ፈረሰኞቹ በቀጣዩ ዓመት ላለባቸው የኢንተርናሽናል እና የሀገር ውስጥ ውድድሮች የተጨዋችን ውል በማደሰና አዳዲስ ተጨዋቾችንም በማስፈረም ላይ ይገኛሉ፡፡
ከሰሜን አፍሪካ ክለቦች ጋር ስሙ ሲያያዝ የነበረው ሳላሃዲን ሰዒድ ለተጨማሪ ሁለት ዓመት ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ለመቆየት ከስምምነት ላይ ደርሷል።በነገው እለትም በክለቡ ፅህፈት ቤት ተገኝቶ ፊርማውን እንደሚያኖር የክለቡ የፋዊ ገፅ አስታውቋል፡፡
በ2009 የኢትዮጵያ ኘሪሜየር ሊግ ለፈረሰኞቹ 15 ግቦችን ማስቆጠሩ እሚታወስ ነው፡፡