በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ14ኛ ሳምንት መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ስታዲዬም ፋሲል ከተማ በኢትዮጵያ ቡና 3ለ2 በተሸነፈበት ጨዋታ ራምኬል ሎክ ተገቢ ያልሆነ ጥፋት አጥፍተሃል በሚል ከሜዳ በቀይ ካርድ መውጣቱ የሚታወስ ነው።
የእግር ኳስ ፌደሬሺኑ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ተጨዋቹ ብር (4000,00)አራት ሺ እንዲከፍልና የ 4 ጨዋታ ቅጣት ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ለተጫዋቹ የተሰጠው ቀይ ካርድ አግባብነት የሌለው መሆኑን በመግለፅ በቁጥር
ፋ/ከ/እ/ክ 444/09 በቀን 15/06/10 ዓ/ም ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባስገቡት የይገባኝ ደብዳቤ መሰረት ጉዳዩን የእግር ኳስ ኳስ ፌዴሬሽኑ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ተመልክቶ በ26/06/10ዓ/ም የእግር ኳስ ፌዴሬሽኑ ለክለቡ በፃፈው ደብዳቤ ራምኬል ሎክ ከተቀጣው የ4 ጨዋታ ቅጣት ላይ 2ቱን ማንሳቱን ገልጿል።
በመሆኑም ተጨዋቹ ከዚህ በፊት ክለቡ ፋሲል ከነማ በሜዳው አርባምንጭ ከነማን 1ለ0 ያሸነፈበት ጨዋታ ያለፈው ሲሆን የ2ኛው ዙር የፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከ ወልዋሎ አ.ዩ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ የሚያልፈው ሲሆን በ17ኛው ሳምንት የሊግ ጨዋታ አፄዎቹ ከሜዳቸው ውጭ በአዲስ አበባ ስታዲዬም ከፈረሰኞቹ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ራምኬል ሎክ ወደ ሜዳ ተመልሶ የቀድሞ ክለቡን የሚገጥም ይሆናል።