አዲስ አዳጊዎቹ ሰበታ ከተማ መስኡድ መሐመድ፣ሳሙኤል ታዬ ና ደሳለኝ ደባሽን ሲያስፍርሙ ዳዊት እስጢፋኖስን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰዋል።
አምና ከጅማ አባጅፋር ጋር ያሳለፈው የቀድሞው ኢትዮ -ኤሌክትሪክ፣ኢትዮጵያ ቡና ና ደደቢት አማካይ መስኡድ መሐመድን በማስፍረም የመሃል ክፍላቸውን ማጠናከር ችለዋል።በ2003 ከኢትዮጵያ ቡና ጋር በውበቱ አባተ መሪነት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ያነሳው መስኡድ በድጋሚ ከቀድሞ እሰልጣኙ ጋር ሚሰራ ይሆናል።
በተመሳሳይ በ2003 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዋንጫን ከቡና ጋር ያነሳው ሳሙኤል ታዬ ከ7 ዓመታት የመከላከያ ቆይታ በኃላ ሰበታን ተቀላቅሏል።ከመስመር በመነሳት በሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሚታወቀው ሳሙኤል ታዬ ከቀድሞ አሰልጣኙ ውበቱ አባቱ ጋር በድጋሚ ሚገናኝ ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -
ሥስተኛው ፈራሚ ባሳለፍነው ዓመት ስሑል ሽረ በፕሪምየር ሊጉ አንዲቆይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከተው ደሳለኝ ደባሽን በአንድ ዓመት ውል ማስፈረም ችለዋል።መሃል ሜዳ ላይ እሚጫወተው ደሳለኝ ደባሽ ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ብርቱ ፈተና ሊጠብቀው እንደሚችል ይገመታል።
በተጨማሪ ሰበታዎች ዳዊት እስጢፋኖስን ለማስፈረም ከጫፍ የደረሱ ሲሆን ዝውውሩም በቅርብ ቀናት ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።