ስሑል ሽረ ሁለት የሜዳው ጨዋታዎች ከሜዳው ውጪ እንዲጫወትና የገንዘብ ቅጣት ተላለፈበት
በ19ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በሜዳው ሽረ ስታድየም ቅዱስ ጊዮርጊስን ያስተናገደው ስሑል ሽረ ጨዋታው ላይ የቀድሞው የክለቡ ቡድን መሪ ኤፍሬም ሓዱሽ በዕለቱ ዳኛ ኢብራሂም እጋዥ ላይ ባሳዩት ያልተገባ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በሆነ ባህሪ ምክንያት ስሑል ሽረ ሁለት በሜዳው የሚያካሂዳቸው ጨዋታዎች 200 ኪ.ሜትር ርቆ እንዲጫወትና የ 20 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበታል።
በያዝነው ውድድር ዓመት ክለቡ ላይ ላበረከተው አስተዋፅኦ በማመስገን ከክለቡ የተሸኙት ኤፍሬም ሓዱሽ በፈፀሙት የስፖርታዊ ጨዋነት ጉድለት ስሑል ሽረ መቀጣቱ ነገሩን አነጋጋሪ እድርጎታል።