ሚቾ የዛምብያ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመሆን የመጨረሻ ሶስት እጮች ላይ በመካተት ከጫፍ መድረሳቸው ታውቋል።
የቀድሞው የፈረሰኞቹ አሰልጣኝ ሰርጆቪች ሚቾ ከሳምንታት በፊት በአዲስ አበባ ስታዲየም ተገኝተው የቀድሞ ክለባቸውን ጨዋታ መመልከታቸው ተከትሎ :: ፈረሰኞቹን በመረከብ ካሉበት የውጤት ቀውስ አውጥተው ወደ ዋንጫ ተፎካካሪነት ያሸጋግሩታል የሚሉ ሀሳቦች እንዲሰነዘሩ ቢያደርጋቸውም በመጨረሻ የዛምቢያ ቤሕራዊ ቡድን አሰልጣኝ ለመሆን ከጫፍ መድረሳቸ እየተሰማ ይገኛል። አሰልጣኙ በአፍሪካ ሊጎች ከፍተኛ እውቀት ያላቸው ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ከዛምቢያን ብሄራዊ ቡድን ጥሩ ስኬትን ያመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የኡጋንዳ ብሄራዊ ቡድን በማያዝ በአፍሪካ ዋንጫ መሳተፋቸው አይዘነጋም።