሲያደርጉ ቢስተዋልም በስልሳኛው ደቂቃ የማስጠንቀቂያ ቢጫ ካርድ የተመለከተው አንተነህ ገ/ክርስቶስ በድጋሚ በሰባ ስድስተኛው ደቂቃ አስቻለው ታመነ ላይ በፈፀመው ጥፋት በቀኑ አልቢትር በአምላክ ተሰማ በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ መውጣቱን ተከትሎ በፈረሰኞቹ የኳስ ብልጫ ተውስዶባቸው ተደጋጋሚ ሙከራዎችን አስተናግደዋል።
በጨዋታው በመስመር በኩል ለመመቐለ ሰብአ እንደርታ ተከላካዮች እራስ ምታት ሆኖ መዋል የቻለው አቤላ ያለው በአንድ ሁለት ጨዋታ ያገኛትን ኳስ በሰማኒያ አምስተኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ በማሳረፍ የባለሜዳዎቹን የግብ ብልጫ በአንድ ከፍ በማድረግ 2-0 እንዲመሩ አስችላል ከግቧ መቆጠር በውሃላም ውጤታቸው አስጠብቀው ለመውጣት ጥረት ሲያደርጉ ማስተዋል ተችሏል።
ከዚህ ግብ መቆጠር በኋላ ተቀይሮ የገባው የመቐለ 70 እንደርታው አሸናፊ ሀፍቱ 92ኛው ደቂቃ ላይ ግብ ማስቆጠር ቢችልም መቐለ 70 እንደርታን ከሽንፈት መታደግ አልቻለም።