በኬንያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ ዋንጫ ላይ እሚሳታፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ቀን ልምምዱን በዛሬው እለት ጀምሯል ፡፡
በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ከተመረጡት 27 ተጨዋቾች መካከል 22 ተጨዋቾችን በመያዝ ለ1 ሰዓት ከኳስ ጋር ቀለል ያለ ልምምድሰርተዋል፡፡
አሰልጣኙ ከልምምድ በኃላ አጭር አስተያየት ለጋዜጠኞች ሰጠዋል፡፡
በሴካፋ ዋንጫ እስከምን ድረስ እንጎዛለን በላቸሁ አቅዳችኋል?
- ማሰታውቂያ -
”ማንኛውም ቡድን ወደ ውድድር የሚያመራው ለተሳትፎ ሳይሆን የውድድሩ አሸናፊ ለመሆን ነው። ተጫዋቾቹም ታሪክ ይሰራሉ ብዬ አስባለው። የመጫወት ፍላጎታቸው ከፍተኛ ነው። ”
ከተመረጡት 27 ተጨዋቾች 22 ብቻ ነው በዛሬው ልምምድ የተገኙት ?
“ተጨዋቾቹ ፍቃደኛ ቢሆኑም የክለቦቹ አመራሮች ሊልኩልን አልቻሉምየፋሲል፤ወልዲያ እና ፋሲል ክለብ ተጨዋቾች አልመጡ ። ከአመራሮቹ ጋር ተነጋግረን መግባባት ላይ ደርሰናል ፡፡ዛሬ ከሰዓት ወደ ቡድን ይገባሉ ብለን እንጠብቃለን”
በለፈው ሳምንት በቻን ላይ ያጋጠማቹሁ የፓስፖርት ችግር ነበር፡፡ አሁንስ በድጋሚ ይፈጠራል ብላችሁ ታስባላቹሁ??
” ከነገ ጀምሮ ፕሮግራሜ ይህ ነው። እነዚህ ተጫዋቾች ወደድንም ጠላንም አስፈላጊዎቻችን ናቸው ናቸው። ስለዚህ በፓስፖርት ችግር ምክንያት መቅረት የለባቸውም የሁላችንም ርብርብ ያስፈልጋል”
በተመረጡት ተጫዋቾች ላይ ሁለት፡ሁለት መሆኑ ያሳጣህ ተጫዋቾች አሉ ??
“አዎ በየ ክለቡ የተለያዩ ተጫዋቾችን አላካተትንም ሆኖም ግን አሁንም ያሉን ልጆች ጠንካራ ናቸው፡፡”