የፊታችን ቅዳሜ እሁድ እና ሰኞ በአ/አ ስታዲየም እና በክልል የሚካሄዱ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እንዳሉ ቀደም ብለን ማሳወቃችን ይታወሳል። ሆኖም ዛሬ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በደረሰን መረጃ መሰረት ቅዳሜ እና ዕሁድ አ/አ ላይ ሊደረጉ የታሰቡት አራት ጨዋታዎች (ኢትዮጵያ ቡና ከሀዋሳ ከተማ፣ ኢትዮ- ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ፣ መከላከያ ከመቐለ ከተማ እና ቅ/ጊዮርጊስ ከደደቢት) በቂ የፀጥታ ሀይል ባለመኖሩ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙ ተሰምቷል።
በዚህም ምክንያት የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በክልል የሚካሄዱት ጨዋታዎች ብቻ የሚኖሩ ይሆናል። እነዚህ የተሰረዙ ጨዋታዎች መቼ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የውድድር እና ስነ ስርዓት ኮሚቴ አባላት ከሰዓታት በኋላ በሚያደርጉት ስብሰባ የሚያሳውቁ ይሆናል። እኛም መረጃው እንደደረሰን የምንገልፅ ይሆናል።