ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ
ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ህዳር
19/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን
አጠናቅቃለች፡፡
ለመሆኑ ምን ምን ጉዳዮችን ይዛ ይሆን?
-ከሀገር ውስጥ፡- የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግን ጨዋታዎች
በተመለከተ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዛሬ በይርጋለም ስታዲየም ከሲዳማ ቡና ጋር ስለሚያደርጉት ተጠባቂ ጨዋታ የቀድሞ ቡድኑን የሚፋለመው የቅዱስ ጊዮርጊሱ ሙሉዓለም መስፍን ስለጨዋታውና ሌሎች ከክለቡ ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን በማስመልከት እንደዚሁም የሲዳማ ቡናው አጥቂ አዲስ ግደይም የነገው ጨዋታ ላይ ለክለቡ ለብሄራዊ ቡድን በመመረጡና አዲስ አበባ በመገኘቱ ባይሰለፍም እሱም ስለቡድናቸውና ስለጨዋታው ምን ሊመስል እንደሚችል የሚላቹ አለ፡፡
ሌላው የኢትዮጵያ ቡናው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች አስናቀ ሞገስም በክለቡ አቋምና ወደፊት ክለባቸው ስለሚያስመዘግበው ውጤት እንደዚሁም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የእሁድ የሐዋሳና የወላይታ ድቻን አስመልክቶ አሰልጣኞቻቸው ከጨዋታው በኃላ የሰጡት አስተያየትን ሀትሪክ ጠይቃቸው
ምላሻቸውን ሰጥተውናል፡፡
-‘‘Oldies but Goodies” በሚለው ተወዳጅ አምዳችን ላይ
እንግዳችን በመሆን ወደ ኋሊት ወስዶ ትዝታውን የሚያስቃኘን
ባለተረኛ የቀድሞ ተጨዋች ደግሞ የኢትዮጵያ ቡና፣ የመከላከያ፣ የኢትዮጵያ መድን፣ የመተሐራ ስኳር፣ የአማካይ ስፍራ ተጨዋች የነበረው ቴዎድሮስ ብርሃኑ/ቴዲ ባሪያው/ ነው፡፡ በጨዋታ እያዋዛ ታሪኩን
ያስኮሞኩመናል፤ እንዳያመልጦት፡፡
ከባህር ማዶ፡- አርሰናሎች በሳምንቱ መጨረሻ ጣፋጭ ድልን ስላጣጣሙበት ምሽት የቼልሲው ዊሊያም ሊቨርፑል ላይ የአቻነትን ጎል አስቆጥሮ ስለተሰማው ደስታ የባርሴሎናው ሊዬኔል ሜሲ ከክርስቲያኖ ሮናልዶ ጋር ጓደኛማቾች እንደምሆን እርግጠኛ አይደለውም ስለማለቱና ሌሎች ያልተሰሙ አዳዲስና ትኩስ
ዘገባዎችን ነገ ማለዳ ይዛ እጅዎ ትገባለች፡፡
በርካታ አንባቢዎቻችን ባቀረባችሁልን ተደጋጋሚ ጥያቄ መሰረት
ሀትሪክን በሳምንት ሁለት ቀን በቅርቡ ይዘን እንቀርባለንና
ጠብቁን፡፡ ተጨማሪና ትኩስ መረጃዎችን በርካታ ተከታታዮች
ባሉት hatricksport.com ይጎብኙን፡፡
ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ የፊት ለፊት ገፅ ይህንን ይመስላል፡፡
መልካም ንባብ
ሳምንታዊ ባለቀለም የስፖርት ጋዜጣ የሆነችው ተወዳጇ ሀትሪክ ስፖርት ጋዜጣ እንደተለመደው ሁሉ ነገም ማክሰኞ ህዳር 19/2010 ዓ.ም በማለዳው በእጅዎ ልትገባ መሰናዶዋን አጠናቅቃለች፡፡
Hatricksport team