ባለፋት ቀናት በቃል ደረጃ ከሰበታ ከተማ ጋር ተስማምቶ የነበረው ውበቱ አባተ ዛሬ በይፋ የሰበታ ከተማ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ተቀጥርዋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዓመት ከፋሲል ከነማ ጋር የኢትዮጵያ ዋንጫን ማሸነፍ የቻለው ውበቱ ከ8 ዓመታት በኃላ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊጉን የተቀላቀለውን ሰበታ ከተማን በሊጉ ተፎካካሪ የማድረግ ከፍተኛ ስራ ይጠብቀዋል።
በክረምቱ የተጨዋቾች ዝውውር ላይ በንቃት እየተሳተፈ ሚገኘው ሰበታ ከተማ ለውበቱ አጨዋወት ይሆናሉ የተባሉትን ተጨዋቾች በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።
- ማሰታውቂያ -
ቅዱስ ጊዮርጊስን ለማስፈረም በመስማማት ውል አስከ ማሰር ደርሶ የነበረው ውበቱ አባተ ጊዮርጊሶች ሃሳባቸውን መቀየራቸው ተከትሎ ውሉ ሊሰረዝ ችሏል።