THE BIG INTERVIEW WITH SOLOMON MEKONNEN (LUCHO)
በይስሐቅ በላይ
- ማሰታውቂያ -
ሀትሪክ፡- …ዳቦ ተቆርሶ ቤተሰቦችህ
ካወጡልህ ሰለሞን መኮንን ከሚለው ስምህ
ይልቅ ብዘዎች የሚያውቅህ…“ሉቾ”…
በሚለው ቅፅል ስምህ ይመስለኛል…?
ሰለሞን፡- …ትክክል ነህ…ብዙዎች
ከዋናው ስሜ ይልቅ መጥራት የሚቀናቸው
ሉቾ በሚለው ቅፅል ስሜ ነው…(ሳቅ)…
ሀትሪክ፡- …እኔም የብዙዎቹን ስሜት
ተጋርቼ…ሎቾ በሚለው ቅፅል ስምህና
መታወቂያህ ብጠራህ ትፈቅድልኛለህ…?
ሰለሞን፡- …(ሳቅ)…ደስ ይለኛል…
ሀትሪክ፡- …በቅድሚያ እንኳን ደህና
መጣህ ሳልልህ ሌላ ነገር ውስጥ ገባሁ…፤…
ሎቾ እንኳን ደህና መጣህ…ስላገኘሁህና
እንግዳዬ ስለሆንክ ከልብ አመሰግናለሁ…?
ሰለሞን፡- …እናንተም እንኳን ደህና
ቆይችሁኝ…፤…በህትመት ሚዲያም
የመጀመሪያ እንግዳ አድርጋችሁ ከረዥም
አመት በኋላ እድሉን ስለሰጣችሁኝ እኔም
ከልብ አመሰግናለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …ወደ ሀገር ቤት የመጣኸው
ከረዥም አመት በኋላ ነው ልበል…ሉቾ…?
ሎቾ፡- …አዎን…!…ጊዜው እንዴት
ይሮጣል መሰለህ…፤…ከ17 አመታት
የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ነው ወደምወዳት ሀገሬ
የመጣሁት…(በደስታ ስሜት ውስጥ ሆኖ)…
ሀትሪክ፡- …በጣም ደስ ይላል…17…
አመት…?…በጣም ረዥም ጊዜ ነው…ልክ
ኢህአዲግ ደርግን ጥሎ ስልጣን ለመጨበጥ
የወሰደበትን የትግል ጊዜ ያህል…ማለት…?
ሎቾ፡- …(በጣም ሣቅ)…እኔ እንኳን
ቆይታዬን በዚህ ደረጃ አለካሁትም…አስቤውም
አላውቅም… (አሁንም ሣቅ)…ግን እንዳልከው
ረዘም ያለ ጊዜ ነው ከሀገሬ ከወጣሁ…፡፡
ሀትሪክ፡- … በኢትዮጵያዊያን የስፖርት
ፌስቲቫል ላይ ለመካፈል ሄደህ ነው
የቀረኸው…?
ሎቾ፡- …በ2ዐዐ2 በፈረንጆች አቆጣጠር…
ጓደኞቼ የግብዣ ወረቀት ልከውልኝ ሄጄ ነው
በዛው የቀረሁት…፡፡
ሀትሪክ፡- …በጨዋታ ዘመንህ ታላላቅ
ስም ያላቸው…ለአንተ በጣም ቅርብ
የሆኑ ተጨዋቾች ሲጠፉ አንተ ተለይተህ
የምትታወቀው ባለመጥፋት ስለነበር በወቅቱ
ሄደህ በመቅረትህ ብዙዎች ተገርመዋል…
እንዴት ያኔ ሳትወስን በ2ዐዐ2 ልትወስን
ቻልክ… ?
ሎቾ፡- …የሚገርምህ ነገር ብዙ
ተጨዋቾች እየጠፋ እኔ እየሸኘው ስመለስ…
ምን አሉኝ መሰለህ…“…ሎቾ ዋልያ ነው
ከሀገሩ ውጪ ሌላ ሀገር መኖር አይችልም…”
ብለው ይተርቡኝ ነበር፤ እንዳልከው ብዙ
ተጨዋቾች ጓደኞቼ ሲጠፉ እኔ እመለሳለሁ፡
፡ በአሁኑ እንኳን ሎቾ አይመለስም ይጠፋል
ብለው ሲጠብቁ እኔ እመለሳለሁ፡፡ ብዙዎች
አለመጥፋቴን ከፍርሃት ጋር ያያይዙታል፤
እኔ ግን ፍርሃት አይመስለኝም፤ደፍሮ
መወሰን አለመቻል ይመስለኛል…፡፡
ሀትሪክ፡- ..ታዲያ አሁን እንዴት…
ደፍረህ ለመቅረት ወሰንክ…?…ሀገሪቷ
አሜሪካ ስለሆነች ነው…?
ሎቾ፡- …(በጣም ሣቅ)…በፍፁም
አይደለም…የሚገርምህ በ2ዐዐ2 እዛው
ከመቅረቴ በፊት አሜሪካ የመሄድ እድል
አግኝቼ ነበር፤ስሄድም ብዙዎች አይመለስም
ቢሉም…የሰው ግፊቶች ቢኖሩብኝም… ሶስት
ነው አራት ወር አካባቢ እረፍት አድርጌ
ተመልሼያለሁ፡፡ በ2ዐዐ2ትም ተጋብዤ ስሄድ
ለሰከንድም ቢሆን እዛው እቀራለሁ ብዬ
አላሰብኩም፡፡ አሜሪካ ስደርስ የተቀበሉኝ
ጓደኞቼ ናቸው…ሱልጣን ገ/ህይወት የሚባል
ጓደኛ አለኝ፤እሱ “…ሎቾ የፈለገ ይሁን ከዚህ
በኋላማ አትመለስም…፤…እዚሁ ቀርተህ
ሰርተህ ትኖራለህ…”…ብሎ በጣም ፎክሮ…
ተዘጋጅቶ ጠበቀኝ…።…ከእሱ ሌላ ውብሸት
የሚባል ጊዮርጊስ ይጫወት የነበረ፣አበበ
የVoA ጋዜጠኛ፣የቅዱስ ጊዮርጊስ ደጋፊ
የነበረችው ከበቡሽ፣እህትዋ ሰናይትና የባለቤቴ
ወንድም ሆነው “…መመለስ የለበትም…”
ብለው ከመመካከር አልፈው የህግ ባለሙያ
ይዘው ጠበቁኝ…፤…ኧረ በፍፁም…እኔ ወደ
ሀገሬ እመለሳለሁ ብል…ማን ሰምቶኝ…በቃ
ጨቅጭቀው… አሳምነው…አስቀሩኝ…።…
እኔም ነገሮች ከአቅሜ በላይ ሲሆኑ ልጄ
የተሻለ የትምህርት እድል እንዲያገኝ
ይረዳዋል ብዬ ውስጤን አሳምኜ ሣልዘጋጅና
ለመቅረት ሳላስብ የዛሬ 17 አመት በዚህ
መንገድ አሜሪካ ገብቼ ቀረሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …አሜሪካስ እንዴት
ተቀበለችህ…?
ሎቾ፡- …የሚገርምህ ነገር ከምጠብቀው
በላይ ሁለት እጆቿን ዘርግታ ነወ የተቀበለችኝ
ብል ይቀለኛል…፤…አንድ አመት ያህል ስራ
የሚባል ነገር ሳልሰራ ምንም ሳይጎድልብኝ
ነበር የኖርኩት፡፡ በየስቴቱ እየተጋበዝኩ ስሄድ
ሁሉም የሚሰጠኝ ፍቅር ቆይታዬ መጥፎ
እንዳይሆን አድርጎታል፡፡ ሰው ፍቅሩን ካለው
ላይ ገንዘቡን እያነሳ ለእኔ ያለውን ክብርና
ቦታ በተለያየ መንገድ ይገልፅልኝ ነበር፤በጣም
የሚገርምህ ሰው “…ሎቾ አንተማ ጀግናችን
ነህ…፤…በጣም እንወድሃለን…”…እያለ
ገንዘቡን ፍቅሩን ያውም በሰው ሀገር
ያለስስት ሲሰጠኝ…አንዴ ይሄን ያህል…እኔ
ለሀገሬ፣ለቅ/ጊዮርጊስ ምን ሰርቼ ነው…?…
ይሄ ሁሉ ክብርና ፍቅር…?…እያልኩ
ራሴን እጠይቅ ነበር…፡፡…ዛሬ ላይ ሆኜ
ሳስበው የሚገርመኝ…ሰው ከፍቅሩ በመነጨ
የሚሰጠኝ ገንዘብ ከራሴ አልፎ ወደ ሀገር
ቤት ሁሉ እልክ ነበር…፤…ልብ በል…
ገንዘብ የምልከው ገና ስራ ሣልጀምር ነው፡
፡ በመሀል ደግሞ ነፍሱን ይማረውና ዘላለም
ተሾመ (የድሮ የኤልፓ ተጨዋች) አትላንታ
ላይ የውስጥ ውድድር አዘጋጅተው ነበር
የክብር እንግዳ አድርጎ ምን የመሰለ ሆቴል
ይዞ ጋበዘኝ፤የተለየ ፍቅርም ስጡኝ፡፡ ለሌላው
የክብር እንግዳ እንደሚደረገው ለእኔም በክብር
እንግድነቴ ገንዘብ አዋጥተው ሰጡኘ፤ብቻ
ምን ልበልህ የተለየ የደስታ አለም ውስጥ
ገብቼ አሳለፍኩ፡፡ አትላንታ በርካታ የሀገራችን
ታዋቂ ተጨዋቾችና ሰዎች የሚገኙባት
ከተማ ናት፤እርስ በርሳቸው
በጣም ይፋቀራሉ፡፡ እነሱ
በዘሩብኝ ፍቅር አትላንታን
ልክ ሁለተኛ ሀገሬ ያህል ነው
የማያት፤ከእነ ዘላለም፣ ኃይሌ
ኳሴ፣ አፈወርቅ፣ ጎላ፣ ክፍሉ
መብራቱና ከሌሎች ጋር
የማይዘነጋ ጊዜን በማሳለፍ
አሜሪካንን በቀላሉ መላመድ
ችያለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …የአሜሪካውን
ነገር ለጊዜው ገታ እናድርገው
እስቲ…ሎቾ ከ17 አመታት
በኋላ ነውና የመጣኸው አዲስ
አበባን እንዴት አገኘሃት…?
ሎቾ፡- …ኡ…በጣም
ተለውጣለች…(ፊቱ ላይ
የመገረም አይነት ስሜት
እየታየበት)…ብዙውን ጊዜ
አሜሪካን አገር ስትኖር
ኢንፎርሜሽን (መረጃ)
ትሰማለህ…ግን በአይንህ
እስካላየህ ድረስ እርግጠኛ
አትሆንም፤ እዚህ ከመጣሁ
በኋላ ያየሁት አዛ እያለሁ
ስሰማው ከነበረው በላይ ነው፡
፡ ከተማው ተለዋውጧል…
በጣም ብዙ ፎቆች በየቦታው
ታያለህ…መንገዶች ሁሉ ተቀያይረዋል…
ከ17 አመት በፊት እንደ ልቤ ስጋልብባት
የነበረችው ከተማ ዛሬ ተቀይራ በቀላሉ
መልመድ አቅቶኛል…፤…አሁን እንደውም
ትንሽ እሻላለሁኝ…እንደመጣሁ በተለይ
መንገዶችን ማወቅ አቅቶኝ ነበር፡፡ አዲስ
አበባ በሰውና በመኪና በጣም ተጨናንቃ ነው
ያገኘኋት…ሰውም ተለውጧል፤…በአጠቃላይ
አዲስ አበባ በፎቅ ተወራ በመንገዶች አምራ
ተለውጣ ነው ያገኘኋት…በዚህም በጣም ደስ
ብሎኛል…፡፡
ሀትሪክ፡- …በርካታ ታዋቂ ተጨዋቾችን
ያፈራችው ለሀገርን ወይም የትውልድ ሰፈርህ
ጨርቆስን ከ17 አመት በኋላ ተመልሰህ
ስታያት እንዴት አገኘሃት…?
ሎቾ፡- …ወደ ሠፈሬ የመጣሁት በከፍተኛ
የሐዘን ድባብ ውስጥ ሆኜ ነው…ወላጅ አባቴን
በጨካኝ ሞት ተነጥቄ ስለነበር በተሰበረ
የሐዘን ስሜት ውሰጥ ሆኜ ነው የመጣሁት፡
፡ ሐዘኔን እርሜን ለማውጣት ወደ ጨርቆስ
ሄጃለሁኝ…የአባቴ ሐዘን ለጨርቆስ ያለኝን
ናፍቆት ቢሻማኝም የሰው ያህል ስትናፍቀኝ
የነበረውና ለማየት የልጅነት ትዝታዬን ወደ
ኋላ ተመልሼ ለማስታወስ በጣም ጓጉቼ
ነበር የመጣሁት፡፡ በችግርዋ ውስጥ ውበትዋ
ደምቃ የምትታየው፣በድህነትዋ ውስጥ
ፍቅር፣ መቻቻልና መተሳሰብ የሚታይባት
ጨርቆስን የዛሬ 17 አመት ትቼያት
እንደሄድኩት አላገኘኋትም፡፡ መንደሩ፣ሠፈሩ
ተለዋውጧል…በጉስቁልናዋ ውስጥ ፈክቶ
የሚታየው የድሮ ውበትዋን አላገኘሁትም፤
ምክንያቱም ግማሹ ሠፈር ፈራርሷል…
ግማሹ ደግሞ ሌላ ቤት ተሰርቶባታል…ሌላው
ይቅር ብዙ ተጨዋቾችን ያፈራው ከቡፌ
ዳ ላጋር ጀርባ ያሉትን ሜዳዋች ለማየት
እድል አላገኘሁም፡፡ የድሮ ሰው ብዙም
የለም…ግማሹ ህይወቱ አልፏል…ግማሹ
መሰብሰቢያውን ቀይሯል…አዳዲስ ሰዎች
ተተክተዋል፡፡ ያም ቢሆን ወንድሞቼን…
አንዳንድ የድሮ ጓደኞቼንና አባቶችን አግኝቼ
ትናንትን ለማስታወስ ሞክሬያለሁ፡፡
ሀትሪክ፡-አንተ ተወልደህ ባደክበት ብዙ
ስም ጥር ሰዎችን ያፈራው የጨርቆስ አካባቢ
ቡድን ተመስርቷል፤የሰንሻይን ባለቤት አቶ
ሳሙኤልን የመሳሰሉ ባለሀብቶች ድጋፍ
እያደረጉለት እንደነበር አውቃለሁ…ይሄንን
ትውቃለህ…?
ሎቾ፡- …ከአንተ ገና መስማቴ ነው…፤…
ግን ሃሳቡ በጣም የሚደገፍና ትልቅ ነገር
ነው፤ ምክንያቱም የእኛ ሠፈር ለእግር
ኳሱ ትልቅ ውለታን የዋለ አካባቢ በመሆኑ
ዳግም የሚጠናከርበትን መንገድ ለመፍጠር
እንቅስቃሴ መጀመራቸው በተለይ እንድ
አቶ ሳሙኤል ታፈሰ አይነት ሰው ደግሞ
ከጀርባ ሆኖ ማገዛቸው፤ የጨርቆስን ታሪክ
ለመመለስ ቁልፉ ሚና ይኖረዋል፡፡ የሰንሻይን
ባለቤት ለኳስ የተለየ ፍቅር ያለው ሰው
በመሆኑ በዚህ ደረጃ መገኘቱ ከማስደሰት
ውጪ አልገረመኝም፡፡ ምክንያቱም ሳሙኤልን
ከድሮ ጀምሮ ነው የማውቀው… እንዴት
እዚህ እንደደረሰም አውቃለሁ፤ሣሙኤል
ወደ ስታዲየም ከመሄዱ በፊት በሠፈር
በኩል ሲያልፍ የእኛን ጨዋታ ተመልክቶ
ነው፡፡ የሰንሻይን ባለቤት አቶ ሳሙኤል ዛሬ
የደረሰበት ትልቅ ደረጃ ከመድረሱ በፊት በብዙ
ውጣ ውረዶች ውስጥ አልፏል፡፡ ያልሠራው
ስራ የለም ስታዲየም መኪና ይጠበቅ ነበር…
ስታዲየም ያፀዳል…ጋሼ ይዘውኝ ግቡ እያለ
ጨዋታ ይከታተልም ነበር፡፡ ደስ የሚለው
ነገር ሣሙኤል በትናንት ማንነቱ የሚያፍር
ባለመሆኑ ይሄ እኔ የምለውን እሱ ራሱ
በኩራት ሲናገረው ነው የምትሰማው፡፡ እኛ
ብ/ቡድን ደርሰን ልምምድ ስንሰራ የስታዲየም
ጣሪያ እድሳት ሲሰራ የሠፈሬ ሰው ስለሆነና
ስለምንግባባ በመሰላል ወጥቼ አወራው ነበር፡
፡ በጥረቱ፣በልፋቱ እዚህ የደረሰ ነው…ዛሬ
እዚህ ደረጃ ደርሶ ሣየው ከእሱ በላይ እኔ
እኮራለሁ…ምክንያቱም አንደኛ የጨርቆስ…
የሠፈሬ ልጅ ከምንም ተነስቶ ትልቅ
በመሆኑ… ሁለተኛው ደግሞ የጨርቆስን
ጉሌት የምናውቅ እናውቀዋለን…ከመጣሁ
በኋላ ሳየው ግን በጣም ተደስትኩ…በዚያ ላይ
የቅ/ጊዮርጊስ ቅልጥ ያለ ደጋፊ ነው፡፡ አንዴ
እንደውም ሲናገር የሰማሁት ስታዲየም ዙሪያ
መኪና ሲጠብቅ ጊዮርጊስ ካሸነፈ ከተመልካቹ
እኩል ቁጭ ብለን 5 ደቂቃ ሲቀረን እንወጣና
የጠበቅንበትን እንቀበላለን…ከተሸነፈ
ግን ደጋፊው ተናዶ መኪናውን አስነስቶ
ስለሚወጣና ስለሚያመልጠን ቀድመን
ወጥተን ነው የምንጠብቀው ብሎ ተናግሯል፡
፡ ሰው ከትንሽ ነገር ተነስቶ አንቱ ሲባል
በዚያ ላይ የትናንት ማንነቱን የምታውቀው
ከሆነ ከሰው በላይ የምትኮራው አንተ ነህና
የሣሙኤል ህይወት ለብዙ ሰው ትምህር
የሚሆን ነው፡፡
ሀትሪክ፡- .. በታዳጊነትህ ለቅዱስ ጊዮርጊስ
ሲ ቡድን በመጫወት ነው ወደ ክለብ እግር
ኳስ ጎራ ያልከው…?
ሎቾ፡- …ለገሀር የእግር ኳስ ሠፈር
ነው…በርካታ ታዋቂ ተጨዋቾችን ያፈራ
ሜዳም ነው፤ እኛም በህፃንነታችን ከዚህ ሜዳ
ተለይተን አናውቅም ነበር፡፡ ታዲያ አንድ
ጊዜ በዚህ ሜዳ ወደ አምስት ነው ስድስት
የሠፈር ቡድኖች ውድድር እናድርግ ነበር፡
፡ ዋንኬ ሰፈር፣ ድንጋይ ጣቢያ፣ ፖሊስ
ሠፈርና… የሚባል መጠሪያ የነበራቸው
ቡድኖች ነበሩ፤ሁሌም ውድድር እናደርግ
ነበር፡፡ የእኛ ቡድን ዋንኬ ሰፈር የሚባል
ነበር፤የሚያስለጥን ደግሞ ኑሬ የሚባል
የድሮ የጉምሩክ ተጭዋች የነበረ ነው፡፡
ኑሬ የጌታቸው አብዶ ጓደኛ ነው…ብ/ቡድን
ድረስም አብረው ተጨውተዋል፤ ጊዮርጊስም
ሲገቡ አብረው ነው የገቡት…ኑሬ ሰፈር
ውስጥ የእኛን ቡድን ሲያሰለጥን ጌታቸው
አብዶ አይቶ ወደ 6 የምንሆን ተጨዋቾችን
መርጦ ለአቶ ይድነቃቸው ሰጣቸው…አቶ
ይድነቃቸው ተሰማም አቶ ታደለ መለሰ
የሚባል የክለቡ ሰው ነበር “በል እነዚህን
ልጆች መዝግበህ ያዛቸው ?” አሉት…
መዘገበን…የተመዘገብነው ወዲያው ለቅዱስ
ጊዮርጊስ ሲ ቡድን እንድንጫወት ሣይሆንከአድና ሁለት አመት በኃላ ይደርሳሉ በሚል
ነበር፡፡ ቆይተው ግን እንድንጫወት ሣይሆን
እንድንገባና እንድንወጣ ቲሴራ ተሰጠን፡
፡ መጀመሪያ ከነበርነው 6 ልጆች
መሀል አብዛኞቹ እየወጡ መጡ…
እኔ ቀጠልኩበት…፡፡
ሀትሪክ፡- ለ ሲ ቡድን
ስትጫወቱ ክፍያ ነበረው….?
ሎቾ፡- …እኛ የዚህን ታላቅ
ክለብ ማልያ ስለመልበስ እንጂ
ስለ ክፍያ አስበንም አናውቅም…
ስንት ይከፈለናል ብለን ተነጋግረንም
አናውቅም…፤…የክለቡን ማልያ
መልበስ በራሱ ከክፍያም በላይ ነው…
ግን የክለቡ ኃላፊዎች ልምምድ
ሠርተን ስንጨርስ 3ዐ ሳንቲም ይሰጡን
እንደነበር አስታውሳለሁ…(ሳቅ)…
ሀትሪክ፡- …ሰንት…?… 3ዐ
ሣንቲም ነው ያልከኝ…?
ሎቾ፡- …ምነው
ተገረምክ…?
…አዎን
ትሬይኒንግ
ሰርተን
ስንጨርስ
ለአውቶብስ
መሣፈሪያ
ብለው 3ዐ ሳንቲም
ይሰጡናል…፤ …
ቡድኑ የህዝብ
ሀብታም እንጂ…
የንዘብ ሀብታም
ስላልሆነ 3ዐ
ሳንቲሟ አንዳንዴ
ቀንሷ…አንዳንዴ
ደግሞ እሷ
ራሷ በወቅቱ
የማትከፈለን ጊዜ
ነበር፡፡ 3ዐ ሳንቲሟ
ትቀነስና ወደ 15
ሳንቲም ወርዳ
ትከፈለን ነበር…
ባስ ሲል ደግሞ 15
ሳንቲሟም እራስዋም
ትቀርና በሚቀጥለው
ከምትሰጠን 3ዐ ሳንቲም
ጋር ተደምራ 45
ሳንቲም ሆና ትሰጠን
ነበር፡፡
ሀትሪክ፡- …ግን
እናንተ በምታገ ኙት
3ዐ ሳንቲም ተደስታችሁ
ነበር የምትጫወቱት…?…
ገንዘቡንስ በትክክል
ለትራንስፖርት ታውሉት
ነበር…?
ሎቾ፡- …(ሣቅ) …
በጣም ተደስተን ነበር
የምንጫወተው…
ከላይ ነገርኩህ እኮ…
እኛ የሚሰጠንን
ገንዘብ ለሰከንድም
አናስበውም…
የጊዮርጊስ ተጨዋች
መባል ማልያውን
መልበስ በራሱ
ከገንዘብ በላይ
ነው፤ በገንዘብም
አይተመንም፡
፡ ደግሞም በሰዓቱ
በምትሰጠን 3ዐ
ሣንቲም ተደስተን…
ተንቀባረን ነበር
የምንኖርባት…
ከእኛ በላይም ጌታ
አልነበረም…፤…ትዝ
ይለኛል…ልምምድ
የምንሰራው
ሴንጆሴፍ ት/ቤት
ውስጥ ነበር…
ልምምድ ጨርሰን 3ዐ ሳንቲሟን
ተቀብለን ወደ ት/ቤት ስንሄድ
ሴንጆሴፍ አካባቢ ህብስት የሚባል
ፓስቲ (ጮርናቄ) መሸጫ ቤት
አለ…እዛ ቤት ገብተን ሁለት
የሰማይ ስባሪ የሚያክል ፓስቲን
ከሻይ ጋር ገምጠንበት ነበር
ወደ ት/ቤት የምንሄደው፡፡ በዚህ
በጣም ደስተኞች ከመሆችን
የተነሣ የሰራነው ማክሰኞ ከሆነ
ሐሙስ ምነው ቶሎ በደረሰ ብለን
እስከመመኘትም እንደርስ ነበር…
(ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …ሐሙስ በደረሰ
የምትሉት ለትሬይኒንግ ነው…?
ሎቾ፡- …ወይ አንተ ቀልደኛ
ነህ…!…የፓስቲ (ጮርናቄ) ሱስ
ይዞን ነው እንጂ…(በጣም ሣቅ)…
ትሬይኒንጉ ብቻ ሣይሆን እሱን
ሠርተን ስንጨርስ በምትሰጠን
3ዐ ሳንቲም ጮርናቄ (ፓስቲ)
ለመግመጥ ነው እንጂ…(ሣቅ)…
እዚህ ላይ አንድ ነገር ሳልነግርህ
ረሣሁት…3ዐ ሳንቲም የሚሰጠን
በልምምድ ወቅት ነው…ጨዋታ ባለ ቀን
ደግሞ 3ዐ ሳንቲሟ በጣም ታደጋለች…
(ሣቅ)…
ሀትሪክ፡- …ወደ ስንት…?
ሎቾ፡- …ጨዋታ ባለን ቀንማ
እንደ እኛ ሀብታም የለም…
በልምምድ ቀን የምትሰጠን 3ዐ
ሣንቲም በከፍተኛ ፍጥነት ወደ 5ዐ
ሳንቲም ትመነጠቃለች…በጨዋታ
ቀንማ ማንም የሚችለን የለም፡
፡ እንደ እኛ አይነት ሀብታምም
በከተማው ፈልገህ አታገኝም…
(ሳቅ)…ዋንጫ ካነሳን ደግሞ
ተወው…(በጣም ሳቅ)…
ሀትሪክ፡- …
ዋንጫ ካገኛችሁ…ምን…
ይደረግላችሃል…?
ሎቾ፡- …ዋንጫ
ስንበላ ከፓስቲ (ከጮርናቄ)
እ ን ገ ላ ገ ላ ለ ን… ( ሳ ቅ )… አ ን ድ
ጊዜ ዋንጫ በልተን ሁሉም
በጣም ተደሰተ…ጉድ ተባለ…ዋንጫ
አግኝተውማ ዝም ማለት የለብንም
አንድ ነገር እናድርግላቸው ተባለና…
“ፀሐይ ምግብ ቤት” የሚባል ምግብ
ቤት ለገሀር አካባቢ አለ…እዛ
ወስደው…ተወው በቃ ይሄን ምግብ
ወረደንበት…(ሣቅ)…ዛሬ ላይ ይሄንን
ስትሠማ ልትስቅ ትችላለህ…እኛ
ግን በወቅቱ ልዩ የደስታ ስሜት ነበር
የሚሰማን፡፡ ከማልያው በስተቀር ስለሌሎች
ነገር አስበን አናውቅም፡፡
ሀትሪክ፡- ሎቾ አንተ የቅዱስ ጊዮርጊስ
ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱም ስም ያለህ ትልቅ
ተጨዋች ነህ፤ ዛሬ የፊርማ ገንዘብ በመቶ
ሺዎች የሚከፈልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል
በጨዋታ ዘመንህ የፊርማ ገንዘብ አግኝተህ
ታውቃለህ….
ሎቾ፡- …የፊርማ…?…አንተ ቀልደኛ
ሰው ነህ…እኔ የፊርማ የሚባል ገንዘብ
አግኝቼ አላውቅም…ራሱ ፊርማን የማውቀው
ሳገባ የተፈራረምኩትን ብቻ ነው…(በጣም
ሣቅ)…አንድም ቀን የፊርማ ገንዘብ የሚባል
ሳልቀበል ነው ከጨዋታ አለም የተለየሁት…
(ሳቅ)…
ሀትሪክ፡- …ወደ ዋናው የቅ/ጊዮርጊስ
ቡድን መቼ ገባህ…?…በወቅቱስ ምን ትሰ
ማህ…?
ሎቾ፡- …የእግዚብሔር ነገር ሆኖ
ሲ ቡድን ውስጥ ብዙ አልቆየሁም…፤…
ትንሽ እንደተጫወትኩ በ197ዐ ዓ.ም አካባቢ
ይመስለኛል…ወደ ዋናው ቡድን አድኩ…
“ወደ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን አድገሃል”
ስባል የተሰማኝን ስሜት በቃላት ልገልፅልህ
አልችልም…ማደጋችን አውነት ቢሆንም
የህልም ያህል ሁሉ ይመስልሃል…አምነህ
መቀበልም ያቅተሃል…፤…የዚህ ታላቅ
ክለብ አካል መሆን የሚሳካ ሁሉ
ስለማይመስልህ ተሳክቶ እንኳን
ባለማመኔ በመጠራጠሬ እውነት እኔ
ወደ ጊዮርጊስ ዋናው ቡድን አደኩ ብዬ
የጠየኩበት አጋጣሚ ሁሉ ነበር…
ከእኛ በፊት ክለቡ ውስጥ ያሉ
በስም የምናውቃቸው ተጨዋች
ጋር አብረህ የምትጫወትበት
እድል መፈጠሩ በራሱ
ለማመን እንድትቸገር ሁሉ
ያደርግሃል፡፡ ወደ ዋናው ቡድን እንድናድግ
የሲ ቡድን አሰልጣኛችን የነበረው ተስፋዬ
ሰለሞን እገዛ በጣም ከፍተኛ ነበር፡፡
አሰልጣኞችን ተስፋዬ ሲያሰለጥነን በሜዳ
ትሬይኒንግ ብቻ ሳይሆን በሽት (ወረቀት)
ፕሪንት አድርጎ ለእያንዳንዳችን አባዝቶ
ይሰጠን ነበር፡፡ የምንሰራው ልምምድ ምን
እንደሆነ ጥቅሙን ፕሪንት አድርጎ እየሰጠ
ስለምንሰራው ትሬይኒንግ በወረቀት ጭምር
ያስረዳን ነበር፡፡ ሲ ቡድን ሆነህ ያውም
በዚያ ዘመን በዚህ ደረጃ አስበኸዋል? እኔ
ሁሌም ሲገርመኝና በጣም ሳደንቀው የምኖር
አሰልጣኝ ነው፡፡ በአሁን ሰዓት አይደለም ለሲ
ለዋናው ቡድን እንዲህ የሚያደርግ አሰልጣኝ
አለ?አላውቅም…ተስፋዬ ግን ለጊዮርጊስ ሲ
ቡድን ስንጫወት ይሄን አድርጓል…፤…ለዚህ
አሰልጣኝ እውነቴን ነው የምልህ ትልቅ ክብር
አለኝ፡፡
ሀትሪክ፡- …ቅዱስ ጊዮርጊስን ወክለህ
ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኡጋንዳ ሄደህ “ተቀይረህ
ግባ” ስትባል እምቢ ብለሃል…የሚል ነገር
ሰማሁ እውነት ነው…?
ሎቾ፡- …(ሳቅ).. አዎን እውነት ነው…!…
ገና የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች መሆኔ
እንደተረጋገጠ ለመጀመሪያ ጊዜ ለክለብ
ሻምፒዮና የሄድነው ወደ ኡጋንዳ ነው…፤…
እንኳን መጫወት ለጨዋታ አብሬያቸው
መሄዴ በራሱ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው፡፡ ይሄንን
ቡድን የሲ በድን አሰልጣኛችን የነበረው
ተስፋዬ ሠለሞን ቡድኑን ይዞት እንዲሄድ…
ስዩም አባተ (ነፍሱን ይማረውና) እንዲሁም
አስራት ኃይሌን የእሱ አማካሪ አድርገዋቸው
አብረው ሄደዋል…እኔ በወቅቱ ቤንች ላይ
እንድቀመጥ ተደረገ፡፡ በኋላ ላይ አሰልጣኛችን
ተስፋዬ ጥላሁንን መሠለኝ ለመቀየር ፈልጎ
“ሎቾ ተነስ ቀይረና ግባ” ሲለኝ የሰማሁበትን
ጆሮዬን ተጠራጥሬ…እ… እኔን… ው…?
ስል “…አዎን አንተን ነው ቀይር…” ሲለኝ
ደግሞ…አረ እኔ አልቀይርም…እኔ አልገባም…
አልኳቸው…
ሀትሪክ፡- …ለምን ፈርተህ ነው…?
ሎቾ፡- …እንዴ ምን ማለትህ ነው…!…
በጣም ያስፈራል…እኮ…ምክንያቱም እኔ ገና
ነኝ…ከእኔ በላይ ስምና ትልቅ ችሎታ ያላቸው
ሲኒዬር ተጨዋቾች አሉ….እንዴት እነሱን
ቀይሬ እጫወታለሁ…?… የሚል ስሜት
በውስጤ ፍራቻ ፈጥሮ ነው እምቢ ያልኩት
እንጂ የአሰልጣኙን ትዕዛዝ ባለማክበር
አይደለም፡፡ በዚህ ቡድን ውስጥ ጌታቸው
ዱላን የመሳሰሉ ትላልቅ ተጨዋቾች አሉ…
የምታደንቃቸው፤… ያ ነው ያስፈራኝ…።…
በጣም የሚገርምህ ኡጋንዳ ላይ ያደረግነውን
ጨዋታ በአቻ ውጤት ብናጠናቅቅም ምን
አይነት ልዩ ጨዋታ መሰለህ የተጫወትነው…
በተለይ ጌታቸው ዱላ ልዩ ነበር፤ጌታቸው
ዱላን እያየሁት ነበር ያደኩት…ስለ እሱ
ችሎታም ብዙ ሲባል እሰማም ነበር…ኡጋንዳ
ላይ በነበረው ጨዋታ ያየሁት የጌታቸው
ዱላ ብቃት ግን እውነትም የተለየ ግብ ጠባቂ
እንደነበር ያረጋገጥኩበት…ይበልጥ ችሎታው
ጎልቶ ወጥቶ ያደነኩት በዛን ቀን ነበር፡፡
ሀትሪክ፡- …ከዚህ ጨዋታ በኋላ በወቅቱ
የሀገሪቱ መሪ የነበሩት ኢዲያሚን ዳዳ
ግብዣ አድርገውላችሁ ነበር? እስቲ እሱን
አስታውሰህ አጫውተኝ…?
ሎቾ፡- …በጣም የሚገርም ትልቅ ግብዣ
ነው ያደረጉልን…ኢዲያሚን ዳዳ…፤…
ፕሬዚዳንቱ ቪክቶሪያ ኃይቅ ወስደው ከልባቸው
ነበር የጋበዙን፡፡ እኛ በመርከብ ቀድመን
ሄደን ቪክቶሪያ ኃይቅ ላይ ወርደን እሳቸው
መሀከላችን እንዲቆሙ ተመቻችቶላቸው
ኢዲያሚን ዳዳ ግን “በፍፁም እዚህ ነው
የምቀመጠው” ብለው የአንድ ሀገር ትልቅ
መሪ መሬት ላይ ተቀምጦ ከእኛ ጋር ፎቶ
መነሣቱን አስታውሳለሁ፡፡ ያ አጋጣሚ ሁሉም
ነገር ለእኔ የመጀመሪያ ነው…የመጀመሪያ
ያየሁት ሀገር፣ የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል
ጨዋታ፣ ከመሪ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ አብሬ
ፎቶ የተነሣሁበት ልዩ አጋጣሚ ነበር።
ብቻ ለእኔ ሰውም፣ ሀገሩም፣መሬቱም ሌላ
ነገር ነው የሆነብኝ፤የማይረሣ ልዩ ስሜት
የፈጠረብኝ አጋጣሚ ነው፡፡
ሀትሪክ፡-ቅዱስ ጊዮርጊስ በመዋቅር
የተነሣ ሲፈርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለማስታወስ
በተቋቋመው የትግል ፍሬ ቡድን ውስጥ
እንድትጫወት ስትጠየቅ እምቢ ማለትህ
እስከአሁን ብዙዎች መልስ አላገኙለትም…?
ሎቾ፡- …እምቢ አላልኩም…የነበረው
ሁኔታ ስለማይፈቅድ ነው…፤…የነበረው
የውድድር ቅርፅ ነው እንዳልጫወት ያደረገው
እንጂ እኔ አልጫወትም ብዬ አይደለም…።…
ምክንያቱም በወቅቱ የኢንዱስትሪ ማህበራት
ለ3 ተከፈሉ…እኔ ፊያት ካምፓኒ ስለምሠራ
ለእርምጃችን ተመደብኩ እንጂ እምቢ ብዬ
አይደለም፤እንዳልከው ትግል ፍሬ ብጫወት
ደስ ይለኛል።ፊያት ካምፓኒ ስለምሰራ ግን
የውድድሩ ቅርፅ አይፈቅድልኝም…የእኔም
ፍላጎትም ትግል ፍሬ ነበር፡፡ ምክንያቱም
ማልያው የጊዮርጊስን ታሪክ የሚያስታውስ
ነው…ለዛ ክለብ የሚጫወቱና አመራሮቹ
በልብ ውስጥ የV ምልክት አለ ይሉ ነበር፡፡
ሀትሪክ፡-…ሌላ አንድ ነገር ሰምቼ ደግሞ
በጣም ተገርሜያለሁ…ሎቾ ለቅዱስ ጊዮርጊስ
ተጨዋች ብቻ አይደለም ክለቡ ከፈረሰ በኋላ
አቋቁሞ ለዚህ ያደረሰው እሱ ነው…የሚል
አዲስ ታሪክ ሰምቼ ተገርሜያለሁ እውነት
ነው…?
ሎቾ፡- …አዎን ትክክል ነው…ቅ.
ጊዮርጊስንም እንደገና በማቋቋም ሌላ ገፅታ
ያለው ታሪክ አለኝ…50 ክለቦችን በአዲስ
በማዋቀር የውድድር ፎርማት ሲዋቀር
የጊዮርጊስን ስም ለመመለስ ከደከሙት ውስጥ
አንዱ ነኝ…፤…እኔ በዚያን ወቅት ፊያት
ካምፓኒ ነበር የምሰራው…ሁሉም ክለቦች
እንደ አዲስ ሲቋቋሙ ባቡሩንም በአዲስ መልክ
ለማቋቋም እንቅስቃሴ ተጀምሯል…፤…
በዚህን ጊዜ ባቡርን የማቋቋም ትልቅ ኃላፊነት
የተሰጠውና እዚያው ባቡር ውስጥ የሚሰራው
አቶ ተሾመ የሚባል ሰው እኔን እንዲያነጋግር
ተመደቦ የምሠራበት ድረስ መጣ፤ እንዴ
እዚህ ምን ትሠራለህ ስለው “…ሎቾ አንተን
ለማነጋገርና ለመለመን ነው የመጣሁት…”
አለኝ ምነው በሠላም ስለው “…የምሰራው
ባቡር ነው…ግን ጊዮርጊስ እንዲቋቋም
እፈልጋለሁ ለዚያ ላናግርህ ነው…”ሲለኝ
ወዲያውኑ ከአፉ ላይ ነጥቄው አይ ጋሽ ተሾመ
ጊዮርጊስ እንዲቋቋም ከአንተ በላይ የምፈልገው
እኔ ነኝ ስለው ተደስቶ “…በቃ እንደዚህ ከሆነ
ለምን አንድ ነገር አናደርግም…” አለኝ…፡፡
ወዲያው ኮሚቴ ተቋቋመ ክለቡን ለማጠናከር
የገቢ ማስባሰቢያ ፕሮግራሞች ተዘጋጀ፡፡ ፒያሳ
አካባቢ የሚገኝ አንድ ቅ.ጊዮርጊስ የሚባል
መዝናኛ ቤት እርዳታ መሰብሰብ ጀመርን…
እዚህ ጋር ልብ በል…ከኮሚቴው ጋር በመሆን
እረዳታ በማሰባሰብ ሥራ የተጠመድኩት ቀን
ቀን ለክለቡ እየተጫወትኩ ማታ ማታ ደግሞ
ክለቡን ለማጠናክር በሚደረገው ርብርቦሽ
ከኮሚቴው ጋር እሰበሰባለሁ፡፡ በአጭሩ ቅ/
ጊዮርጊስ ከፈረሰ በኋላ እንደገና እየተጫወትኩ
ኮሚቴ እየሆንኩ የቅ.ጊዮርጊስ ሥምና ታሪክ
እንዳይጠፋ የበኩሌን አሻራ አሣርፊያለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- አባትህም የታወቁ የስፖርት
ሰው ነበሩ ሲባል ሰማሁ ስፖርት የቤተሰባችሁ
ባህል ነበር…?
ሎቾ፡- አባቴን በሞት ነጥቂያለሁ…፤…
በዚህ አጋጣሚ ነፍሱን በገነት ያኑርልኝና
አባቴ በህይወት ዘመኑ ከስፖርት ጋር
ትስስር ነበረው፡፡ እንደ እኔ እግር ኳስ
ተጨዋች ባይሆንም የታወቀ ብስክሌተኛም
ነበር…ሲወዳደር ባለውቀውም፡፡ከጓደኞቹ
ስሰማ ቀንደኛ የቅ/ጊዮርጊስ ደጋፊም ነበር…
እኔ ቅ/ጊዮርጊስ ስገባ እኔ የምኖረው አያቴ
ጋር ነበር…እሱ ከወንድሞቼ ጋር ለብቻው
ነበር የሚኖርው…አንድ ኮንትራክተር ጓደኛ
የነበረው አባቴ ሚዜውም ነበር…እንደ
ልጃቸውም ነበር የሚያዩኝ…አንድ ጊዜ
ያገኘኝና “…ሰለሞን ኳስ እንዴት ነው የት
ክለብ ገባህ…” ሲሉኝ ጊዮርጊስ C ስላቸው
“እ…አባትህ ጊዮርጊስ ስለሆነ ነው አንተም
እዛ የገባኸው” ሲሉኝ እኔ አባቴ የጊዮርጊስ
ደጋፊ መሆኑን አላውቅም ነበር…በኋላ ስለ
አባቴ ስሰማ ቀንደኛ የቅ.ጊዮርጊስ ደጋፊና
የመንግሥቱ ወርቁ የተለየ ፍቅርና ድጋፍ
ያለው ሰው ነበር…፡፡…ለእሱ ካለው ፍቅር
የተነሣ ከአንድ ጓደኛው ጋር ሆኖ ዋንጫ
ገዝተው በግል ሸልመውታል፤አባቴም
የጊዮርጊስ የልብ ሰው ነው፡፡
ሀትሪክ፡- … አጭር ስለሆንኩ ለብሔ
ራዊ ቡድን አልመረጥም ብለህ ስትጠራ
የደነገጥክበትን አጋጣሚ መለስ ብለህ ታስት
ውሰዋለህ… ?
ሎቾ፡- … በወቅቱ የነበሩት ተጨዋቾች
አካል ብቃት የተለየ ነው … በጣም
ፈርጣማና ረዣዥሞች ነበሩ … እኔ
ደግሞ በጣም አጭር ስለሆንኩ ምናልባት
ላልመረጥ እችላለሁ የሚል ስጋትን በውስጤ
ፈጥሮብኛል … በ1971 ይመስለኛል እነ
ሰብስቤ፣አያያ፣ ገብሩ ፣ተስፋዬ ይጠፋሉ …
እኔ ደግሞ ስራዬን እየሠራሁ ለጊዮርጊስ
እጫወታለሁ፡፡ እንደ አጋጣሚ በእለቱ እኔ
በመደበኛ ስራዬ ላይ ሆኜ ከፌዴሬሽን ወርቅዬ
የምትባል ፀሐፊ ስልክ ትደውልልኛለች …
ምነው በሠላም ነው ስላት “… ሎቾ ለብ/
ቡድን ተመርጠሃልና እሱን ላሳውቅህ ነው
… ፤ … በአስቸኳይ ትጥቅህን ይዘህ ወደ
ፌዴሬሽን እንድትመጣ …” ትለኛለች …
እኔም የምሰማውን ማመን ስላልቻልኩና
በዚህ ፍጥነት ለብሔራዊ ቡድን የመጣራት
እድል አገኛለሁ የሚል ግምት ስላልነበረኝ
… እባክሽን አትቀልጂ … ስራ ላይ ነኝ…
እንደዚህ አይነት ቀልድ አይመቸኝም ስላት
በጣም ከት ብላ ሳቀችና “ሎቾ ኧረ ቀልድ
አይደለም … ይልቁንስ መንግሥቱ ወርቁ
እያሠራችው ስለሆነ ቶሎ ትጥቅህን ይዘህ ና”
ብላ አስረግጣ ስትነግረኝ ከመደንገጤ የተነሣ
ልቤ በጣም መታ፣ ሰውነቴም ተንቀጠቀጠ፣
ለደቂቃ ባለሁበት ቦታ ፈዝዤ ቀረሁ…
ሀትሪክ፡- … ከዚያስ…?
ሎቾ፡- …በቃ …ምን ልበልህ… ሁለት
የተዘበራረቅ ስሜት በውስጤ ተፈጠረ…
ከፍተኛ ድንጋጤና … ከፍተኛ የደስታ
ስሜት … የምሰራው ፊያት ካምፓኒ ውስጥ
ነበር ወዲያውኑ ከሥራ ቦታ ወጣሁና ወደ
ቤት ሩጫ ጀመርኩ … ወይ ጉድ እኔ ለብ/
ቡድን ተጠራሁ…? … የማይታመን ነው …
እያልኩ ብቻዬን እያወራሁ ቤቴ ሄጄ ትጥቄን
ይዤ ስታዲየም ለመድረስ ከ2 ሰዓት በላይ
የሚወስደው 15 ደቂቃ እንኳን ሳይፈጅብኝ
እንደ ንፋስ በርሬ ስታዲየም ደረስኩ፤ ስታዲየም
ገብቼ ስመለከት እውነትም መንግሥቱ
ተጨዋቾቹን እያሠራ ነው፤ ተመልካቹ ደግሞ
ቁጭ ብሎ ልምምዱን ይመለከታል፤በጣም
እርግጠኛ ለመሆን መጀመሪያ ፀሐፊዋን
ላነጋግር አልኩና ጠየኳት “…እንዴ አንተ
ልጅ ምን ሆነሃል? ቀልዱን ተውና ትጥቅህን
ቀይረህ ግባ አለችኝ…” ፀሐፊዋ እንደዛ ብላኝውስጤ ግን በጣም ፈራ… እንዳለችኝ ቀይሬ
ከመሄድ ይልቅ ተመልካቾቹን ተቀላቅዬ
ተቀመጥኩ፤ መንግሥቱ አሰርታቸው የትንፋሽ
ጊዜ ሲሰጣቸው ያበጠ ይፈንዳ ብዬ ሄድኩኝ፡
፡ ወደ መንግሥቱ ጋ ስሄድ ልቤ በፍርሃት
ራደ… ሰውነቴም ተንቀጠቀጠ… እንደምንም
ብዬ ሄድኩና ራቅ ብዬ ቆምኩ… ቀና ብዬም
እሱን ማየትም አልቻልኩም… በዚህን ጊዜ
መንግሥቱ ወደ እኔ ጠጋ አለና “…ገና አሁን
ነው የምትመጣው፤በል ነገ ተመልሰህ ና…”
ሲለኝ እሺም እምቢ ሳልል ከአጠገቡ ዞር
አልኩ …ከእሱ ንግግር በኋላ ልቤም እፎይ
አለ ተረጋጋሁ… ለብ/ቡድንም በትክክል
መመረጤን አረጋገጥኩ… ፤…ይሄ ሁሉ
ምንድነው… ለብ/ቡድን መመረጥ ምን ያህል
ትልቅ ነገር እንደሆነና ማልያውን ለመልበስ
እንደምንጓጓ… ለአሰልጣኞች የምንሰጠውን
ክብር የሚያሳይ ነው፡፡ መንግሥቱ ትልቅ
አሰልጣኝ ነው… ማነው እሱን ፊት ለፊት
ደፍሮ የሚያዋራው? እሱ እኮ ንጉስ ነው…
የተለየ አሰልጣኝ ነው፡፡ ፍርሃቱም መረበሹም
የሚመነጨውም ከዚህ ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …እንደተባልከው በነጋታው
ሄድክ… ?
ሎቾ፡- …ሄድኩኝ…የነበረው ስብስብ
በጣም ያስፈራ ነበር…፤… ከሁሉም ትዝ
የሚለኝ ኃይሉ ጎሹ ነው… ትጥቅ ቀይሬ ስገባ
ኃይሉ ጎሹ አፍን በእጁ ይዞ በግርምት አይን
ያየኝ ነበር…
ሀትሪክ፡- …ለምን…?
ሎቾ፡- … እንዴት መጣ…?…ሉቾም
ለዚህ ደረስ…?… ብሎ ነዋ…. ምክንያቱም
ኃይሉ ጎሹ ሲጫወት ልብሱን ልብስ
አጣቢዎች ጋ ወስደን አሳጥበንለት ይዘንለት
እየመጣን እንሰጠው ስለነበር… ሲያየኝ
አላመነም፤በወቅቱ በብ/ቡድኑ ውስጥ
እነ መሐመድ ሸርዳድ፣ ክብሮም
ተወልደመድህን የመሳሰሉ ታላላቅ ተጨዋቾች
ነበሩ…ብቻ ስብስቡ ድንጋጤን ይፈጥራል፡
፡ አብሬያቸው የምሰራው ከማደንቃቸው
ከማከብራቸው ተጨዋቾች ጋር በመሆኑ
ገና ኳስ ስይዝ ስሜን ለጠራኝ ተጨዋች
ወዲያው አቀብላለሁ…አንዱ ከፊት ስሜን
ከጠራ ለአሱም… ከጎን አንዱ ሲጠራኝ
ለእሱም ወዲያው… እኔ የተሻለ ነገር ማድረግ
እየቻልኩ ወዲያው ስለጠሩኝ ብቻ ማቀበሌን
የታዘበው ኃይሉ ጎሹ… ” …ሎቾ አየሠራኸው
ያለኸው ልክ አይደለም… ችግርህን
ተረድቼዋለሁኝ… ከይሉኝታ ውጣ…፤ …
አንተም የብ/ቡድንተጨዋች ነህ… እነሱም
እንደ አንተ የብ/ቡድን ተጨዋቾች ናቸው…
በመካከላችሁ ልዩነት የለም… ስለዚህ ስምህን
ስለጠሩህ ብቻ ይቀየሙኛል እያልክ እየፈራህ
ወይም በከበሬታ ብቻ ወዲያው አታቀብል …
አንተ መጠቀም የምትችለውን ተጠቀም…፤…
ማድረግ የሚገባህንም አድርግ…”… አለኝ
…ኃይሉ ጎሹ የታላቅነት ተዕፅኖ ውስጥ
መውደቄን ተረድቶ ነው እንዲህ ብሎ
የመከረኝ…ከተወሰነ ጊዜበኋላ እየተላመድኩ…
እየተመሳሰልኩ መጣሁ…፡፡
ሀትሪክ፡- …ለአንተ ምርጡ አሰልጣኝ
ማን ነው…?
ሎቾ፡- …መንግሥቱ ነዋ…!…ንጉስ
መንግሥቱ ወርቁ…፤…ሀገራችን ምጡቅ
አዕምሮውን ሳትጠቀምበት ያለፈ በጣም
የምቆጭበት…ግን በጣም ምርጡ አሰልጣኝ
ለእኔ ከመንግሥቱ ውጪ የለም፡፡
ሀትሪክ፡- …ሎቾ የጨዋታ ዘመኑ
ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ስልጠናው ቢመጣም
አብዛኛውን ጊዜ ያሳለፈው በምክትልነት ነው
ይሉሃል…ምነው ዋና አሰልጣኝነትን ትፈራነበር…?
ሎቾ፡- …ትክክል ነው አብዛኛውን ጊዜዬን
በምክትልነት ነው ያሳለፍኩት…ይሄ የሆነው
ግን ከእኔ ፍራቻና ኃላፊነትን ደፍሮ ለመውሰድ
ከሚመጣ ችግር አይደለም…፤…ከአንተ
የተሻሉ ሲኒዬር አሰልጣኞች እያሉ እነሱን
ዘለህ ወደ ዋና አሰልጣኝነት አትመጣም፡፡
ያም ቢሆን ግን ወደ ውጭ እስከሄድኩበት
ጊዜ ድረስ ለአንድ አመት ያህል ዋና አሰልጣኝ
ሆኜ በክለቡ ታሪክ አፅፌያለሁ…የቅ/ጊዮርጊስ
ዋና አሰልጣኝ በመሆን በምስራቅ አፍሪካ
የክለቦች ሻምፒዮና ኬንያ ላይ ቡድኑን በዋና
አልጣኝነት ይዤ በክለቡ ታሪክ የመጀመሪያ
የሆነውን የነሐስ ሜዳልያ በታሪክ ለመጀመሪያ
ጊዜ አግኝቻለሁ…፤…ወደ አሜሪካ ከመጣሁ
በኋላም የሜሪላንድን ቡድን ለ11 አመት
ያህልም አሰልጥኜኝ ሁለት የኢትዮጵያዊያንን
ውድድርም አሸናፊ ሆኛለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- …በብሔራዊ ቡድን ደረጃ ደግሞ
ለመጀመሪያ ጊዜ ተመርጠህ የተጫወትከው
ከማዳጋስካር ጋር ነው…ልበል…?
ሎቾ፡- ..ሃሳቡን ደርሰህበታል…ለብ/
ቡድን ተመርጬ ለመጀመሪያ ጊዜ ለጨዋታ
የሄድኩት ወደ ማዳጋስካር ነው…ግን እዚያ
ሄጄ አልተጫወትኩም…፤…ትክክል ነህ የመ
ጀመሪያ የብ/ቡድን ጉዞዬ ማዳጋስካር ነው፡፡
ሀትሪክ፡- …በወቅቱ ወደ ማዳጋስካር
የሄደው ብ/ቡድን ተሸንፎም፣ተደብድቦም
ነው ከዚያ የተለመለሰው ይሄንን አጋጣሚስ
ታስታውሰዋለህ…?
ሎቾ፡- …(በጣም ሳቅ)…እኔም ዛሬም
ድረስ ሳስበው በጣም ይገርመኛል…፤…
በጨዋታው አሸንፈውናል… የሚፈልጉትን
ሶስት ነጥብም አግኝተዋል…።…ሰው
ተሸንፎ ይደበደባል…?…አሸንፈውም…
ደብድበውንም ነው የመለሱን…ሁላችንም
ከተደበደብን በኋላ ያልነው ነገር አሸንፈውን
የደበደቡን ብናሸንፋቸው ኖሮ ምን ሊያደርጉን
ነበር…?… ያልነው፡፡ ምክንያቱም ከስታዲየም
ወጥተን ሆቴል እስክንደርስ ድረስ የድንጋይ
ናዳ ነው ያወረዱብን፤ በፍፁም መቋቋም
ያልቻልነውን የድንጋይ ናዳ ነው እንደዝናብ
ያወረደብን…፤…የተሣፈርንበት አውቶብስ
መስታወት እላያችን ላይ ነው የረገፈው፤
አስታውሳለሁ ኃይሉ ጎሹ ነበር…“…ተኙ…
ተኙ ሊለቁት ነው ድንጋዩን…” ሲለን ሁሉም
ተጨዋች ተንደርድሮ ወንበር ስር… (ሳቅ)…
ከወንበር ስር ለመውጣት ቀና ስንል የሆነ
ቦታ ጓ…ይላል…መስታወቱም ይረግፋል..
ብቻ መድሃኒአለምና ሾፈሩ ጎበዝ በመሆኑ
ተረፈን እንጂ እንደነበረው ሀኔታ በህይወት
አንመለስም ነበር፡፡
ሀትሪክ፡- …ይሄን የማድረጋቸው ዋናው
ምክንያት ምንድነው…?…ከመሃከላችሁስ
የተጎዳ የለም…?
ሎቾ፡- ምክንያታቸውን የሚያውቀው
ፈጣሪና እነሱ ብቻ ናቸው…እኛም ግራ
የተጋባነው ለምን እንደዚህ እንዳደረጉ
ነው…፤…የከፋ ጉዳት የደረሰበት ባይኖርም
የመስታወቱ ስባሪ ያልዘነበበት ተጨዋች
ግን አልነበረም…፡፡…የመስታወቱን ስባሪ
ከፀጉራችን ውስጥ ለማራገፍ የነበረውን ስቃይ
ልነግርህ አልቻልም…፤…የመስታወቱን
ስባሪ ከየፀጉራችን እንደቅማል ስንለቅም ነው
የነበረው። የሚገርምህ የመልስ ጨዋታ አዲስ
አበባ ላይ ስለነበረ እነሱ በጣም ፈርተው ነበር…
የስፖርት ቤተሰቡም መደብደባችንና በመከራ
መውጣታችንን ሰምቶ ስለነበረ የመልስ ምት
ይሰጥ ይሆን…?… የሚል ግምት ነበረን፡፡
ግን እኛም እንደገመትነው እነሱም እንደፈሩት
አንድም ነገር አልደረሰባችውም፤ህዝቡ
እነሱ በማይሰሙት ቋንቋ ከመሳደቡ ውጪ
አልነካቸውም…ምናልባት ይሄ ስፖርታዊ
ጨዋነትና እንግዳ ተቀባይነት የሚለው ነገር
የተጫነው ይመስለኛል፡፡ አሁን ስላለው
የስፖርታዊ ጨዋነት ችግርና አደጋገፍ ስሰማ
ያ አጋጣሚ የተከሰተው አሁን ቢሆን ኖሮ
ምን ይከሰት ነበር ብዬ እጠይቃለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- በጨዋታ ዘመንህ ተለይተህ
ከምትታወቅባቸው ችሎታዎችህ አንዱ
ከርቀት በድንገት አክረረህ የምትመታቸውና
ለበረኞች ፈተና በሆኑት ሹቶችህ ነው…
ይሄንን ያዳበርከው ወይም የተማርከው ከማን
ነው…?
ሎቾ፡- … በራስህ በጥረትህ የምታሳድገው
ነገር አለ…በዚያን ጊዜ ግን ኃይሉ ጎሹ ኃይለኛ
ሹተር ስለበረ እሱ እንዴት እንሚመታ… ምን
እንደሚሠራ እየተከታተልኩ አጠና ነበር…፤…
እንደገና ኑሬ በሠፈር ቡድን ሲያሰለጥነን ባናና
እና የሹት አመታትም በመደጋገም እሞክር
ነበር…፤… ጊዮርጊስ እንደገባሁ በተደጋጋሚ
ሹት እመታ ነበር፡፡ ወደ ሹቱ ተስቤ የባናናምቱን እየረሳሁት መጣሁ…በዚህን ጊዜ ለገሠ
የሚባል ደወልልኝና “…ሎቾ ወደ አንዱ ብቻ
ትኩረት ስታደርግ አንደኛውን እየረሣኸው
ትመጣለህ… ስለዚህ ሹቱንም ባናና ምቱንም
ቀላቅለህ ተጠቀም…” ብሎ መክሮኛል…።
እኔ ደግሞ በባህሪዬ ምክር እሰማለሁ…
ምክሩን ተቀብዬ ሁለቱንም እንደ አስፈላጊነቱ
በመጠቀም ስኬታማ ሆኜበታለሁ፡፡
ሀትሪክ፡- ከዚህ ከሹት ጋር በተያያዘ
የበረኛ ክንድ ገንጥለሃል…፤… ለሌላ አንድ
ግብ ጠባቂ የመሰለፍ ብቻ ሣይሆን ከሀገርም
እንዲጠፋም እድል ፈጥረሃል ትባለለህ…?
ሎቾ፡- …(በጣም ሣቅ)…እርምጃችን
ሆኜ ከኦሜድላ ጋር ስንጫወት ነው…፤…
የኦሜድላው በረኛ ደግሞ ደረጀ ነው
የሚባለው… በጣም ጎበዝ በረኛ ነበር…
በወቅቱ የጦሩ ደጋፊዎች በሚቀመጡበት
ቦታ ባለው ጎል ላይ ነው… ከፍቃደ ጋር
ደብል ፓስ ተቀባበልንና ኳሱ እግሬ ስር ሲገባ
በሹት ነረትኩት… በረኛው ኳሷን እንደምንም
ቢያወጣትም ትከሻው ተናጋ…ረዥም
ሰዓት ህክምና ተደርጎለት ታስሮ ገባ…1ለዐ
እየመራናቸው እረፍት ወጣን …ከእረፍት
ስንመለስ እንደዚሁ አንድ ኳስ አግኝቼ
ያውም በግራ እግሬ አክርሬ ሹት ስመታ…
ደረጀ አድናለሁ ስል ኳሷ እጅን ጥሳ ገባች…
በዚህች ኳስ የተነሣ መጀመሪያ ተነቃንቆ
የነበረው ትከሻው የበለጠ ወለቀ…፤… ህክምና
ቢደረግለትም ተመልሶ መግባት አልቻለም…
በዚያው ወጣ ፡፡ እሱ ሲወጣ ተጠባባቂ
የነበረው ግርማ ተቀይሮ ገባ… በገባበት
ሰዓትም …በቀጣይ ጨዋታም… ጥሩ ስለነበር
ግርማ ለብ/ቡድን የመመረጥ እድል አገኘ፡፡
ለጨዋታ ወደ ጊኒ የሚሄደው ብ/ቡድን ውስጥ
ተካተተና ጊኒ ተጫውተን ስንመለስ ግርማ
አጋጣሚውን ተጠቅሞ አይቮሪኮስት ላይ
ጠፋ… በዚህ የተነሣ ሎቾ የግርማ ባለውለተኛ
ነው ተባለ… (ሳቅ)…
ሀትሪክ፡- …ሎቾ ሜዳ ውስጥ ነጭናጫ
ሆኖ ቀይ ካርድ ብዙ ጊዜ አያይም ይሉሃል…?
ሎቾ፡- …እኔ የቡድኔ አምበል በመሆኔ
ብዙ ጊዜ በዳኛ የሚደርሱብንን በደሎች ፊት
ለፊት እናገርለሁ…ዝም አልልም… በዚህ
የተነሣ ብዙዎች ነጭናጫ ያደርጉኛል፡
፡ በአምበልነቴ ስለምጠይቅ ብዙ ጊዜ ቀይ
ካርድ አይቼ አላውቅም፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ
በቀይ ካርድ ያስወጣኝ አለም አስፋ ነው
አስታውሳለሁ… ፤ …አለም መጀመሪያ
ዝቶ ስለነበር ነው ያስወጣኝ እንደሰማሁት…
ለምን ጠየከኝ ብሎ መጀመሪያ ቢጫ …ቀጥሎ
እይልን እንጂ ስለው ቀይ አውጥቶ አስወጣኝ፡
፡ ውሳኔው ልክ ባለመሆኑ ከፍተኛ ተቋውሞ
ነበር የቀረበበት… ያለፈ ነገር ቢሆንም…
ከሜዳ ስወጣ ደጋፊው በአንድ ድምፅ “…
አለምነሽ ሌባ…፤…አለምነሽ ሌባ…” ተብሎ
እንደተዘመረበት አልረሣውም…በጣም ሳቅ…
ሀትሪክ፡- …በእናንተ የጨዋታ ዘመን
ለብ/ቡድን ስትጫወቱ የሚሰጣችሁ ትጥቅ
ይመለስ ነበር፤ ካልመለሳችሁ ድጋሚ አትመረ
ጡም የሚባል ነገር ሠምቻለሁ እውነት
ነው…?
ሎቾ፡- …አዎን እውነት ነው…!… የብ/
ቡድን ትጥቅ እንደ አሁኑ ዘመን በሽበሽ
አልነበረም… ከተጫወትን በኋላ የመመለስ
ግዴታ አለብን…ይሄንን በተመለከተ አንድ
ነገር ላጫውትህ…
ሀትሪክ፡- …በጣም ደስ ይለኛል…?
ሎቾ፡- ለብ/ ቡድን ተመርጬ ነው፤
መጀመሪያ ከሞሪሺየስ ጋር ነበር ጨዋታችን
እነሱን አሸንፈን አለፍን… ቀጣይ ጨዋታችን
ከኬንያ ጋር ሞምባሳ ላይ ነበር…ሞምባሳ ላይ
ደግሞ ዝናብም በጣም ሞቃታማ አየር ነበር፡፡
ሜዳው ደግሞ የተፈጥሮ ሣር ስለነበር በጣም
ስለዘነበበት ሜዳው በጣም ጨቅይቷል…
ቦክቷል፡፡ ሜዳው አስቸጋሪ ቢሆንም
2ለዐ እየመራናቸው ነበር፡፡ በዚህ ጨዋታ
ለብሰን የገባነው ገምባሌ (ካልሲ) ደግሞ
እንደአሁኑ አይደለም… እየተጫወትን እያለ
የገምባሌው ላስቲክ ስለረገበ ወደታች እየወረደ
ቁርጭምጭሚቴን አልፎ ጫማዬን እየሸፈነ
አስቸገረኝ… አላጫወት ብሎ ትኩረቴንም
ሰረቀው…ወደ ጉልበቴ ስጎትተው መልሶ
እየወረደ በቃ ረበሸኝ፡፡
መጨረሻ ላይ የአንደኛውን እግሬን
ገምባሌ (ካልሲ) ጎትቼ አወጣሁትና ወረወሩ
ኩት፤ ጨዋታው ሲያልቅ በደስታ ሰክረናል
ማን ያስታውሰው …ረስቼው ወደ ሀገሬ
ተመለስኩ፡፡ እዚህ ስመጣ ትጥቅ አስረክቡ
ተባለ ከየት ላምጣው…አንድ እግሩን ኬንያ
ላይ ጥዬ መጥቻለሁ፡፡ መጨረሻ ላይ አንድ
እግሩን ላስረክብ ስል አንቀበልም አሉኝ…አደጋ
ውስጥ መግባቴን ሳውቅ አንድ ተመሳሳይ
ቀለም ያለው ገምባሌ (ካልሲ) ፈልጌ አገኘሁና
ለፌዴሬሽኑ አስረክቤ ተረፍኩ እንጂ ችግር
ውስጥ እገባ ነበር፡፡ በእኛ ጊዜ እንዳሁኑ
አይደለም የተጫወትንበትን ትጥቅ የመመለስ
ግዴታ ነበረብን፡፡